ነፃነት ዘገዬ

ከጥቂት ሣምንታት በፊት ዶ/ር እሌኒ ስለምትባል ወጣት ኢትዮጵያዊ ምሁር ሲያቀብጠኝ በእንግሊዝ አፍ ጽፌ በላክሁት ጦማር ሳቢያ በደረሰብኝ የሞራል ውድቀት ላለፉት ብዙ ጊዜያት አንገቴን ደፍቼ ምንም ሳልል ቆይቻለሁ። አሁን ግን ”እስከመቼ ኩርፊያ?” ብዬ ተደፋፈርኩና ብዕሬን አነሳሁ። የሚገርመው የት ጠፋ ብሎ አንድም ሰው አልጠየቀኝም። እንዴህ ነን እንዴ ለካ? ትዝብት ነው ትርፉ!

 

የጠቀስኩላችሁን ጽሑፍ ልኩ በድረ ገፆች መውጣቱን በጉጉት ስጠባበቅ ከአንዱ በስተቀር በሌሎቹ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። አቡጊዳ ድረ ገፅ አንጀቴ ውስጥ ገብቶ የተጎዘጎዘው ያኔ ነበር። በችግርህ ጊዜ የደረሰልህ ሰው እውነተኛ ወዳጅህ ነው የሚባለው ታዲያ ለዚህ አይደል? በዚያ የድረ ገፆች ”አድማ” ዙሪያ በወቅቱ ልጫጭር አሰብኩና ኩርፊያየ በረድ እስኪል ልቆይ ብዬ በይደር አዘገየሁት። ሁኔታው ግን ሆድ ሆዴን እየበላውና አካሄዳችን እንዲህ ከሆነ ”መዛለቂያችን እንዴት ሊሆን ይሆን?” በሚል እያሰላሰልኩ ነበር ክራሞቴ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ