ከንጉሤ ጋማ

“ፍትህና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር አልኖርም” በሚል ምክንያት ራሱን በእሳት አቃጥሎ በገደለው ጀግናዉ መምህር የኔሰው ገብሬ ላይ የመለስ መንግሰት የከፈተዉ የስም ማጥፋት ዘመቻ የህዝብ ቀልብ አልሳበም። ክህደት፤ ዉሸትና ንቀት የአምባገነኑ መንግስት ተብዬዉ መለያ ጠባይ መሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የተሰወረ አይደለም።

 

ከዚህ አሳፋሪና አስነዋሪ ባህሪይ ጋር ከጠ/ሚር መለስ ጀምሮ እገሌ ከእገሌ ሳይል ሁለት አስርተ አመታትን ያስቆጠረ፤ እጅግ የወረደ የስርዓቱ ባለስልጣናት ገበና እንደሆነ በሚገባ ይገነዘባል።

 

ህዝብ የሚያዉቀዉ እዉነት የሆነ የአደባባይ ሚስጠር ህሊናቸዉ በማይወቅሳቸዉ የመንግስት ተንበርካኪዎች ባደባባይ ይካዳል፤ ይዋሻል። እናም እንዲህ ያሉ ግለሰቦች በየደረጃዉ፤ በየቦታዉ፤ በየስራ መደቡ በተሰገሰጉባት አገር ምን ትርጉም ያለዉ ስራ ይሰራል? ብሎ ሁሌም በየግሉ እራሱን መጠየቁ የተለመደ ነዉ። ህዝብ የመለስን መንግስት ከማመን የተቆጠበዉ ከሽግግር መንግስቱ ምስረታ ጀምሮ እንደሆነ በርካታ ነጥቦችን መጥቀስ ይቻላል። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒዲኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ