ለመለስ የተፃፈ ደብዳቤና የመለስ መልስ

ለመለስ የተፃፈ ደብዳቤና የመለስ መልስከፍቃዱ ጌታቸው ለመለስ

(ፍቃዱ ጌታቸው)
እንደምን አለህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ
እኛማ ይሔውልህ
ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ
በየአደባባዩ እንላለን ዋይ ዋይ
ዛሬም ጀነራልህ ተኩስ ነው ትዕዛዙ
ወገን ያጋድማል የግፍ አፈሙዙ
ለምንድን ነው ስንል ስምክን አስቀድመው
ከክርስቶስ በላይ ምስልህን አትመው
ቅዱስ መጽሐፍ ይመስል
ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው
ቢረፈርፉንም አላለቅንምና
ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፵፮

ታጣቢና አስታጣቢ

ፎጣ በትከሻ ውሀሀውን በጣሳ
ይዞ ሲያቀርብለት ታጣቢ ቢነሳ
አስጣታቢ እንቢ አለ የጁን ወሀ ነሳ
እንደዚህ ነበሩ ታጣቢ አስታጣቢ
የሚከባበሩ አንዱ ለአንዱ አሳቢ
ዛሬ እንዲያስታጥብ አንዱን ብንልከው
ብድግ ቢልለት ታጣቢ እንደ ድሮው
አስታጣቢ ጎኑ ተቀምጦ አስታጠበው

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ