ሰውለሰው (ግንቦት 2003 ዓ.ም) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

አቶ መለስ ዜናዊ ”የብልህነቱ” ጥግ አማራንና ኦሮሞን መከፋፈሉ ነው ይባልለታል። ይህ እንዴት ብልህ ሊያሰኝ እንደሚችል አቶ መለስ ዜናዊ ብቻ ያውቃል። እነዚህ ሁለቱ ትላልቅ ብሔረሰቦች በጠላትነት ተፋርጀው እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባይገቡለትም ተባብረው እንዳይቆሙ ለማድረግ በብርቱ ሠርቷል። አቶ መለስ ግድ የለውም፤ ወደ ጎንደር ጎራ ካለ ”ኦሮሞ ሊበላህ እየመጣ ነው” ብሎ በአደባባይ ለመናገር በሰማይ ያለውን እግዜርን አይፈራም። እግር ጥሎት ወደ ወለጋ ብቅ ካለ ደግሞ ”ነፍጠኛ አማራ ሊያጠፋህ እየመጣ ነውና ተጠንቀቅ!” ማለቱን አይረሳውም። እንዲህ በሰው ልጆች መካከል ጥርጣሬንና አለመተማመንን ሲዘራ የሚኖርን ሰው አጃቢዎቹ በምን መለኪያ ”ብልሁ” መሪ እያለ እንደሚያሞካሹት ስናስብ እንገረማለን።

 

እንዲሁም ወደ ትግራይ በሄደ ግዜ ”አንተ እኮ ወርቅ ህዝብ ነህ! እንኳንም ካንተ ወርቅ ከሆንከው ህዝብ ተወለድኩ!” ካለ በኋላ ”አማራና ኦሮሞ ግን ደርጎች ስለሆኑ ከነዚህ ጠላቶችህ እጅ ከህወሓት/ከእኔ በቀር የሚያድንህ የለም” ብሎ መስበኩን አይተውም። እንዲህ የሚያደርገው ግን የትግራይን ህዝብ ስለሚወድ አይደለም። የትግራይን ህዝብ አብሮ ከኖረው ህዝብ ገንጥሎ የግል ንብረትና ዋሻው አድርጎ ሁሉንም ቅጥቅጥ አድርጎ እስከ ልጅ ልጆቹ መግዛት ስለሚፈልግ ነው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!