ደም ያለበት ጳጳስ

(የመነኩሴው ደም ይጮኻል!)

ከምዕመን (ናይሮቢ - ኬንያ) መስከረም 1999 ዓ.ም.

ከዘፍጥረት ዓለም - ከኦሪት ትዕዛዛቱ

… “አትግደል” … ነበር ቃሉ - አንደኛው ከአሥርቱ፤

 

እግዚኦ ማኅረነ ክርስቶስ …!

ነፍሰ-ገዳይ ሲሆን ጳጳስ …

ያውም “ብፁዕ ወቅዱስ …”

 

(… ቃለ-ክርስቶስ ከጥንት የምናውቀው

ሳዑል ወደ ጳውሎስነት ሲቀየር ነው፤

በኛስ ዘመን ጉድ መጣብን

ጳውሎስ ሳዑል ሲሆንብን!!)

 

… የመነኩሴው ደም ይጮኻል - የፈሰሰው ከታቦቱ ስር

የሰማዕትነት ዋጋ - እማይዘነጋ ለዘወትር!

 

… ንስኀ ሳይገባ ለራሱ

ሳትማር ተኮናኝ ነፍሱ

እንዴት ሊያስተምረን ነው ጳጳሱ?!

 

አባታችን ሆይ የሰማዩ - በቃ! በለን አሁንስ

“ነፍሰ-ገዳይ” ጳጳስ እየዞረ - ምናለ ታቦት ባያረክስ?

አቡነ ዘበሰማያት … - ኢትዮጵያን ይቀር በላት

ነፍሰ-ገዳይ ጳጳስ - ዳግም እንዳይነግሥባት!

 

አቤቱ ኧረ ተለመነን!?

ለዘላለም ዓለም አሜን!!!


 

ከምዕመን (ናይሮቢ - ኬንያ) መስከረም 1999 ዓ.ም.

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ