‘ፍርሀቴን አቃጠልኩት’ ለየኔሰው ገብሬ የተጻፈ (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
እነሆ አርባኛው ቀንህ በካህናት ፀሎት ተነሳ። በመላው ዓለም የተበተኑ ወገኖችህም ስምህን ከፍ አድርገው አወደሱ። የጠበሰህ እሳት ከሚያሰማህ ስቃይና ሕመም ይልቅ ትግራይ በቀል ጠላቶችህ እንዲሁም ሆዳምና አድርባዮች የሚያደርሱብን በደልና ግፍ ይበልጥ እንዳሳመመህ ነገርካቸው። ከነፃነት እጦት ሞት እንደሚሻል መራር ሞት ሞተህም አሳየሃቸው። የዘርን አጥር ሰብረህ፣ የጎጥ ፖለቲካን ኮንነህ ኢትዮጵያውያን እንደ ሕዝብ ነፃነትን እንደሚሹ አስተምረህ አለፍክ። ታጋዮች በስምህ ተማምለው ተነሱ። ገጣሚዎች ስምህን ከፍ እያደረጉ ተቀኙ።
”እንደ ትንግርት ራዕይ የመለኮት ጸጋ፣
ሰብስበህ አሰርከው አበሻን ባንድጋ።
ቆራጥ መስዋዕትነት ቢሹት የማይገኝ፣
ሞትህ ያገር ልደት ሉሆን ነው መሰለኝ። …”
ለአንተ ሞት ምክንያት የሆኑት ወያኔን ዕድሜ የሚሰጡ ከየመንደሩ የወጡ ሆድ አደሮች መሆናቸውን አስብ ዘንድ ብርታት ሆንከኝ። ባንተ ሞት የተሳለቁ እኒህ ትራፊ ለቃሚዎች እኔም ዘንድ አሉ። ለኔም ሞት እንደማይመለሱ አውቃለሁ። ቀን ከሌት የስለላ ዶሴ እያመላለሱ የራሳቸውን የውርደት ሞት የሚጠብቁ ብዙ ናቸው። ውስጣቸው ባዶ የሆነ፣ በፍርሀት የተሸማቀቁና ጊዜያዊ ጥቅም የደለላቸው ወይም ራሳቸውን ለማዳን በሌላው ሕይወት ገበጣ የሚጫወቱ በያገሩ በየመንደሩ አሉ። እኒህ አሾክሻኪዎችንና እበላ ባዮችን ግን አጥብቄ እፈራ ነበር። ለመኖር ሲሉ ወይም ለመታመን ሲሉ ብዙ መዘዝ ያመጣሉ እያልኩም አስብ ነበር። ቤተሰቦቼና የቅርብ ወዳጆቼም በኔ ምክንያት ሊደርስባቸው የሚችለውን ሳስብ ‘ጎመን በጤና’ እያልኩኝ ‘ባገር የመጣ ነውና ምን ይደረጋል’ በሚል ፈሊጥ ፍርሀቴን ሳባብለው ነበር የኖርኩት። ... ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!



