ከቅኝቱ ወጣ (ሶምራን)
ሶምራን
ከ’ንግዲህ አልዘፍንም ዘፈኑም አስጠላኝ
ግጥምና ቅኝቱ ደስታ መቼ ሰጠኝ
ዘር እየለያየ ማዘመር ሲመጣ
ሕመሜ ስቃዬ ከቅኝቱ ወጣ
ኢሬቻን አክብሬ ስቄም አልገባሁ
ደመራን አከብሬ ስቄም አልገባሁ
አረፋን አክብሬ ስቄም አልገባሁ
ወንድሜ በወንድም ተረግጦ እያየሁ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሶምራን
ከ’ንግዲህ አልዘፍንም ዘፈኑም አስጠላኝ
ግጥምና ቅኝቱ ደስታ መቼ ሰጠኝ
ዘር እየለያየ ማዘመር ሲመጣ
ሕመሜ ስቃዬ ከቅኝቱ ወጣ
ኢሬቻን አክብሬ ስቄም አልገባሁ
ደመራን አከብሬ ስቄም አልገባሁ
አረፋን አክብሬ ስቄም አልገባሁ
ወንድሜ በወንድም ተረግጦ እያየሁ
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ክንፈሚካኤል ገረሱ
የመይሳው ትልሞች የዮሐንስ ግርፎች፣
የአሉላ የባልቻ የገብርዬ እንቡጦች፣
የምዬ ምኒልክ የጣይቱ ደቦል የጣይቱ አንበሶች።
የአብዲሳ አጋ የሞገስ አስገዶም የዑመር ሰመተር፣
የገረሱ ዱኪ የጦና ጎበና የጅማ አባ ጅፋር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ክንፉ አሰፋ
"ዋሸሁ እንዴ?" (ነን ሶቤ) ሲል ይጠይቃል፣ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ። ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው ለታዳሚው ሕዝብ አይደለም። በአስር ሺዎች የታደሙበት የኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ ከታዳሚው ፊት-ለፊት ለተቀመጡት ለእነ አባዱላ ገመዳ፣ ወይንም ደግሞ ለእነ ለማ መገርሳ ይመስላል። ከፍ ሲል ደግሞ ኮንሰርቱን በቀጥታ ሥርጭት እየተከታተሉ ላሉት የአድዋ ባለ ግዜዎች የቀረበ ጥያቄ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ዓላማና ግብን አሳልጦ አስማምቶ፣
በሥራ በምግባር ስብዕናን ገንብቶ።
በታሪክ ማሕደር ውጤት አስከትቦ፣
ዝናን ተጎናጽፎ ለምልሞና አብቦ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
አተኩሮ ላያት ውስጧን አብጠርጥሮ፣
በንቁ ሕሊና በሰከነ አእምሮ።
ላስተዋላት ቀርቦ ባሕርይዋ ለገባው፣
ደስታ ሰቆቃዋን ባደብ ላሳለፈው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...