የተረገመ ሰው (ጌታብቻ አንተነህ)
የተረገመ ሰው
ጌታብቻ አንተነህ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )
ወይ ለአባቱ አልሆነ ወይ ለእነዚያ እናቱ
እግዚአብሔር ያንሳልን ይህን የሰው ከንቱ
ከሁለት ዘር ተወልዶ አንድ መያዝ ያቃተው
ወገንን ተወገን እያባላ ያለው
ሀገርን ለማጥፋት ሀገር የሚቆርሰው
ምን ዓይነት መርዝ ሆነ ምን አይነት እሾህ ነው
ማስተዋል የነሳው የተረገመ ሰው
በመርገም አንነቅለው እርግማን ምግቡ ነው
በታገሉ ደም ላይ የተረማመደው
በፈሰሰ ደም ላይ ቃል ገብቶ የካደው
በሥልጣን መከታ ሀገር የሚገለው
ተደብቆ ይኖራል ጊዜ እስኪያጋልጠው
ከጌታብቻ አንተነህ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)