ጌታቸው ቃሉ

ዘመነ ህዳሴ - ለሕዝቡ ትካዜ
ተሰማ ተደርጎ - ግፍ እንደአባዜ
ባለህዳሴዎች በልፅገናል ያሉ
ወገን በሰው ሀገር ሲሰቃይ እያዩ
ባዘን የወጣውን ጠቅልለው አሰሩ።

 

ዝቅ የሚለው እሱ የተረታ
ያለውን ትቶ ከየራሱ ኮታ
በገዛ ሀገሩ ስራ እንዳይፈታ
ወገን የሚኖር እየሆነ ከርታታ
ገዢ ስላጣ ነው የሚሆን አለኝታ፤

ቤታችን ጦቢያ ሁሉን የሰጠች
ልጆቿ ሲገፉ በጣም አፈረች
የመንግስት ያለህ ብሎ ሚጮኸው
ሚሰራ ጠፍቶ ካገር የወጣው
ታደጉኝ ብሎ ወዳገር ያለው
ሞቶ እሬሳው እንዳይመጣ ነው።

መንግስትስ የለም በኢትዮጵያ ምድር
ሕዝብ በሰው ሀገር ሲደነባበር
መላኩ ፈጣን መመለስ ምሱ
ልጆቹን ከጂ ከሞላ ከርሱ፤

ልጁን የናቀውን ማን ያከብረዋል?
እንዳለቀ ዕቃ ገንዳ ይከተዋል፤
ሀገር የሸጠን ማንስ ያምነዋል?
ዛሬ ልጆቹን ንቆ ይኮራል!
ነገ ሲሰደድ ደሞ ያገኘዋል!።

ጌታቸው ቃሉ
ኀዳር 8 / 2006
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ