የለም ትንሽ ሥራ (ክንፈሚካኤል ገረሱ)
ክንፈሚካኤል ገረሱ
ወያላነት ቢሆን የታክሲ አጋፋሪ፣
ቢሆን ሊስትሮነት ጫማ አሳማሪ።
እረኝነት ቢሆን ውሎ ከነቦራ፣
ቢሆን ግንበኝነት ብሎኬት ድርደራ፣
ትንሽ ሃሳብ እንጂ የለም ትንሽ ሥራ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ክንፈሚካኤል ገረሱ
ወያላነት ቢሆን የታክሲ አጋፋሪ፣
ቢሆን ሊስትሮነት ጫማ አሳማሪ።
እረኝነት ቢሆን ውሎ ከነቦራ፣
ቢሆን ግንበኝነት ብሎኬት ድርደራ፣
ትንሽ ሃሳብ እንጂ የለም ትንሽ ሥራ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ይቺ መዝጊያ ትሁን
መቶ አራት ግጥሞችን ተሸክሜ ይዤ
ረቡዕ ረቡዕ ስጥል አንድ አንዷን መዝዤ
በዚች በአሁኗ ቀን በጨበጥናት ሳምንት
ወሩን ስደምረው ሆነኝ ሁለት ዓመት
ዳግም በአዲስ ዓመት እስከምንገናኝ
የዘንድሮው መዝጊያ ይቺ ትሁንልኝ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ክንፈሚካኤል ገረሱ
ጊዜን እያሰሉ በሰዓት መጥኖ፣
በጥበብ በምጥቀት ዓላማን ከውኖ።
ትላንትናን ሳይሆን ዛሬን እየኖሩ፣
የሕይወትን ቅኔ እየመሰጠሩ።
እንደ ጧፍ ተቃጥሎ እንደ ሰምም ፈሶ፣
ለተተኪው ትውልድ አሻራን አውርሶ።
ይህ ነው መኖር ማለት መመላለስ በዓለም፣
እንደ ሻማ ቀልጦ የአዳም ዘርን መጥቀም።
ክንፈሚካኤል ገረሱ
ከዕለታት አንድ ቀን ስድስት ሰዓት ግድም፣
ገሚሱ ሲያሻቅብ ገሚሱ ሲያገድም።
አለቃ ደክሟቸው ወደ ቤት ሲያዘግሙ፣
አመሻሽ አዳሩን ሲቃኙ ሲያልሙ።
በሃሳብ ጅረት ባህር ሲቀዝፉ ሲዋኙ፣
ካንድ ከሚያውቁት ሰው ድንገት ተገናኙ።
ክንፈሚካኤል ገረሱ
ዓመት ለፍልፎ፣
ቃል ተንቆርቁሮ፣
ጆሮ አደንቁሮ።