የኃየሎም አርአያ አሟሟት… እና የጀሚል ያሲን አገዳደል (የመጨረሻ ክፍል)
በዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ)
ይህ የመጨረሻው ክፍል ነው። የመጨረሻውን ክፍል ከማቅረቤ በፊት የጽሁፌን አሃድ በምስጋና ልጀምር። ሁልጊዜ በህሊናዬ የነበረውን… ነገር ግን ለመጻፍ ጊዜ አጥቼ በነበረበት ወቅት ብርታት ለሆነኝ የእውነት እና የፍቅር አምላክ ምስጋና ይጋባው። ምንም እንኳን ባላነበውም ስለጽሁፉ በሰማሁ ጊዜ… ይህንን ታሪክ ለመጻፍ ምክንያት የሆነኝን የኢትዮ ሚዲያ ባለቤት አብርሃ በላይን በንፁህ ልቤ አመሰግነዋለሁ። ይህንን ጽሁፍ በነጻ ህሊና በድረ ገጾቻችሁና በሬዲዮናቸው ላይ ላቀረቡ ጋዜጠኞች፤ እንዲሁም ጊዜያቸውን ወስደው ይህን ታሪክ በመስማትና በማንበብ (ብትቀበሉትም ባትቀበሉትም) በጨዋ ኢትዮጵያዊነት ሃሳብ የሰጡኝን በሙሉ… በጽሁፍ ምስክርነታችውን የሰጡኝንም ጭምር፤ እኔም በተራዬ እጅ በመንሳት “እግዚአብሄር ያክብርልኝ” እላለሁ።
በመጨረሻም ይህንን ታሪክ ሥጽፍ አንዳንድ የህግ ጉዳዮች ብዥታ ሲፈጥሩብኝ፤ በምክር የረዱኝን ዳኛ ወልደሚካኤልን አመሰግናለሁ። ለብዙ አመታት አብረውኝ በነጻ ጋዜጠኝነት ለሰሩ የሙያ አጋሮቼም ምስጋና ይድረሳቸው። በፎረማችን ውስጥ ሃሳብ የሰጡትን እዚያው አመስግኛለሁ። ከዚያ ውጪ ግን እንደኔው የጀሚልን ጉዳይ እየተከታተለ ያቀርብ የነበረውን የመብሩክ ጋዜጣውን ሰይፉ መኮንን… የረሳኋቸውን ነገር እያስታወሱ የነገሩኝን የማዕበሉን አክሊሉ ታደሰ፣ የሞገዱን ክንፉ አሰፋ እና የኢትኦጱን ሲሳይ አጌና ላመሰግን እወዳለሁ። አሁን ስሟን ዘነጋሁት መሰለኝ… (ሃያት?) የጀሚል እህት በውጭ እየተገናኘን፤ ከጀሚል የሚላኩትን ደብዳቤዎች ታመጣልኝ… ስለወንድሟም ሁኔታ ታስረዳኝ ነበር። የቤተሰብ ፎቶ ያለበትንም አልበም የሰጠችኝ እሷ ናት። ባለችበት ምስጋናዬ ለሷም ይድረስ። በመጨረሻም አገር ቤት ይህንን ጉዳይ ስከታተል ፍርድ ቤት እየላኩ፤ ዜናውን እንዲዘግቡ አስቸግራቸው የነበሩ ወንድሞቼን ሃብታሙና ብሩክን ነገሩ አስር አመት ቢያልፈውም አመሰግናቸዋለሁ።(ሙሉውን ጽሁፍ በፒዲኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)



