ማን ነው የረገመሽ? (ያለው ጌትነት)
ያለው ጌትነት
አፄ ዮሐንስ ነው ዳግማዊ ምኒልክ፣
አባ ኮስትር ካሳ ቆራጡ የጦር ልክ፤
ጃንሆይ፣ መንግሥቱ፣ ወይስ የኛው መለስ፣
ስቃይሽን ያበዛው የማን ነው ግብረ-መልስ፤
ማን ነው የረገመሽ ያሳነሰሽ ከዓለም፣
ታሪክሽን ያጠፋ ጣዕርሽን የሚወድ ለሞትሽ የሚቆም?
ሙሉውን አስነብበኝ ...ያለው ጌትነት
አፄ ዮሐንስ ነው ዳግማዊ ምኒልክ፣
አባ ኮስትር ካሳ ቆራጡ የጦር ልክ፤
ጃንሆይ፣ መንግሥቱ፣ ወይስ የኛው መለስ፣
ስቃይሽን ያበዛው የማን ነው ግብረ-መልስ፤
ማን ነው የረገመሽ ያሳነሰሽ ከዓለም፣
ታሪክሽን ያጠፋ ጣዕርሽን የሚወድ ለሞትሽ የሚቆም?
ሙሉውን አስነብበኝ ...ምኒሊክ ኃይለማርያም
ባንተም - በኔም ስር ያለው
ከደምህ ውስጥ ሚተነው
በደሜ ውስጥ ሚሰርጸው
ያ ትኩሳት
አቢይ አፈወርቅ
አንዳንድ ነገሮች፣
. . . ዕጹብ ድንቅ ናቸው፦
እንደ ንጋት ጸሀይ፣ መንፈስ የሚያሞቁ፤
እንደ አመሻሽ ጀምበር፣ ውበት የሚያፈልቁ፤
የልብ የሚያደርሱ፣ ለነፍስ የቀረቡ፤
ከኮተኮቷቸው፣ ሁሌም የሚያብቡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሣልህ ኦምራን
ዓባይ አመል አለህ ባልክበት አትቆምም
ህዳሴውን ሰምተህ መኩራትህ አይቀርም
የላይ የታች ብለው ሰዎች ቢፋተጉ
አንተ ግድ አይሰጥህ በጦር ቢፋለጉ
ከላይ ጣና መልካህ መፍሰስህ አይቀሬ
ማስገበሩም አይተው የታጠቀው ሡሬ
ሙሉውን አስነብበኝ ...
አበራ ለማ
(ግጥሙን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)
ቀብር ውጡ ወዳጆቼ - ጌታ ብዕር አረፈ
ደራሲው ሰው ሆነ - ፈጣሪነቱን ተገፈፈ፤
በመጋኛ ተቦትልኮ - በዘር ሀረግ ተጠርንፎ
ጌታ ብዕር ተሻረ - ካባ ማዕረጉን ተገፎ
የት ይደርሳል ያልነው ጎበዝ - ተስፋ ያልነው ሽል ጨንግፎ፤