ወጋየሁ ደግነቱ

የዝነኛውን ኮከብ ድምጻዊ የወጋየሁ ደግነቱን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ሰምቼ የተሰማኝን ኀዘን ለቤተሰቡና ለመላው የሙዚቃ አፍቃሪ ስገልጽ እጅግ ጥልቅ በሆነ ስሜት ነው። ብርታቱን ይስጣችሁ! እያልኩ ትቶልን ካለፈው ጥዑም ሙዚቃዎች መገናኛ ብዙኀን እንዲያሰሙን እጠየቅሁ፤ የበኩሌን ኀዘን በሚቀጥለው ግጥም መግለጽ እሻለሁ።

ወጋየሁ ደግነቱ

ክንፈ ሚካኤል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

ሰጎን[1] ኦልኬስትራን አቅንቶ ያቆመው

የወበራው ጀግና ወጋየሁ ደግነቱ ነው።

 

በልጅነት ወራት የማንጎራጉረው

“እናትና አባቴን በተለየኋቸው”

ትዝ ይለኛል ዛሬም ግጥሙ ከነዜማው።

ዓመት አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር

አንበሳና ሰጎን ሁሌ ፍክክር

አሸናፊ የሌለው ያመት ውድድር

ይተባል ይገናል ጊዜው ሲጨምር።

 

መስፍንና ሲሳይ ካንበሳው ክ/ጦር

ወጋየሁ መርአዊ ከምስራቃዊ ሰጎን

ነበሩ ከዋክብት ከምስራቁ ወገን።


 

ክንፈ ሚካኤል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ሐምሌ ፲፫ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. - ሜልንበርን፣ አውስትራሊያ

[1] የሐረር ፓሊስ ምስራቃዊ ሰጎን የወታደሩ አንበሳው ክ/ጦር ኦልኬስትራ ይባል ነበር

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ