ጊዜ የሰጠው ቅል (ክንፈሚካኤል ገረሱ)
ክንፈሚካኤል ገረሱ
"ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል።" ይላሉ አበው፣
ጊዜ ማንሳቱ ጊዜ መጣሉ ጊዜ መስቀሉ ጊዜ ማውረዱ እሙን ነው።
እንደ አበው ብሂል፤
በጊዜ መራጃ በጊዜ ማሽን በጊዜ ሞተር፣
ቅል ድንጋይ ይሰብራል ይፈጫል ጠጠር።
ግና! ግና!
የጊዜ ቀመር የጊዜ ዑደት ሲገልጠው ጭምብሉን፣
ቅል ቅልነቱ ሕያው ሲሆን ሲላበስ ርሱነቱን።
እውን፤
ከሰበረው ካደቀቀው ቋጥኝ አለት፣
ይቆም ይሆን ከድንጋይ ፊት።
ክንፈሚካኤል ገረሱ
ታህሳስ 19 ቀን 2009 ዓ.ም.