የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፵፭
ከወራትም አታልፍ
መትረየስ ብትደግን - ታንክ ብታወጣ
ለሊትና ቀኑን - ጥይት ብታንጣጣ
ኣጋዚን ይቅርና - ሰይጣን ብታሰልፍ
የድሜህ ሐረግ ደርቆአል - ከወራትም አታልፍ
ከወራትም አታልፍ
መትረየስ ብትደግን - ታንክ ብታወጣ
ለሊትና ቀኑን - ጥይት ብታንጣጣ
ኣጋዚን ይቅርና - ሰይጣን ብታሰልፍ
የድሜህ ሐረግ ደርቆአል - ከወራትም አታልፍ
ቃል እገባለሁኝ
ተነስ እንዳይባል - እራሱ ተነስቷል፣
ተውም እንዳይባል - ንፁህ ደሙ ፈሷል፣
እንግዲህ በሀገር - ነፃነት እስኪገኝ፣
ከህዝብ ጋር ልቆም - ቃል እገባለሁኝ!
ወለላዬ ከስዊድን
አላለቅስም ያልኩት ...
እንባ የፈሪ ነው ብዬ ዋጥ ያ’ረኩት፣
አይቻል ተችሎኝ ይዤው የከረምኩት፣
ገንፍሎ ወጣና እንባዬ ፈሰሰ
ጉንጮቼን ሰንጥቆ ፌቴን አዳረሰ
በዛ እንባዬ መሀል አንገቴን አቅንቼ
ለፈጣሪ ጮኽኩኝ! እጆቼን ዘርግቼ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ጌታቸው አበራ
ለ’ክቡር’ ጠቅላይ ሚኒስትር፣
ለኢህአዴግ ሊቀ-መንበር፣
ጠቅላይ ‘አዛዥ’ ለ”ኣግዓዚ” ጦር ...፤
ይድረስ ለአቶ ኃይለማርያም!
በስምዎ ባዘሏት ወላዲተ-አምላክ ...
በወልድ በእየሱስ ክርስቶስ ስም ልያዝዎ፣
ኢትዮጵያን በጥይት አያቃጥሏት ...
እግዚአብሔር አባት ይቅር ይበልዎ!
ማርእሸት መሸሻ
አዋጅ አዋጅ አዋጅ፣ የደበሎ ቅዳጅ
እንቁጣጣሽ ቀርቷል፤ የለም ዓመት በዓል
መልዕክቱን አስተላልፍ ለዘመድ ለወዳጅ
የእልፈ አዕላፍ ዘመን ወግና ልማዱ
ኢትዮጵያዊነቱ፣ ነባር ታሪክ አምዱ