ቅኝት በመስፍን ማሞ (ክፍል ሁለት)  
 
አንባቢ ሆይ በእንደኛው ክፍል የፊታውራሪ ተክለሃዋሪያት ኦቶባዮግራፊ ቅንታችን ከሳያደብር የተነሳው ታዳጊ በእንደምን ያለ ሁኔታ አዲስ አበባን ረግጦ፤ ሀረር አድጎ፤ አደዋ ዘምቶ፤ ሰነባብቶም ውቅያኖስ አቋርጦ፤ አድማስ ዘልቆ፤ ሩሲያ እንደኖረና በትምህርት ዳብሮ፤ በአስተሳሰቡ በልጽጎ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ ተመልክተናል። ሁለተኛውንና ማሳረጊያውን ክፍል ሁለት ደግሞ እነሆኝ ብለናልና አብረን እናዝግም…
 
እንደ ቀዳማዩ ክፍል በዚህም ውስጥ የፊታውራሪ ኦቶባዮግራፊ ትርክት ይንቆረቆራል። ግና ጅረቱ ኩልል እያለ፤ እያንሳፈፈ፤ እያፈዘዘ አይወስድም። በየመሀሉ ይደፈርሳል፤ ይጨቀያል፤ መንገዱም ጠመዝማዛ፤ አዳላጭ ሰርጥና ቆንጥር ይሆናል። እና አንባቢን ይሞግታል፤ ይታገላል፤ ይፈትናል፤ አጠያይቃል… ታዲያ በዚህ ሁሉ ጉዞ ሂደት ግና ታሪኩ ደግሞ ይመስጣል፤ ያማልላል፤ ያጓጓል፤ መጨረሻው ይናፍቃል። እንዲህ የሆነበት ምክንያት ስለምን ይሆን? ምክንያቱም በዚህ ክፍል የምናገኘው ተክለሀዋሪያት የሚለይባቸው በርካታ ባህሪያት አሉትና! እናፍታታው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ