ወለላዬ ከስዊድን

አላለቅስም ያልኩት ...

እንባ የፈሪ ነው ብዬ ዋጥ ያ’ረኩት፣

አይቻል ተችሎኝ ይዤው የከረምኩት፣

ገንፍሎ ወጣና እንባዬ ፈሰሰ

ጉንጮቼን ሰንጥቆ ፌቴን አዳረሰ

በዛ እንባዬ መሀል አንገቴን አቅንቼ

ለፈጣሪ ጮኽኩኝ! እጆቼን ዘርግቼ

ምነው? ፈጣሪ አምላክ ምነው! ረሳኸን

ምነው! ይሄን በደል አላይልን አልከን

ምነው? የኛን ጩኸት ሰምተህ ጨከንክብን

ብዬ ወተወትኩት አልኩበት እዬዬ

አሁንም ይፈሳል አልቆመም እንባዬ

ምነው! ፈጣሪ አምላክ! ...


ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!