የኤደን ስጦታ (አንዱዓለም በቀለ)
አንዱዓለም በቀለ (ከስዊስ)
ግጥሙን በድምፅ ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!
ግሪኮች ናይሎስ ብለው ቢሰይሙህ፣
አኒል አኒል ... ብሎ ዐረብ ቢያሞካሽህ፣
ኢታሩ "ታላቅ ወንዝ" ... ሃፒ ሃፒ አሉህ፣
ደስታ ቢያገኙብህ ...
ጥንት ግብጻዊያን ... ሕይወት ቢዘሩብህ፤
በሰላሳ ስሞች ... ቢጠሩ ቢያጅቡህ፣
ዓባይ የኛን ዓባይ ... እኛ መች አጣንህ፤
ከላይ ከከፍታ ... ቁልቁል ተወርውረህ፣
ከአለት ተጋጭተህ ... ጢስ ሆነህ ተነስተህ፣
በፏፏቴህ ዜማ ... ልዩ ድምፅ አውጥተህ፣
ንገራቸው እስቲ ... ከረቂቅ ሚስጥርህ። ሙሉውን አስነብበኝ ...



