ሚዛን አጣሁ (ክንፈሚካኤል ገረሱ)

"ሚዛን ማጣት" የተሰኘው የቼክ ሪፐብሊኩ አርቲስት ፔትር ሆሌክ (Petr Holecek) የሥነጥበብ ሥራ
ክንፈሚካኤል ገረሱ
ላ'ምሮዬ ሰላም ስፈልግ አማራጭ፣
ነገሩ ሳይገባኝ ተጉዤ ባቋራጭ።
እርም ብዬ ትልቅ ውጥን ግዙፍ ሃሳብ፣
ትንሽ ሳልም ትርኪምርኪ ስሰበስብ።
አድጋለሁ ስል እየጫጨሁ እየከሳሁ፣
እንደ ሕልሜ ሚዛን አጣሁ።
ክንፈሚካኤል ገረሱ
ኅዳር ፩ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.