አድርባይነታችን ብዙ እያስከፈለን ነው (ቀመሩ ደስአለኝ)
ቀመሩ ደስአለኝ
ኢትዮጵያ ውድ ሀገራችን በወያኔ ማፍያ ቡድን ተወራ፣ ብሔራዊ አንድነቷ፣ አሃዳዊ ሉዓላዊነቷ፣ ታሪካዊ ክብሯ ተደፍሮና ተዋርዶ፣ ሀገር ተቆርሳ ሀብቷ እየተዘረፈና እየተበዘበዘ፣ ለም መሬት እየተሸጠ፣ ህዝቧ ተረግጦ በጠብመንጃ ኃይል መብቱን ተነፍጐ፣ ፍዳውን ሲያይ እነሆ ሃያ ዓመት ሆነው።
እንደሚታወቀው ግን የኢትዮጵያ ህዝብ በነፃነት የኖረ፣ ነፃነት አፍቃሪ፣ ለነፃነቱ ፍፁም ታጋይ፣ የማይደፈር፣ አትንኩኝ ባይ፣ መብቱን አፍቃሪ፣ ደፋርና ጀግና ሀገሩን ከውጭ ወራሪ ኃይሎችና ከውስጥ አዋኪዎች ተከላክሎ፣ ጠብቆና አስከብሮ በብሔራዊ አንድነቱ ታፍሮና ኰርቶ በፍቅር የኖረ ህዝብ ለመሆኑ በዓለም ሕብረተሰብ ፊት በእጅጉ ያስመሰከረው ሐቀኛ ታሪኩ ነው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



