የቴዲ አፍሮ ፀሎት በእስር ቤት

አስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

ኢትዮጵያን ማፍቀሬ ወንጀል ሆኖብኝ

አንድነት ማፍቀሬ ጥፋት ሆኖብኝ

እየፎከሩ ነው በሞት ሊቀጡኝ፤

ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ሆነህ ከዙፋንህ

አንተስ በእነሱ ላይ ምን ይሆን ቅጣትህ?

 

እግዚአብሔር ሆይ እጄን አንስቼአለሁ

ፍርድህን አታዘግይ ብዬ እማጸናለሁ።

 

ፍቅርን በዘራሁ በጸብ አውድማ ላይ

ሠላምን ባሳደግሁ ኃይማኖትን ሳለይ

እነሆ ተገረፍኩ በሐሰት ጅራፍ

በእስር በስቃይ ነፍሴ እንድታልፍ።

 

የሠራዊት ጌታ ኢትዮጵያን ታደጋት

ከጭካኔ አገዛዝ እባክህ ነፃ አውጣት።

ለአንተ አንመችም ይህንን አውቃለሁ

በፀጋ ታደገን ብዬ እጮሃለሁ።

 

ለብዙ ዘመናት ቃል ገብተህልን

በነፃነት ጥላ በድል መርተኸን

ዛሬ ምነው ጌታ ለስቃይ ዳረከን

እኛን በመሰሉ ፍዳ አስቆጠርከን።

 

እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ ኢትዮጵያን አትርሳት

ከሰማየ ሰማያት ሠላምን ላክላት።

ህዝቦችዋ ተባብው በፍቅር በሐሴት

ለመኖር አብቃቸው በእውነተኛ ሕብረት።

 

እኔስ ልኑር በቃ በእስር በግዞት

ሱባዔ ገብቼ ለሀገሬ አንድነት።

ምህላዬን እባክህ በፍጥነት ስማኝ

ህዝቤን ሳትዘገይ ነፃ አውጣልኝ።

 

ፀሐይ ትወጣለች‼!


አስፋወሰን ዓለምሰገድ 01/05/2009 This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ