አንቺን አስታዋሼ (ወለላዬ)
(ባልና ሚስት ፩)
(ወለላዬ ከስዊድን)
ባል:-
መቼ ትመጫለሽ
መቼ ልጠብቅሽ
ወይ መቼ ላምጣልሽ
መቼ ላቀብልሽ
ሽሮና ... ምናምን ስለተላከልሽ
ሽሮውን ውሰጂው
በርበሬውን ውሰጅ
ቅቤውንም ውሰጅ ...
ሚጥሚጣ ተይልኝ
እሱ ስለሆነ -
አንቺን ሚያስታውሰኝ
ሚስት:-
ምን ይሰራልሀል ብቻውን ሚጥሚጣ
ትደፋው የለም ወይ እንጀራ ስታጣ
ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)



