ሜኑው በእጃችን ነውና ከእንግዲህ አንፈራም
አቤ ቶክቻው (አውራምባ ታይምስ)
እኔ የምለው ቢራ ለካ መሰረታዊ ሸቀጣ ሸቀጥ ውስጥ የሚመደብ ነበርነና... አንድ ወዳጄ ምን እንዳለኝ ሰምተዋል? "እኛን ለማስከር ካልሆነ በስተቀር ቢራ መሰረታዊ ነገር ነውን?" ብሎ ጠይቆኝ ነበር። እኔም ቢወደድ አከሰሩን ቢረክስ አሰከሩን የመባሉ ነገር እየደነቀኝ ዝም ብል ሌላው አዋቂ ነኝ ባይ "ድሃ ድህነቱን ይረሳ ዘንድ ይጠጣ ይስከርም.. እንዲል መጽሀፉ እንኳንም ቀነሰልን" ሲል ወሳኔውን ካሞካሸ በኋላ "በነካ እጃችሁ ጫትንም ብትቀንሱልን እና አንደናችንን በተሟላ ሱስ ውስጥ ብታኖሩን መልካም ነበር" አለኝና አረፈው።
በነገራችን ላይ ይህ የዋጋ ዝርዝር በፎቶ ኮፒ ተባዝቶ በመንገድ ላይ እየተቸበቸበ ይገኛል። ታዲያልዎ በርካቶች እሱን ከመንገድ ላይ እየገዙ በየካፌውና በየ ቢራ ቤቱ ሲገቡ "ከእንግዲህ ሜኑው በእጃችን ነውና አንፈራም" በሚል ልዩ መፈክኢር ታጅበው ነበር አሉ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)



