አጫጭር የሀገር ቤት ምናብ-አከል ዜናዎች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይነጋል በላቸው

  • ወያኔ ተለጣፊን በማፍራት የሚስተካከለው እንደሌለ አንድ ታዋቂ የፖለቲካ ተንታኝ ገለጹ

አዲሱ ሹመት የጭቡ መሆኑን ዜጎች ገለጹ

“የሰሞኑ የወያኔዎች የቁጭ በሉ ሹመት የልጅነት ጊዜ የዕቃ ዕቃ ጨዋታን ያስታውሰኛል። እልም ያለ ዐይን ያወጣ የጭቡ ሥራ ነው። ማንን ሊያታልሉ ይሆን እንዲህ እንሻቸው የሚጥሱትን የራሳቸውን ሕገ-መንግሥት ተብዬ ሳይቀር ሽረው ይህን የመሰለ ከማሳቅ ባለፈ የማንንም ቀልብ የማይስብ የአራድነት አይሉት የቂልነት ሥራ የሚሠሩት?” በማለት የገለጡት አንድ የመንደር አዛውንት፤ እንደዚህ ዓይነት ለአንዲት ድሃ ሀገር ለታይታዊው የማስመሰል ቲያትር ሲባል ብቻ ሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን በመደርደር የብሔሮችን የሥልጣን እኩልነት ለማሳየት መሞከራቸው ሕዝቡን የመሳደብ በንቀት ልምጭም የመማታት ያህል እንደሆነ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አጫጭር የሀገር ቤት ወሬዎች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

(ምናባዊ) ይነጋል በላቸው

  • የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች በሥራቸው መሰላቸታቸው ተገለጠ
  • ፍርሀትና ትግስት ውሕደት መፍጠራቸው ተነገረ
  • የአዲስ አበባ መንገዶች መጨናነቅ ችግር ማስከተሉ ይፋ ሆነ
  • የአምልኮ ሥፍራዎች ለድምፅ ብክለት ተጠያቂ ናቸው ተባለ
  • በአዲስ አበባ ያገለገሉ ዕቃዎችን መሸጫ ሱቆች እየተበራከቱ መሆናቸው ተገለጸ

ባለፈው የዜና ዕወጃችን ይህን መሰል የሀገር ውስጥ አጫጭር ወሬዎች ዘገባ ቢያንስ በሣምንት አንድ ጊዜ እናቀርባለን ብለን ቃል ባልገባነው መሠረት ከመጀመሪያው የቀጠለውን የዛሬውን ዝግጅት ቀጥለን የምናቀርበው በታላቅ የደስታ ስሜት ነው። እነዚህ ወሬዎች በምናባዊ የአቀራረብ ፋሽን በመዋዛታቸው የአንዳንዶችን አመኔታ በቀላሉ ላያገኙ እንደሚችሉ ቢጠረጠርም ሀሰት እንዳልሆኑ ግን ለተከታታዮቻችን በዚህ አጋጣሚ ልናስታውስ እንወዳለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አጫጭር የሀገር ቤት ወሬዎች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

(ምናባዊ አጫጭር ዜናዎች) ይነጋል በላቸው

ኢትዮጵያ የሁለት ፕሬዝደንቶች ሀገር መሆኗ ተገለጸ - ዘግይቶ የደረሰ አስደሳች ዜና - የመለስ ፎቶ ሀገር አስለቀቀ - የኑሮ ውድነቱ ሕዝብን እያስለቀሰ ነው -የኢትዮጵያ ኤፍ ኤሞች መንግሥታዊ አደራቸውን በብቃት እየተወጡ ናቸው ተባለ - New Tense has been found in Ethiopia!

ኢሣት ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ እንዳይሠራጭ ታፈነ

ከአንድ ዓመት ተኩል ስኬታማ አፈና በኋላ የተጣለበትን ተደጋጋሚ የአየር ሞገድ እመቃ ተቋቁሞ ላለፉት ጥቂት ሣምንታት በኢትዮጵያ ሥርጭቱን ጀምሮ የነበረው የኢሣት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ከትናንት በስቲያ ኅዳር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ዝነኛ ሥርጭቱ መቋረጡ ታወቀ። ባለፉት የሥርጭት ጊዜያት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የብሶት መተንፈሻና የታፈኑ የሀገር ቤት ዜናዎች ማወጃ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”እናቴ አልዳነችም! ...‏”

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ, PM Hailemariam Desalegn(ምናባዊ)

ፊልጶስ

እናት ለልጇ ያላትን ፍቅር መለኪያ፣ ወሰን፣ ድንበርና ግዜ ይኖረው ይሆን? … በእግዚአብሔር ፈጣሪነትና ፈቃድ፤ ዘጠኝ ወር በመሀጸኔ ተሸክሜ፣ በጭንቅና በጣር አምጨ ወለድኩት። አርባ ቀን ሲሞለው እምነታችን በሚያዘው መሰረት ክርስትና አስነሳሁት። በክርስትና ስሙ ኃይለማርያም ብዬ ስም አወጣሁለት። ጡቶቼን እያጠባሁ፣ የምችለውን ሁሉ እያደረኩና የማይጠገበውን የእናትነትን ፍቅር እየመገብኩ አሳደኩት። ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤትም ላኩት። ልጄም ለቁምነገር በቃ። ከስልጣን ወደ ስልጣን ተሸጋገረ። ከትልቅ ደራጃም ደረሰ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርም ተባለ። ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ የኔ ልጅ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከባህር የወጣች አሳ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ Birtukan Mideksaተስፋዬ ገብረአብ

ብርድ እንዳገረጣት - እንደ ወይራ ቅጠል፣

ድምፁ እንደሚሰማው፣ እንደ ክረምት ማዕበል፣

በምልምል ግንድ ላይ፣ አንድ ዘለላ ቅጠል፣ ሆኜ የአሸንቋጦ፣

ነፋስ አወዛውዞ፣ ሊጥለኝ ነው ቆርጦ፣

(ግጥም - አሌክሳንድር ፑሽኪን)

- አያልነህ ሙላቱ እንደተረጎመው -

 ከፖቶማክ ወንዝ ዳርቻ ከሚገኘው ሬስቶራንት በረንዳው ላይ ተቀምጣለች። ይህ ዋሽንግተን ዲሲ ነው። ወንዙን የተሻገረ ግን ቨርጂኒያ ገባ ማለት ይሆናል። ዓይኖቿን አሻግራ ወንዙን በዝምታ ስታጤነው ቆየች። ከመኖሪያዋ ርቃ ወደዚህ ሬስቶራንት የመጣችው ብቻዋን መሆን በመፈለጓ ነበር። ያዘዘችውን የሎሚ ጭማቂ ቀመስ አደረገችለት። እና እጇ ላይ ሲታሽ የከረመውን የቾምስኪ መጽሐፍ ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አንድ መልከቀና ጎረምሳ በቀጥታ ወደሷ ሲመጣ ተመለከተች። በፈገግታ እንደተዋጠ እጁን ዘርግቶ ሰላምታ አቀረበላት። አላወቀችውም። ቢሆንም እሷም ፈገግ ብላ የተዘረጋላትን እጅ በትህትና ጨበጠች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!