የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፲፯
ከወደድነው እንጂ አብረን ከጠላነው
ቀጥ ያለው ጠማማ ጣፋጩም ሬት ነው
ፊልተር የመሰለው ጥርት ያለው ጠላ
የተበጠበጠ ይባላል አተላ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከወደድነው እንጂ አብረን ከጠላነው
ቀጥ ያለው ጠማማ ጣፋጩም ሬት ነው
ፊልተር የመሰለው ጥርት ያለው ጠላ
የተበጠበጠ ይባላል አተላ
ሙሉውን አስነብበኝ ...አንተን ጌታ ሲፈጥር
እሱን ጌታ ሲፈጥር
ትልቅ ነው ትንሽ ነህ
አላለህም ነበር
ከሱ በታች አ’ርጋ
ያዋለችህን ሆድ
ባቅምህ ድፈንና
ውጣ ከመዋረድ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሲበሉ ካልበሉ ሲጠጡ ካልጠጡ
ከሰው ካልወሰዱ የጅዎን ካልሰጡ
ወይም ካልጎተቱ ወይ ካልተጎተቱ
ካላስፈተፈቱ ወይ ካልፈተፈቱ
ወይም ካልደለቁ ወይ ካላዳለቁ
እንኳንስ አኩርፈው ቢስቁም አይደምቁ
ሙሉውን አስነብበኝ ...እንደናቴ የሚተወኝ
በጥፋቴ የማይወቅሰኝ
በይቅርታ የሚዘለኝ
ማን ሊመጣ ወዴት ሊገኝ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ልጅነቴን እንግልት
ወጣትነቴን ዕንክርት
ጉልምስናዬን ፍርሃት
ጋጥ አድርጎ እንክት አድርጎት
በባዶ አካል በባዶ ቤት
አሳዘነኝ መምጣቱ ሞት
ሙሉውን አስነብበኝ ...