የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፳፫

ፈረደበት!
ቀሚስ ባይባልም አድርገሻል ቀሚስ
ጭፈራም ባይባል ተነስተሻል ለዳንስ
ዓይነ ግቡ ኾኖ ይታያል ቁመናሽ
ዓይቶ የማያልፈው ፈረደበት ያማሽ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ቀሚስ ባይባልም አድርገሻል ቀሚስ
ጭፈራም ባይባል ተነስተሻል ለዳንስ
ዓይነ ግቡ ኾኖ ይታያል ቁመናሽ
ዓይቶ የማያልፈው ፈረደበት ያማሽ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሐሳብና ስሜት አድርገው ሩጫ
ሐሳብ አሸንፎ ተቀበለ ዋንጫ
እንደዚሁ ሁሉ ሐሳብ የሌለው ሰው
ለጊዜው ቢሮጥም ሽንፈቱ ቅርብ ነው
ሙሉውን አስነብበኝ ...ምን ዐይነት በሽታ መጣ በዚህ ዓመት
ቻይን አሜሪካ እግዜሩም ታሙበት
እግዜሩን እናውጣው የእኛ ነው ጥፋቱ
ጨክኖ አይጨክንም እሱ በፍጥረቱ
ሙሉውን አስነብበኝ ...በጣም ያሳስባል የአዳንድ ሰው ጉዳይ
ማበድ ጤንነቱ እንዴት ነው የሚለይ
እብድ ነው አይባል ደኅና ልብስ ለብሷል
ግን ደግሞ ሚሠራው ካበደው ይብሳል
ሙሉውን አስነብበኝ ...ኖርንበት እያልን እሱ እየኖረብን
አንድ አገር ብቻውን ሁለት ኾነብን
እልም ብሎ ጠፍቶ ያ ሁሉ በረዶ
ያደረ ይመስላል ሌላ አገር ተወልዶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...