የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፱
ማነው የመከረው ይህ ሁሉ ሙሽራ
ዝም ብሎ ያገባው ትዳርን ሳይፈራ
ሁሉንም ይወቁት በሉ ንገሯቸው
ሲኦልና ገነት ትዳር ማህል ናቸው
ማነው የመከረው ይህ ሁሉ ሙሽራ
ዝም ብሎ ያገባው ትዳርን ሳይፈራ
ሁሉንም ይወቁት በሉ ንገሯቸው
ሲኦልና ገነት ትዳር ማህል ናቸው
ነቢዩ ሲራክ
ማጣቱ ዘልቆ ሳይጎዳኝ፣
ድህነቱን ችየ በኖርኩኝ፣
እህ ብየ ተመስገን ብየ ኑሮ በገፋሁኝ፣
የመኖሬን ተስፋ ቀማችሁኝ፣
ሙሉውን አስነብበኝ ...አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ
አውሬነቱን ያልጨረሰ
ከ’ጭራቅ’ የባሰ!
እንደ በግ ፍሪዳ
ሰው አርዶ የሚበላ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሶምራን
ምን ያለ ዘመን ነው ተወግዞ ያስወገዘ
የሰው ደም ቀዝቅዞ ለውሃ ያገዘ
እንስሳ መሰሉን ሲበላ አላየሁም
ሰው ሰውን ለመብላት ምነው አላቅማማም?
ሙሉውን አስነብበኝ ...ገ/ኢ. ጐርፉ
ውበትሽ አክለፍልፎኝ
ድቅን ብሎ እየታየኝ
ከሰው ሁሉ አላክፎኝ
እንደ አውሬ በርሃ ለየኝ።