ሠላማዊ ህልም (ተስፋዬ ገብረአብ)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ተስፋዬ ገብረአብ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

- ፩ -

“ተረት ተረት …”

“የላም በረት …”

“… ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ልጅ ነበረ። ሲኖር ሲኖር ቆይቶ ከሌሊታት አንድ ሌሊት ህልም አለመ። አዲስ ልብስ የለበሰ ይመስለዋል። አዲስ ጫማም አድርጎአል። ወላጅ እናቱ በሚያብረቀርቅ ጠርሙስ አዲስ ወተት ሞልተው ይሰጡታል። እሱም ወተቱን ተቀብሎ በለምለም ሳር ላይ እየተራመደ ያንን የወተት ጠርሙስ ይዞ ከአንድ እጅግ ያማረ ውብ ቪላ ውስጥ ሲገባ ህልም አለመ። ህልሙ ከዚያ በላይ አልቀጠለም …” ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኔና ሥልጡኑ ጎረቤቴ (ክፍል ፪)

የአንባብያን ድምፅ: 1 / 5

Star ActiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

(ክፍል ሁለት)

በልጅግ ዓሊ

ጎረቤቴ አንድ ቀን ወደ ቤቴ ብቅ ብሎ ከወትሮ በተለየ ረጋ ባለ ሁኔታ ትዳር መያዝ እንደፈለገ ነገረኝ። እኔም የትዳርን ጥሩነትና አሁን ወቅቱ እንደሆነ አስረድቼው ጨዋታችንን ቀጠልን። ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኔ እና ሥልጡኑ ጎረቤቴ (፩) (በልጅግ ዓሊ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

በልጅግ ዓሊ

ጎረቤቴን በጣም እወድዋለሁ፣ እሱም ይወደኛል። ለብዙ ዓመታት አብረን ጎን ለጎን ኖረናል። እንመካከራለን፣ እንወያያለን፣ ችግር፣ ኀዘን፣ ደስታም አብረን እንካፈላለን። ገና ወንደላጤ ከነበርንበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ትዳር ይዘን ልጆች ወልደን እስከምናሳድግበት ድረስ ጎረቤታሞች ነን። ልጆቻችንም አብረው ነው የሚጫወቱት። የዓመት በዓልም እንደ ሀገራችን ደንብ አብረን ነው የምናሳልፋው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀለበቴን ስጧት (በልጅግ ዓሊ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በልጅግ ዓሊ

“አቤት! አቤት! ደስ ማለቱ፣

አቤት! አቤት! ደስ ማለቱ፣

ያ ምንደኛ የኢህአፓ ቅጥረኛ፣

በቀይ ሽብር ተመትቶ መንገድ ላይ ሲተኛ”

- የፋሺስቶች መዝሙር 1970 ዓ.ም.

የከርቸሌ ፍርደኛ ከወትሮው ለየት ያለ ኀዘን ሰፍሮበታል። የወቅቱ አስከፊ ገጽታን የማይገነዘቡ የወንጀል እስረኞች እንኳን አዘውትረው ከሚያወሩት የሌብነት ገድል ተቆጥበዋል። ምን ትሆን ይሆን? የሚለው ጥያቄ በእያንዳንዱ እስረኛ አዕምሮ ውስጥ ይጉላላል። የልጅቷን የደስ ደስ የማያውቅ የለም። ለባሏ ያላት ፍቅር ደግሞ የተደነቀና እያንዳንዱ እስረኛ የራሱ የሚመኛት ዓይነት ሚስት ናት። እሁድ እሁድ ሕፃን ልጃቸውን ታቅፋ ለጥየቃ ሰልፍ ለመያዝ በሌሊት ነው የምትደርሰው። እሁድ ብዙ ምግብ ስለሚመጣ የምግቡን ማጣት የምታስተጓጉለው ሰኞ ሰኞ ነው። እሱም በግድ በእስረኛው ልመና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሽጉጤ ደሜ - የደም ድምፅ (በልጅግ ዓሊ)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

በልጅግ ዓሊ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የዛሬውን አያድርገውና አዲስ አበባ ትንሽ ከተማ ነበረች። አሁንማ በጣም ሰፍታለች። የህዝቡም ቁጥር ጨምሯል። የሽጉጤ ደሜ ታሪክ ሲፈፀም አሁን ካላት ስፋት ጋር ሲወዳደር የትየለሌ ነው። ከሦስት አስር ዓመታት በፊት አንዱ ሠፈር የተፈፀመው ሌላው ሠፈር ይሰማ ነበር። ዛሬማ ምኑ ቅጡ ብሽቅጥቅጡ እንኳን ሌላ ሠፈር የተሠራው የጎረቤትም መርዶ አይሰማም። አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት ሠፈሮች አንዱ ”ልደታ” ነው። ሠፈሩ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ጥቅጥቅ ብለው የሚኖሩበት ነው። የሠፈሩ ነዋሪ ችግረኝነቱ ሳይበግረው ተፋቅሮ የሚኖር ሲሆን፣ በደስታም ይሁን በኀዘን የማይለያይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...