ይድረስ ለአንድ የሀገሬ ወታደር!

ከአቢይ አፈወርቅ

“ቅዱስ ማለት ራሱን ንጹህ ለማድረግ ሙከራውን የማያቋርጥ ሀጢያተኛ ነው ይላሉ። ምናልባትም የህይወቱን 3/4ኛ ጊዜ ያሳለፈው በተንኮል ይሆናል። ይሁንና ቀሪውን የእድሜውን ሩብ በቅዱስ ተግባር በማሳለፉ ስሙ ሲወደስ ይኖራል።” ይህን ያሉት ኔልሰን ማንዴላ ናቸው። በኛ ዘመን ሰሌዳ ህዳር 30 ቀን 1972 ዓ.ም ከእስር ቤት ሆነው ለቀድሞዋ ባለቤታቸው ለዊኒ ማንዴላ ከላኩላት ደብዳቤ ላይ የተነቀሰ አባባል ነው። “አንዴ ሌባ - ሁሌም ሌባ” ከሚለው ጭፍን ድምዳሜ ርቆ ለክፉዎች እንኳ በህይወት እስካሉ ድረስ በጎ የመሆን ጀምበር እንደማትጠልቅባቸው የሚያሳይ ይመስለኛል።

 

ይህንን መልእክት በመግቢያዬ ማስቀደሜ በተለይ ላንተ የመከላከያ ሰራዊቱ አባል ለሆንከው ለአገሬ ዜጋ ለመጻፍ ያሰብኩትን ሀሳብ ጠቋሚ ይሆናል የሚል እምነት ስላለኝ ነው። ወታደሩ ወንድሜ ሆይ፦ ከዚህ በኋላ አንተን የወያኔ ወታደር ብዬ ልጠራህ አልፈልግም። ለማንም አገዛዝ ባሪያ ያልሆነ፤ ለህዝብና ለህገ መንግስቱ ብቻ የቆመ፤ ማስተዋል የሚችል የ’አገሩ ወታደር’ ለመሆን የማትችልበት ምክንያት አልታይህ ስለሚለኝ። የኢትዮጵያን እድገት የሚመኝ፣ የህዝቧ ህመም የሚያመው፣ ማሰብና ማመዛዘን የሚችል ሀገር ጠባቂ ትሆንልኝ ዘንድም በጽኑ ስለምመኝ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ