ጥያቄ (ጎዶሊያስ ደስታ)
በሥልጣን ቅርምት በወንበር ሲሻሙ፣
በደንብ፣ በመመሪያ፣ በአንቀፅ ሳይስማሙ፣
ሁሌም ሕግ ሲያወጡ፤ ጋዜጣ ሲያትሙ፣
ስንት? ድሃ አለቀ፤ ስንቶቹስ? ወደሙ።
መቼም "Vote" ይደረግ አይቀርም መባሉ፣
እስኪ ሃሳብ ስጡ በግዝ ምትጣሉ።
ስንት? ንብረት ይውደም፤ ስንቱስ? ይቃጠሉ፣
ስንትስ? ሕይወት ይጥፋ፤ ስንቱስ? ይቀበሩ፣
ስንቱስ? አገር ይልቀቅ፤ ስንቱስ? ይባረሩ፣
ስንቱስ? ውሃ ይብላው፤ ስንቱስ? ይደፈሩ።
በየትኛው? አሃዝ፤ በየትኛው? ቁጥር በሙሉ ትስማሙ፣
በማንስ? መመሪያ፣ በየትኛው? ደንብስ ይፀናል አቋሙ።
በድሃ-ደም ቀለም የቀረፃችሁት፣ በተራበ አንጀት ላይ የቆመው ወንበሩ፣
ስንት? ዘመንስ ቀረው፤ ስንት? ዓመት ትኖሩ፣
እንደ ጥፋት ውሃ እስኪገለጥልን የፈጣሪ ሥራ፤ አምላካዊ ግብሩ።
ጎዶሊያስ ደስታ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



