እኔ ፍቅር ነኝ በፍቅራችሁ በየትኛውም ሥፍራ እገኛለሁ አይደል መለኮታዊ ተምስሌቱና ቃሉ? በመሆኑም መዋደድ መፋቀር በምድር ፍስሃን፤ በላይ ደግሞ የነፍስ ዋጋ ሰለሚያስከፍለን ትምህርቱም፤ ፀሎቱም ፤ድርጊቱም ሁሉ ስለመዋደድ ቢሆን እጅግ በተወደደ ነበር። አለመታደል ሆኖብን እንጂ።

 

ከአያያዝ ይቀደዳል ካነጋገር ይፈረዳል እንዲሉ ፍቅራችንን፤ ውዲታችንን በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ተፈቃሬውንና አፍቃሪውን ሊበድልና ሊጎዳ ይችላል። ዛሬ እንኩዋን ልናወጋ ያሰብነው ስለጓደኛ፤ስለእናት፤ስለፍቅረኛ ፍቅር ሳይሆን ከፍተኛውን መሰዋእት ስለሚከፈልላት ሃገር ኢትዮጵያ ይሆናል። ይህችን ሃገር ሁሉም ዜጎች አንዳችን ከሌላው ሳንበላለጥ እንወዳታለን፤ ይሁን እንጂ አንዳንዶቻን የኛን ውዴታ አግዝፈን የሌሎችን ለማሳነስ እንሻለን።


ስለሆነም አላስፈላጊ ታርጋ እየለጠፍን ኢትዮጵያዊነታቸውን ጥያቄ ውስጥ እናስገባለን። የኢትዮጵያዊነት መስፈርቱ በየአደባባዩ ባንዲራ አሸርጦ ወይም አገልድሞ ድምፅን አጉልቶ በመጮህና፤ ጨዋነት የጎደላቸው ዘለፋዎችን በማዝጎድጎድ እንዳልሆነና ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ ግድ ይሆንብናል።ካልሆነልን፤ ታሬክ  እንደ እድፍ እጣቢ እዳሪ ሳትደፋን እራሳችንን ወደ ውስጥ ለማስተዋል አሁንም ጊዜው አለን። ለዚች ሃገር ክፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉ ዜጎች- ለእዩሉኝ፤ ለይስሙልኝ ወይም ጭፍን ጥላቻቸውን ለመሸፈን፤በአውሮፓና አሜሪካ መዲናዎች ተሰልፈው ፤ለTV(ቴሌቭዥን) ጠቀሜታ ህሊናቸውን ለሸቀጥ ባለማዋላቸው፤ ኢትዮጵያዊነታቸውን ጥያቄ ውስጥ ያስገቡ የጎዳና ቀረርቶችን በማስተዋላችን ጨዋነታችንን እንደከንቱነት ፣ ትህትናችንን እንደሞኝነት፣ አክብሮታችን እንደፍርሃት ፤ እየተወሰደ አንዳንድ ታሪካዊ ግንዛቤ የጎደላቸው ፤መሰረተአልባ ድርጊቶች ሲፈፀሙ ከዛሬ ነገ ይታረማሉ ይወገዳሉ ብለን በትግስት ጠብቀን ነበር። በተቃራኒው በስፋት ስለቀጠሉ ለማህበረሰቡ ደህንነትና ሰላም ሲባል የእርምት መልክታችን ይድረሳችሁ ።


፩ኛ፦ ማንኛውም የእምነት ሥፍራ ምዕመናን ከፈጣሪአቸው ጋር የሚገናኙበት፤ ለራሳቸውና ለሌላው ሰላም፤ መረጋጋት የሚለምኑበት የሚመኙበት ሁኖ ሳለ፤ መሰረቱን የሳተ፤ የባንዲራ ምንነት ግንዛቤ በጎደለው ወይም በተሳናቸው ቡድንና ግለሰቦች፤ ኢትዮዽያን የማይወክሉ ባንዲራዎች እየተሰቀሉ ለችግር የሚገፋፉ
አትኩሮቶችን እየሳቡ ነው። ፪ኛ ባህላዊ ሃገራዊና እምነታዊ በአላት በአንድነት ስናከብር ለምሳሌ- ልደት፣አዲስ ዓመት፣ ኢደል መውሊድ፤ አረፋ፣የነጻነት በአል፣የአድዋ- ድል መታሰቢያ፣በሰሜን አሜሪካ ኢትዮዽያ የኳስ ጨዋታ…..ወዘተ ኢትዮጵያውያን በጋራ የምናከብረውና የምንሳተፍበት ስለሆነ የወቅቱን የሃገሪቱ ባንዴራ ልንጠቀም ሲገባን አለተጤነም።


፫ኛ ፥- እያንዳንዱ ቤተሰብ ወይም ወላጅ ልጆቹን አስተምሮ የሆነ ደረጃ ሲደርሱለት ለሰርግና ለመሳሰሉት ደስታውን ከማህበረ ሰቡ ጋር ለመጋራት ባዘጋ ው ድግስ ሽንኩርት ሳይልጡ፣ ወጥ ሳይወጠውጡ፣ሊጥ ሳይለውሱና እን ራ ያልጋገሩበትን መስተንግዶ ለፖለቲካ ጠቀሜታ ለማዋል ኢትዮጵያን የማይወክል ባንዲራ
ሰቅለው ሰናይ ኢጭ አበዙት ምነው ሰላም ቢሰጡን ማለታችን አግባብ ነው ይገባናልም። በመሆኑም ባንዲራ ከምንም በላይ አብይ ክቡር ሲሆነ በቦታው በጊዜው ሊጠቀሙት ካልተቻለ አላስፈላጊ ውዝግብ ሊቀሰቅስ ስለሚችል መጠነኛ ማብራርያ ቢሰጠው ከወዲሁ ከፍራታችን ሊታደገን ይችላል የሚል እምነት አለ።
ባንዲራ፥ የአንድ ሕዝብ ወይም ሃገር ትንሽም ሆነ ትልቅ ማህበረሰብ መታወቂያ፤ ምልክቱና ብሎም ታሪኩ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ የእኔነቱ አሻራ ነው። በዚህ እኔነት ውስጥ አንድነት፣ ወንድማማችነት፣ እህታማችነትን፣ አክብሮ መከበርን፣ ልዩነትን አካቶ አብሮነትን አቆላልፎ የያዘ ትልቅ ጉዳይም ነው። በመሆኑም
ዓለም አቀፍና አካባቢያዊ ዕውቅና ይሰጠዋል፡ይህ እውቅና ያገኘው ባንዲራ አንድና ብቸኛም ይሆናል።

ማንኛውም ሃገር በተመሳሳይ ጊዜ ከአንድ ባንዲራ በላይ ሊጠቀም አይችልም አይገባውምም። በሆነ ምርጫና ፍላጎት የባንዲራው ባለቤት የሆነው ሃገር ሲቀይረው ተለዋጩ ዕውቅና ያገኛል ብቸኛም ይሆናል።ልዩ በሆነ አጋጣሚ በአንድ ሃገር ሁለት ባንዲራ ሊኖር ይችላል። ማለትም ቅኝ አድራጊ ወይም ወራሪ ሃይላት ተወራሪውን ግዛት በሙሉ መቆጣጠር ሳይቻለው ሲቀርና፤ ሃገሬን አላስነካም ባዩ ሲፋለሙ የሚከስት ነው።የአምስት አመቱ የጣሊያን ወረራና የኢህአዲግ ከሕግ በላይ ሁኖ በባድሜ የተከለው ባንዲራ የቅርብና የሩቅ ትውስታዎቻችን ናቸው። ባንዲራ የአንድ ነፃ ሃገር መታወቂያ ምልክት ሲሆን ኢትዮጵያ በነፃነት የኖረች በመሆኗ አፍሪካ ውስጥ ቀደምትና አንጋፋ ባንዲራ ባለቤት ነች።የሰንደቅ ዓላማው ቀለም ፍቺና ትርጉም መለስተኛ ልዩነት ቢኖረውም ከሌሎች ጥቁር አፍሪካ ሃገሮች ጋር አንድነት ያለው ሲሆን አቀማመጥና አደራደራቸውን በመለዋወጥ የሚገለገሉባቸው አራት ቀለማት ጥቁር፤ ቢጫ፤ ቀይ፤ አረንጓዴ ስሆኑ በተናጠል ሲፈቱ፦ ጥቁር-የሃጉሪቱን ሕዝብ ይወክላል የሰው ዘር መ መርያ፤ ክብር፤ ወግ ባህልና ታሪክ ያለው ነዋሪና ባለቤት መሆኑን ይገልጻል። አረንጓዲ፦እናት ሃገር ድንግል መሬት፤ ክምቹ ሃብት፤ ልምላሜን ውበትን ያሳያል። ቀዩ፦  ግንነት፤ ተከላካይነት፤ የሚከፈል ውድ መሰዋእትነት ሲሆን ቢጫ፦የነዋሪውን ሕዝብ ነጻነት ከነክብሩ የሃጉሪቱን ሃብትና መሬት የተከፈለው ተከፍሎ ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ የሚጫር የእድገት የብልጻጌ ተሰፋና ምኞት ነው።በኢትዮዽያ ባንዲራ መቼ ተ መረ ምን ያህል ጊዜ ተለዋወጠ ቅርፁና ቀለሙስ ምን ይመስል ነበር? የዛጒኤ ሥርወ መንግሥት የክርስቶስ ምስል ያልበት አርማ ይጠቀሙ እንደነበረና፤ አፄ ዮሐንስ አራተኛም ሁለት ቀይ ቀለማት በቢጫ ቀለም የተከፈለ አርማ ይጠቀሙ እንደነበር ይነገራል።

 

በመሳፍንቱ ዘመን ይጠቀሙበት የነበረው ባንዲራ እንደ አሁኑ አረንጋዲ ብጫ ቀይ ሳይሆን ቀይ ብጫ አረንጋ,ዲ ሁኖ መሰረቱን ለማያያዝ ባንድነት ተሰፍቶ በየቀለማቱ የተተለተለ ከጫፉ ሾጠጥ ከስሩ ሰፋ ያለ ሦስት ማዕዘን ቅርፅ ነበረው። ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘው የኢትዮጵያ ባንዲራ በ1897 ከአድዋ ድል አንድ አመት በኋላ የአፍሪካ የነፃንት ፈር ቀዳጅ የህብረታቸው አርማ ሁኖ ተውለበለበ። ይህ ባንዲራ አረንጋ,ዴ ብጫ ቀይ ቀለማት አግድም ተሰፍተው መሃሉ ዘውድ የደፋና ሰንደቁን በመስቀል ዘንግ የተሸከመ አንበሳ ወይም የይሁዳ አንበሳ ተብሎ የሚታወቀው ምሰል ይገኝበታል። የባንዲራው ቀለማት የየራሳቸው ትርጉምና ውክልና አላቸው። አረንጓዴ፦ ሃገር፤ልምላሜ፤ሃብትን ቢጫ፦ሰላም፤መረጋጋት በሃገሪቱ ብሔርና ብሔረሰቦችና እንዲሁም የተለያዩ የሃይማኖት ክፍሎች መቻቻልና መግባባትን ሲያስረግጥ ቀዩ ደግሞ ለመላው የጥቁር ዘር ነፃነት፤ሃገሪቱን ከወረራ ተከላክሎ ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ የፈሰሰውን ደም ያመለክታል። የዓጼው መንግሥት እስተወገደበት 1974 ዓም ድረስ የሃገሪቱ ባንዲራ በመሆን አገልግሎቱ አበቃ።

 

ይህን ባንዲራ ከአርማው ይዘት እንደምንረዳው የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎትና ምንነት ሳይሆን እንደ ዘመኑ አስተሳሰብ የአፄዎችን ምንነትና እምነት የሚገለፅበት ነበር።ይሁን እንጂ ሕዝቡ እኔንና እምነቴን አይወክልም ብሎ ሁለተኛ ወይም ተለዋጭ ባንዲራ ሳያሻው ላንድነቱ አብላጫ በመስጠት ሰንደቁን አክብሮ የፈለገበት ሊደርስ እንደሚችል በማመን ተቀብሎት ኑሯል።በአፂ ኃይለ ሥላሴ ዘመን መንግሥታዊ ተቋማትና ትምህርት ቤት ልሙጡ አረንጓዲ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ይሰቀል ነበር። ይህ ማለት ሃገሪቱ ባለሁለት ባንዲራ ስለሆነች ሳይሆን የተለያዩ እምነት አባላት በተቋማቱ ተሳታፊዎች ስለሆኑ የተደረገ የፖለቲካ እግምት ነበር። የወታደሩ መንግሥት በ17 አመት የግዛት ዘመኑ ሦስት ባንዲራዎች ሲጠቀም የመ መርያው የአፄውን ባንዲራ ከአንበሳው ላይ ዘውዱን አውርዶ መስቀሉን በጦር ቀይሮ ንጉሡን በአዋጅ እስካወረደበት
September 11, 1974 –November 1974 ሁለተኛው ሞፈርና ቀንበር ክብ የማሽን ክርክር በወይራ ቅጠል ታቅፎ ከ1975-1987 አገለገለ። ሦስተኛው መደቡንና መሰረቱን ሳይለቅ መ ሉ ኮከብ የአክሱም  ውልትና የማሽን ክርክር ተቀምጦበት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ባንዲራ ሁኖ 1987-1991 አገልግሎ የወታደሩ መንግሥት ጋር አበቃ ።

 

1991-1996 አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት አግድም ተሰፍተው ምንም አይነት ምልክት ወይም አርማ ሳይኖረው የኢ ዲግ መራሹ የሽግግር መንግሥት ባንዲራ በመሆን ይታወቃል ይህም ማለት በአሁኑ ጊዜ ሕጋዊ እውቅናና ተቀባይነት ሳይኖረው በየዋህነትና ሆን ተብሎ በየቦታው የሚሰቀለው ነው። ከ1996 እስከ አሁን ድረስ ሃገሪቱ የምትጠቀምበት ሦሰቱ ቀለማት እንደነበሩ ሆነው መ ሉ ሰማያዊ ክብ፣ ኮከብና የብር ን ጨረር ያካተተ ሲሆን እያንዳንዱ ቀለምና ምልክቶች የየራሳቸው ትርጉምና ውክልና አላቸው። ክቡ ስማያዊ፦ ሰላምን፤ ኮከቡ፦ብዙነታችንን፡የፀሐይጨረር፦ተስፋ፡ምኞትን፡አረንጓዴው፦መሬት
ወይምሃገርን፤ቢጫው፦መረጋጋት፤ቀዩ፦ጥንካሬ ይገልፃሉ። በአሁኑ ጊዜ ሕጋዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው የ ገሪቱ ባንዲረ ይህ ብቻ ነው።


ሕጋዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅና አለው ሲባል የሃገሪቱ ሕዝብ በወኪሎቹ ተወስኖ በሸንጎ ያፀደቀው በሃገሪቱሕገ ደንብ ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው የሕዘቡ የመሰዋዕትነት ውጢት፣የበደሉ ካሳ፣የትዝታው ማስታገሻ፣የአንድነቱ መሰረት፣የእኩልነቱ ዋልታ በመሆኑ እንደ ዓይን ብሌኑ ይጠብቀዋል እንደአስፈላጊነቱም ይከላከለዋል። ስለሆነም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በሕዝቡ ምርጫውና በውሳኔው ላይ የምንወስደው ተፄራሪ ድርጊት ቁስሉን ማስፋትና ብሶተ ትዝታውን መቀስቀስና ሃገሪቱን ወደባሰ ቀውስ ሊከት ስለሚችል ከአሁኑ እንዲታሰብበት። ብዙነታችን የአንድነታችን መሰረት፤ውበትና ጥንካሬአችን ስለሆነ በአግባቡ ካልተያዘ ሊያስከትል የሚችለው መዘዝ ብዙ የሚጠይቅ በመሆኑ እሳትን በሳት እንዳይሆን በመስጋት፤ እንጂ ነው ሳይቃጠል በቅጠል የተባለው።(« ልጆቻችን ለምንድን ነው ኢትዮጵያ ብቻ ሁለት ባንዲራ ያላት ብልው ቢጠይቁን ሁለት ሃገር ስለሆነች ወይም የስደት ባንዲራ ነው እንደማንል እንኳን መጠርጠር ማሰብም አይቻልም») እናስ ምን ይሆን መልሳችን?።


ቸር ይገጠመን!!!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ