በዴሞክራሲያዊ ሽግገር ወቅት የሕግ የበላይነት በኢትዮጵያ
ፕ/ሮ ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
የሕግ የበላይነት፤ በሰው ሕግ፤ በሕገቢስነት
ባለፉት፡ዓመታት ሳነሳቸው የነበሩት ርእሶች ሁሉ በአንድ መሰረታዊ በሆነ እምነት ላይ የተመሰረቱ ነበሩ፤ ይሄውም የሕግ የበላይነት ነው። የሕግ የበላይነት ምንድን ነው? በኢትዮጵያስ ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአትሽግግር ወቅት እንዴት ሊገነባ ይችላል?
‹‹የሕግ የበላይነት›› የሚለው ቃል ወይም አባባል፤ በለዘበ አለያም በተደጋጋሚ፤በምሁራን፤በሕግ ባለሙያዎች በብዛት ለፖለቲካዊ ውይይት መጠቀሚያነት ውሏል። የፈላጭ ቆራጮችም አንደበት ሳይቀር ለመማያ፤መገዘቻ ጥቅም ላይ ያውሉታል። በኦክቶበር2011 በኖርዌይ ለሚታተመው አፍተንፖስተን ለሚባለው ትልቁ ጋዜጣ መለስ ዜናዊ የሕግ የበላይነትን በተመለከተሲናገር“እኛ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ የሰብአዊ መብትን መከበርንም በአግባቡ እየገነባን ነው። የዴሞክራሲ መብቶች የተከበሩበት ሃገር ይህ የእኛ ሃገርነው።” (ድንቄም!!!)
የሕግ የበላይነት በተለይ ለሕግ ባለሙያዎች (ጠበቆች) የሕገንግሥታዊ የበላይነትን የሚያረጋግጥ ነው። የፖለቲካ ሊቃውንትም ሃረጉን የኢንስቲትዩሽን ስርአትን በሃገር ውስጥ ለማስረዳትና ባለስልጣናትም ሥልጣናቸውን አላግባብ እንዳይጠቀሙበት ለመከላከያነት ያውሉታል።ሕጉ በአግባቡ እንዲተረጎምና ሕዝቡም ተጠቃሚነት እንዳይጓደልበት መከላከያ ይሆንና መሰረታዊ የሆኑት ሰብአዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲጠበቁና በተግባር ላይ እንዲውሉ ዋስትና ነው።
በኢንቬስትመንት ሂደት ላይ ውል እንዲከበር፤ የገበያው ልውውጥ የሰመረ እንዲሆን፤የተረጋጋና ሰላማዊ አካባቢ ለመፍጠር፤ የህግ የበላይነትና መከበሩ አስፈላጊነታቸው ለኤኮኖሚስቶችም ዋነኛ ጉዳይ እየሆነ ነው። የሕግ የበላይነት በሌለበት ኢንቬስትመንትም ሆነ ልማት ተግባራዊነታቸው ዋስትና ስለማይኖረው ፈላጭቆራጮች እንዳሻቸው በማፍረስና ከሕግ በላይ በመሆን ስለሚንዱት የሕግ የበላይነትወሳኝነቱ የማያጠያይቅ ነው። የሕግ የበላይነት በተከበረበት ቦታ፤መልካም አስተዳደር፤ (ተጠያቂነት፤ ግልጽነት፤ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫዎችና ሌሎችም…) ይተገበራሉና የሃገሮችም ኤኮኖሚ ያድጋል። የዓለም ባንክና ኢንተርናሽናል ሞኒታሪ ፈንድ ከ1990 ምሮ የህግ የበላይነት በአፍሪካ በትክክል በተግባር እንዲውል ከሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር በመሆን ሲወተውቱ ዓመታት ቢያሳልፉም ውጤቱ ግን ከንቱ ልፋት ሆኖባቸዋል።
የሕግ የበላይነትን በተመለከተ የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ ስርአታቸው ፈላጭ ቆራጭ አረመኔ ገዢዎች ብዙ ዝባዝንኬ፤ አርቲ ቡርቲ ሲቀበጣጥሩ ይሰማሉ። ‹‹በግለሰብ ሕግ›› ጭቆና ውስጥ ያሉ ሕዝቦች ከሕግ በላይ ሆነው በሚገዙት እኩዮች ሥልጣንን አፍነው በግል በያዙ ሰዎች የሚሰቃዩ ናቸውና ለሕዝቡ የሚያስፈልገውንና የሚበቃውን የሚወስኑለትም እነዚሁ ገዢዎች ናቸው፡፡ ጆሴፍ ስታሊን፤አዶልፍ ሂትለር፤ማኦ ዜ ዱንግ እና ሌላዎችም አድርገው ያለፉት ይህንኑ ነው። አሁንም የአፍሪካፈላጭቆራጮችየሚያደርጉት ድርጊት ይሄው ነው።
የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች እራሳቸውን ሕግ አድርገው ነው ሕዝቡን የሚረግጡት፡፡ (ቅዠት ፈጠር በሆነው የሕግ መሰል ስሪታቸውና በትእዛዝ የሚፈጽሙት) ትእዛዞቻቸውን ይሞነጭሩና፤ለወጉ አድቦልቡለው ለፈጠሩት የሎሌ ፓርላማቸው ያቀርቡና ሳይነበብ ሳይገነዘብ ማሕተም ተረግጦበት ሕግ የሚባል ስም ይሰጠውና ይደነገጋል። ይህን የግል ትዕዛዛቸውን ራሳቸውን ፖሊስ ከሳሽ፤ዳኛና አቃቤ ሕግ ሆነው ይጠቀሙበታል፡፡ ይህን የዕዝ ሕግ (ወይም ሕግ በትእዛዝ) መብት ለመጨፍለቂያነት እና እንዲሁም ተቃዋሚዎችን ለማስፈራሪያና ለማገጃ ያውሉታል። በማርች28/2006 ኮንግሬስማን ክሪስተፈር ስሚዝ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ፤የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብትና ዓለም አቀፋዊ ውክልና ሊቀመንበር፤ከመለስ ዜናዊ ጋር ባደረገው ውይይት ወቅት የዕዝን ሕግ ምንነት ለመገንዘብይቻላል።
ባለፈው ኦገስት አዲስ አበባን በጎበኙሁበት ወቅት ባለፈው ሰኔ በሚያዛቸውና አገልጋዮቹ በሆኑት ደህንነቶች ሕይወታቸው ስላለፉት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ለምን ምርመራ እንዳላካሄደ ጤቄው ነበር። ለዚህ የሰጠኝ መልስም፤ ምረመራው ቢካሄድተቃዋሚዎችን ሕይየወት ለእስራት የሚዳርግ በመሆኑbeየድጋሚ ምርጫ ስለሚካሄድም ይህንን ከማድረግ መቆጠቡን ነው የነገረኝ‹‹ በመቀጠልም ስለማንኛውም ተቃዋሚ በቂ የሃገር ክህደት ማስረጃዎች (dossier) ያሉኝ ስለሆነ ባሰኘኝ ወቅት ወደ እስር ቤትላጉራቸው እችላለሁ፤ ብሎኝ ስለነበር የመታሰራቸው ጉዳይ አስቀድሞ የታቀደና የተወሰነ አንደሆነ ግልጽ ነበር።
በ2011 ኦክቶበር መለስ ዜናዊ ኖርዌይን በጎበኘበት ወቅት፤ ሁለቱ የስዊዲሽ ግለኛ ጋዜጠኞች፤ጆሃን ፐርሰን እና ማርቲን ሽብዬ ገና ጉዳዩ በፍርድ ሂደት ላይ እያለና ውሳኔም ላይ ሳይደረስ መለስ -- ሕጉ መለስ ነውና - ያለምንም ሃፈረትና ይሉኝታ፤ የሽብር፡ወን ለኞች ናቸው ብሎ በየነባቸው። ሁለቱ ጋዜጠኞች ይላል መለስ ‹‹ሌላው ቢቀር የሽብርተኛ ቡድኖች ተላላኪ ልጆች ናቸው። ጋዜጠኞች አይደሉም። ለምንድን ነው ጋዜጠኞች ኬላ ጥሰው ከሽብርተኞች ጋር መሣርያ በታጠቁ፡ሽብርተኞች ታጅበው፤ ሽብርተኞች በዋሉበት ውጊያ ላይ በመሳተፍ ወደ ሃገርየገቡት ይህ ጋዜጠኝነትከሆነ፤ሽብርተኛነትምን እንደሆነ ማወቅ አልችልም›› እንደ፡ አባባሉ መለስ የኢትዮጵያን ሕገመንግሥት አንቀጽ 20(3) አንድ ተከሳሽ በፍርድ፡ወን ለኛነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ነው›› ከሚለው ጋር የሚተዋወቅ አይመስለኝም፡ ስለነዚሁ የስዊድን ጋዜጠኞች፤ ለሕሊና የሚዘገንን፤የአብዬንለእምዬየሆነመግለጫበፌብሪዋሪ 2012 መለስ ሰጥቶ ነበር።
መንግሥት እነዚህ ሰዎች በእስር መዋላቸውን አጭር መግለጫ እንዳወጣ…….በሚቀጥለው ቀን፤ሙግቱ ለመገናኛ ‹‹ብዙሃን ነጻነት፤ምንም የተንኮል ዓላማ የሌላቸው ንጹህ ዜጎች›› በሚል። ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ የምስክሮች ቃል፤ሳይሰማ ቀድመው ውሳኔውን የሰጡት አግባብነት የሌለው፤ማን አለብኝነተ ነው። ንጹሃን ወደ እስር ወን ለኛው መንግሥት በነጻነት። (የጫማው ልኬት ከተስማማችሁ ተጫሙት)
መለስ፤ ሰዎቹ ተጠርጥረው ገና ወደችሎት ከመቅረባቸው በፊት እራሱ በፍርደ ገምድልነት ችሎቱ ወን ለኛነታቸውን ከማረጋገጥ ውጪ አንዳች ውሳኔ እንዳያሳልፍ ከሕግበላይ እራሱን ኮፍሶ ፈረደባቸው። ይህን ያደረገው መለስዜናዊ ታዲያ እንዴትሆኖነው፤ የፍርዱ ሂደት ከማብቃቱ በፊት ሰዎችግላዊ አስተያየታቸውን በመስጠታቸው ለመውቀስ የሞራል ብቃት ያገኘው፡፡ ይገርማል ይደንቃል!
ስለ ሕግ የበላይነት ተግባራዊ ዕውቀት
ስለኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ የጭቆና አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያው ስርአት ሽግግር ምሁራንና የሕግ ባለሙያዎች እንደሚወያዩበት አይነት በሕግ የበላይነት ተግባራዊ ዕውቀት ላይ መወያየቱና መከራከሩ ማካሄድ ይቻላል ተገቢም ነው። የሕግ የበላይነትን በሥራለመተርጎም እንዲቻል ተግባራዊ ልምምድና ስልጠና በማድረግና በአሜሪካና በኢትዮጵያ ጸረ-ሽብርተኝነት ሕጎችን በመመርመር ጠቃሚ ትምህርት ሊገኝ ይቻላል።
በ2001ፕሬዜዳንት ቡሽ ከሽብርተኞች ጋር ስለሚካሄደው ጦርነት፤ ለመያዣ፤ስለእስር፤ ስለእስረኞች አያያዝ፤ ስለ ፍርዱ ሂደት፤ እና ስለተወሰኑ የሌላ ዜጋ አባላት (የጠላትተዋጊዎችለተባሉት) ስለሆኑት ተጠያቂዎች ጉዳዩን የሚመለከት የጦር ፍርድ ቤት መሰየም አንድ ወሳኝ ሕግ በፊርማቸው አጽድቀው ነበር።
በ2006 የአሜሪካን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔውንና የተቋቋሙትንም የጦርፍርድ ቤቶች ሕገ መንግስቱን ጥሰዋል በማለት ውድቅ አድርጎታል (Hamdan v. Rumsfeld) እነዚህ የሽብር ተጠርጣሪዎች የአሜሪካን መንግሥትን የሕግ፤ የጦርሕግን (የጄኔቫ ኮንቬንሽንንና የመለዮ ለባሾችን የሕግ ኮድ ጨምሮ) የወንጀል ሕግን በመዘርዘርና መሰረቱ ለጸናው ለአሜሪካው የሲቪል ነጻነት ከበሬታ በማሳየት፤ ከለላ ሊያገኙ እንደሚገባ እንደሚከተለው አትቷል። “የሽብርተኝነት ተጠርጣሪው ዕድሉከቀናው በንጹሃን ዜጎች ላይ እስከሞት የሚያደርስ አደጋ ሊጥል የሚችል አደገኛነው። ያምሆኖ ወሳኙ አካል የሕግ የበላይነትን ማክበርን መሰረት ባደረገ መልኩ በወጉ ለፍርድ በማቅረብና ፍትሕ ሳይጓደልበት ውሳኔ እንዲያገኝ ሊደረግ ተገቢነው።”
በ2004 በተመሳሳይየሽብርተኝነት ወን ል (Rasul v. Bush) ተከሳሽ የአሜሪካን ከፍተኛ ፍርድቤት በሕግ የበላይነትላይ በመመርኮዝ ፕሬዜዳንቱ የሃቢየስኮርፐስን የሕግ መመርያ እንዲያከብሩ ጠየቀ። (ሃቢየስ ኮርፐስ (habeas corpus) ለአሜሪካን ሕዝብ ከተሰጠው የሕግ የበላይነትን ማስጠበቂያ መብትና መንግሥትም የሕግ የበላይነትን ሲጥስተጠያቂነት እንዲኖረው የሚያስችለው ታላቅ ሕገ መንግሥታዊ ስነ ስርአት ነው ፍርድ ቤቱ በሽብርተኝነት ተጠርጣሪው ከጠበቃውጋር የመገናኘትና የመመካከርን፤ ሊከለከል ጨርሶ እንደማይገባው ያዛል። ይህን መብት ማጉደልም የአሜሪካንን ሕገመንግሥታዊ መብት በማስተካከያነት የተቀመጠውን 5ኛውን ሕግ መጣስነው። በሌላ አባባልም ማንኛውም ተጠርጣሪ፤ ወይም ተከሳሽ ምንም ወንጀል የፈጸመ ቢሆን፤ በአሜሪካን ሕገ መንግሥት መሰረት የሕግ የበላይነትን መሰረት ባደረገ መብቱ ተጠቃሚነቱ አይጓደልበትም።
በሌላ ጎኑ ሕግበ ትእዛዝ (ትዕዛዛዊሕግ) የመለስን ጸረሽብርተኝነት ሕግ (አዋጅ ቁጥር 652/2009) ዜጎችን፤ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞችንና ጋዜጦችን፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን መሪዎች እና በመለስ አይን ያልተስማሙትንና በጥላቻ መዝገቡ የተከተቡትን የዴሞክራሲና ሰብአዊ መበት ተሟጋቾች፤ለገዢነት መዳፉ ጡጫ ያላጎበደዱትን ለማፈኛና ለተገዢነት ለማዋል መሳርያው ሆኖታል።
በፌብሪዋሪ 2012 መ መርያ ላይ ነጻ የሆኑ የተባበሩት መንግሥታት የሰበአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች፤ (የተባበሩት መንግሥታት ልዩ መዝጋቢዎች) በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የነጻነት ጥያቄ አዲሱ የጸረ ሽብር ሕግ በባሰሁኔታ ያግደዋል በማለት ሕዝባዊ መግለጫ አውጥቷል። የተባበሩት መንግሥታት የጸረ ሽብርና የሰብአዊ መብት ልዩ መዝጋ ቢየሆነው ቤን ኤሚርሰን፤ በኢትዮጵያ የወጣው አዲሱ የጸረ ሽብር ሕግ እንዳሻ በመተርጎም ሊያደርስ የሚችለውን ችግር ለመከላከል እንዲቻል ጸረሽብርሕጉ ከሃገሪቱ የወንጀል ሕግ ጋር በማይቃረን መልኩና የዓለም አቀፉን ሰብአዊ መብት ድንጋጌ ባከበረ መልኩ መቀረጽ አለበት ሲሉተችተዋል።
ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ልዩ መዝጋቢው ፍራንክላሩ፤ ባለስልጣናት ለሚያደርሱት በደልና ሃላፊነትን መዘንጋት የሰብአዊ መብት መጣስን በተመለከተ ጋዜጠኞች በመመርመርና አጣርቶ የጉዳዩን ስረመሰረት በማውጣት ለሕዝቡ ዕውነቱን ይፋ በማድረግ በኩል ከፍተኛውን ድርሻ ይጫወታሉ።
ሙያዊ ግዴታቸውን ስለተወጡ ብቻ ሊታሰሩና ሊሰቃዩ ቀርቶ ሊጠየቁ እንኳ አይገባም ሲሉ ገምግመዋል። ማርጋሬት ሴካጋ ያየተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ልዩ መዝጋቢ እንዳለችው፤ ጋዜጠኞች፤ የኢንተርኔት የዕለት ሁኔታ አስተላላፊዎች፤ ሌሎችም የሰብአዊ መብት በበለጠ ሊከበር ይገባል ባይ ተሟጋቾች በኢትዮጵያ ላሉ ገዢዎች የነዚህ ተሟጋቾች እውነታ አልዋጥ ስለሚላቸውብ ቻጫና ሊደረግባቸው አይገባምአሉ። የሰላማዊ ሰልፍና በነጻ የመሰብሰብና ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ጉዳዮችልዩ መዝጋቢ ማይናኪያይ በተለያዩ የህዝባዊ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ገደብናጫና የፈጠረው የጸረ ሽብርተኛነት ሕጉ ነው። አብዛኛዎቹ ከሚባል በላይ ሕዝባዊ ድርጅቶች የዚህ አዋጅ ተጠቂሆነዋል፤ እንቅስቃሴያቸውም ተገቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለነዚህ ሕዝባዊ ድርጅቶች ጥበቃና ከለላሊሰ ጥግዴታው ነው። በተለይም የሰብአዊ መብትን ለማስከበር በሚንቀሳቀሱ ሕዝባዊ ድርጅቶች አኩዋያ ሲሉ አሳስበዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የፍትሕ አካላትና የጠበቆች መብትና ነጻነት ተከላካይ ልዩ መዝጋቢ የሆኑት ጋብሪኤላናውል፤ በሕግፊት ለክርክር የቀረቡ ሰዎች፤ በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት ላይ በተደነገገው መሰረት ሕጉ እስኪ ወነጅላቸውና ውሳኔውን እስኪያሳልፍባቸው ድረስ ነጻሰዎችነታቸው ሊጠበቅይገባል። የመከላከል መብታቸውንም ለመጠበቅ እንዲችሉ ከጠበቆቻቸውጋር በፍርዱ ሂደት ወቅት ያላንዳች ገደብ የመገናኘትና የመመካከር መብታቸው ሊከበርላቸው ተገቢ ነው በማለትአስረድተዋል።
የሕግ የበላይነት መንፈስ
የሕግ የበላይነት ስሜት በቀላል አባባል እንደሚከተለው ሊገለጽ ይችላል፡- ሥልጣን ለሙስና ይዳርጋል፤ ፍጹማዊ አምባገነን ሥልጣን ደሞ ለበለጠ፤ ለገነነና መረን ለለቀቀ ሙስና ይዳርጋልና የህግ የበላይነት ደሞ ይህን ስልጣን ለመቆጣጠርና ፍጹምና አምባገነንም ስልጣን ከገነነ ሙስና እንዲቆጠብ ማድረጊያው ዋና መሳርያነው። የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ ለሴኪውሪቲ ካውንስል በ 2004 ባቀረቡት ዘገባ፤ የሕግ የበላይነትን ተግባራዊነትን፤ ምንነትና መሰረታዊ ሕዝባዊና ሃገራዊ ጥቅሙን ሲያስረዱ፤ ‹‹ሁሉም ሰብአዊ ፍጡራን፤ ድርጅቶችና አባሎቻቸው፤ ሕዝባዊም ሆኑ የግል፤ መንግሥትን ራሱ ጨምሮ የሕግ ተጠያቂነታቸውን ማረጋገጫ፤ በዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ላይ የተመሰረቱና የመንግሥታት ተቀዳሚ መመርያ ሊሆን የሚገባውነው።›› ተግባራዊሲ ደረግም የሕግን የበላይነት በማረጋገጥ ለዚህም ታማኝነትን የሚጠይቅ የሕግን ደንብ የሚያስከብርና ማንም ከሕግ በላይ አለመሆኑን ማረጋገጫ፤ ለሁሉም አላንዳች መድልዎ በእኩልነት የሚያገለግል፤ የስልጣን ክፍፍልን ሚዛን የሚያስጠብቅ፤ በውሳኔ አሰጣጥም እኩልነትን የሚያሳይ፤ ከጥርጣሬ የጸዳና ግልጽነትን ያቀፈ ሊሆን ይገባል›› የዓለም ባንክም የሕግ የበላይነትን ጥቅምሲገልጽ ‹‹የሕግ የበላይነት ባለበት መንግሥታት እራሳቸውን ይቆጣጠራሉ፤ ሕዝቦችንም በሕጋዊና በእኩልነት ለሕግ የበላይነት በመገዛትና የሕብረተሰብ አባላት የሆኑትን ግለሰቦችም መብት በማክበር ያስተዳድራሉ። በሕግ የበላይነት የሚመሩ በርካታ ድርጅቶችና ኢኒስቲቱሽኖች ጭምር እንቅስቃሲያቸውን በተመለከተ ለዚሁ ተገዢ በማድረግ ላይ እምነታቸውንያሳርፋሉ።
የሕግ የበላይነት እንደ አሮጌ ጨርቅ ‹‹አይጣጣፍም አይለጣጠፍም››
አንዳንዶች ከሌሎች ሃገሮች ያገኙትን የሕግየበላይነት ማስመሰ ያድንጋጌ ቁንጽል ሃሳብ በመውሰድ ለጣጥፈው ቀጣጥለውና ቀባብተው ለራሳቸው ጥቅምበማዋልእንደየሕግ የበላይነትድንጋጌ በማስቀመጥና ጥቅም ላይ በማዋል መጠቀሚያ ሲያደርጉት ይታያል። በ2012 ያወጣውን የሽብርተኝነትንመዋጊያአዋጁን ለማሳመን መለስ ዜናዊ የሚከተለውን ለሕሊና የሚሰቀጥጥ ሰበቡን የማሕተም መርገጫ ያደርጋቸዋል የፓርላማ አገልጋዮቹን ሲያስረዳ እንዳለው የሽብርተኝነትን መከላከያ አዋጃችንን ስናወጣ በዓለምላ ይካሉት ጸረሽብር አዋጆችቃል በቃል በመተርጎምነ ው።
በአሜሪካ በእንግሊዝ፤ በአውሮፓያለውን የጸረሽብር አዋጆች ሕግ ወስደናል። ከነዚህ ሶስት ሃገራት የወሰድነው ነው የኛ አዋጅ መሰረቱ። ከነዚህ ሃገራት ለኛ የሚበጀንን እየመረጥን አካተነዋል፡፡ በነዚህ ውስጥ ለምሳሌ ሁሉም ውስጥ ያለው፤ አንድን ድርጅት ሽብርተኛ የሚያሰኘው የሃለፊዎቹና አመራሮቹድርጊት ነው የሚለውን እኛአሻሽለነዋል፡፡ የሽብርተኝነትን ትርጓሜ በተመለከተ አንዳችም ቃል ሳንጨምርና ሳቀንስ እንዳለ ነው የወሰድነው፡፡ አንድምቃል አልተለወጠም፡፡ ቃልበ ቃል ለመውሰዳችንም እራሱን የቻለምክንያት አለን፡፡ በቅድሚያ እነዚህ ሰዎች የዴሞክራሲያው ስርአት ግንባት ልምድ አላቸው፡፡ ከነዚህም ሰዎች ልምድና እውቀት መዋስምንም የሚያሳፍረ ጉዳይ አይደለም፡፡ ከጥሩ መምህር ለመማር ፈቃደኛ መሆን ጠቃሚ እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ ምንም የሚያሳፍር ሁኔታ የለውም፡፡ በሌላው ዓለም ካለው የሽብርተኝነት ሕግና ደንብ የበለጠ እንጂ ከማንኛቸውም ሃገራት ያነሰ አይደለም…።
በዚህ አሳፋሪ በሆነመልኩ በሚሰጥ አሳሳችና ጠባብ አመለካከትን በያዘው ማሳመኛ፤ ስለሕግ ጨርሶ ግንዛቤ ማጣትን አስተሳሰባዊ ስህተትን ለመሟገቻነት ማቅረቡ አሳዛኝና አደናጋሪ ነው፡፡ የሽብርተኛነት መከላከያ አዋጁ በሕግ የበላይነት ላይየተመሰረተ ለመሆኑ ማረጋገጫ ለማድረግ በመጣር የችሎታውን ባዶነት ከማረጋገጥና ‹‹የባለስልጣናት መሟገቻ››” (argumentum ad verecundiam) ከመሆን ውጪ ጠቀሜታ አላስገኘለትም፡፡ የክርክሩ ማሳመኛ መሰረትም፤ አሜሪካና ታላቋ ብሪታንያ ዴሞክራሲያዊና ለሕግ የበላይነትም ተገዢዎች በመሆን የረጂም ዓመታት ልምድ ያላቸው በመሆናቸው በዓለም ካሉት የሽብርተኛነት መከላከያ ሕጎች ሁሉ የበለጡ ናቸው ስለዚህም ከነሱ ቃል በቃል ወስደን ከሽብርተኝነት መከላከያ ደንቦቻቸው ጠቃሚ ያልናቸውን በመውሰድ ተጠቅመንባቸዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም የኛ የሽብርተኝነት መከላከያ ሕጋችን እንከን የለሽና በዓለም ቀዳሚነትን የሚይዝነው ይለናል፡፡ ማንም ቢሆን ረጂሙን የቀጭኔን አንገት ወስዶ ከጅብ ጠንካራ መንጋጋ ጋር የኦቦሸማኔን ፈጣን ቋንጃዎች በመውሰድከ ዝሆን አይበገሬ ጉልበት ጋር በማገናኘት አንበሳን መፍጠር በፍጹም አይቻልም፡፡ የደኑ ንጉሥ በሁለንተናው የተለየ አውሬነው፡፡በተመሳሳዩም የሽብርተኝነትን መከላከያ አዋጅ ከዚህም ከዚያም ቃርሞ በማዳቀል በማንኛውም መመዘኛ ‹‹አንዳችጉድለትየሌለው›› የሚባል የዕዝ አዋጅ መፍጠርን መመርያ ማድረግ አይቻልም።
ኩረጃ እኮ መሃይምነት ከፍተኛው አለማወቅ በመሆኑ፤ይህን መሳዩ ህሊና በዕዝ የፈጠረውን ጉዳይ ‹‹እንከንየለሽ›› ማለት ሕሊናቢስነትን ማረጋገጫ ብቻ ነው፡፡ ከግንዛቤ ማጣት ችግር ባለፈ መለስ የአንግሎ አሜሪካንን ሕግጋት ባህል ማወቅቀ ርቶበ ወሬ ደረጃም ሲነገር ጨርሶ አለመስማቱን በራሱያረጋግጣል፡፡የአንግሎ አሜሪካን ጸረ ሽብርተኛነት ሕግ (መለስ በዝርዝር ያላስቀመጠውና ማንም መገመት እንደሚችለው፤ የአሜሪካውያን የአርበኝነት ድንጋጌ (USA Patriot Act) ሊሆን ይችላል) የሕግቃላቶች፤ ቃላት ሃረጎች ስንኞች፤ ጥቅሶች፤ ፓራግራፎችስብስብ ጋጋታ አይደለም፡፡ የአርበኝነት ድንጋጌ የተረቀቀው በጥንቃቄ ተመክሮበት፤ ከዚያም ኮንግሬስ አገናዝቦትና ተወያይቶበት ተከራክሮበት ጥንቃቄ በተመላበትና፤ በመገናኛብዙሃንም ሕዝባዊ ውይይት ተደርጎበት የሕዝብ አስተያየት (በኢትዮጵያ ለይሉኝታ እንደሚደረገው ሳይሆን) ተሰብስቦና ተመክሮበት የተዘጋ ነው፡፡ በተለይም ከአሜሪካን ሕገመንግሥት ከአራተኛው፤ አምስተኛውና ስድስተኛው አሜንድመንት፤ቁ1 ንቁ9 ጋር በማይቃረንና በማይፋለስመልኩ የተቀረጸነው፡፡……. ቀደምት የአሜሪካን መስራች አባቶችእና የተራው ሕዝብ አንደበቶች ሕሊናቸውን በማይሞግት መልኩ በጥንቃቄ አስበውበትና ጥቅምናጉዳቱን ከሕብረተሰቡ አኳያ በመመዘን ሲቀርጹት ‹‹በአሜሪካ ምድር ንጉሡ ሕጉ ነው፡፡ ነጻ በሆኑ ሃገሮች ሁሉ ከሕጉ በላይ ንጉሥ የለም ሊኖርም አይችልም።”
መለስ የአሜሪካንንና የእንግሊዝን የሽብርተኛነትን መከላከያ ቆርጦ መቀጠል ከፈለገ፤ ቃላትን በመቀንጨብ፤ አንቀጾችን በማግበስበስ፤ ምሳሌዎችን በመኮረጅ ሊሆን አይገባም፡፡ይህን ማድረግ ከተፈለገበ ጥቅልሙሉውን ይዘቱን መውሰድ ያስፈልጋልያ ካልሆነ የተቀነጫጭቦ ኩረጃ የዋናውን ቅርጽ ስለሚያዛባውና ትርጉሙን በማዛነፍ ስለሚያጠፋው ነው። ከመሰረቱ እነዚያቃላቶች፤ ምሳሌዎች፤ አንቀጾች እና ሌሎችም ተፈላጊውን ትርጉም እንዲሰጡና ከዋናው ሕገ መንግሥት ጋር ሳይጣረሱ የሕዝብን መብትም ለማፈራረስ እንዳይመቹ ሆነው በጥንቃቄና እውቀት በተመላው ሁኔታ የተዋቀሩ በመሆናቸው ሲቀነጫጨቡና ሲለጣጠፉ ትርጉማቸው ይጠፋል ከጥቅማቸውም ጉዳታቸው ያመዝናል፡፡ እንዚህ በድፍረት በውር በድንብር የኮረጃቸው ቃላቶች፤ ፓራግራፎች፤ አንቀጾች የተወሳሰበ ታሪካዊ ልዩትርጉም ያላቸውናቸው። መለስ የአሜሪካንን ሕግ ማዳቀልና መኮረጅ ካስፈለገው፤ ግንዛቤ ባልጎደለው መልኩ አስተሳሰብ ባልራቀው መንገድ፤ የአሜሪካን ሕገ መንግሥት ከተቀረጸበት ስሜትና ትርጉም ጋር አገናዝቦ ማስቀመጥ አለበት።
መለስ ማገናዘብ ይጎድለዋል፡፡ የአሜሪካን ጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ መለስ እንደሚያስበው ፍጹም አይደለም ስለዚህም ለመኮረጅ የሚበቃም አይደለም፡፡ ለምሳሌ በ2004 የኒውዮርኩ ፌዴራል ዳኛ፤ የአሜሪካን የአርበኝነት ሕግ ሕገ መንግሥታዊ ይዘትይጎድለዋል ምክንያቱም የኤፍቢአይ ፖሊስ ከሕግ ጥበቃ መብትውጪ፤ ሕዝቡ አስተያየት ተጠየቆ ሃሳቡን ባልቸረበት ሁኔታ፤ ከኢንተርኔት ግልጋሎት ሰጪዎች ኢንፎርሜሽን እንዲሰበስብ መብት ስለሚሰጥ ነው በማለት ውሳኔ አሳለፈ። የአርበኝነት ድንጋጌ ሕገ መንግሥታዊ አይደለም ምክንያቱም በአሜሪካን ሕብረተሰብ ላይ የፌዴራል ቁጥጥርንና ፍተሻን አምስተኛው አሜንድመንት ካጎናጸፈው መብት በተቃራኒ ይጥሳልና፤ ዳኛው ሲተነትኑት “ላለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ሕዝቡ በሕግ የበላይነትን ጠብቆ፤ ተወዳዳሪ በሌለው ነጻነትና ጥበቃ ኖሯል፡፡ ስለዚህም በሕዝቡ ላይ ተጨማሪና ሕጋዊያ ልሆነ ሕግ ልንጭንበት መብቱም ሥላጣኑም የለንም ማድረግም አግባብ አይደለም፤ በማለት ጽፈዋል።
መለስ ያልገባውና መረዳትም ያልቻለውሁኔታ በአሜሪካና በኢትዮጵያ መሃል ያለውን ልዩነትነው፡፡ በአሜሪካ እንደኢትዮጵያ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሕግ ከሕ ገመንግሥቱ ጋር ቅራኔ ከፈጠረተ ቃውሞ ይነሳበታል ምክንያቱም አሜሪካውያን ጠበቆች የሕብረተሰብን ነጻነት እንዳይነካና እንዳይሸራረፍ ሌት ተቀን አፍጠጠው የሚጠብቁና የሚከላከሉት ጥብቅና የሚቆሙና የሚሞግቱ በመኖራቸውና የአሜሪካን ዳኞችም ሙያዊ ግዴታቸውንበሚወጡበትጊዜ ማንም ምንም አይነትጫና አለያም የፍርዱን ሂደት አላግባብበ ማወላገድ እንዲፈርዱ ጫና የሚያደርግባቸውባ ለስልጣን የለምናነው።
በሌላ አባባል ሕጉ ሲጣስ ወጥረው በመያዝኮ ንግሬሱንም ሆነ ፕሬዜዳንቱን በችሎት ፊትገትረው የመያራውጡት ጠበቆችና ይህንንም በፍትሕ ስርአቱ መሰረት የሚዳኙ ዳኞች በመኖራቸውነው፡፡ ስለዚህም ግድፈት ሲገኝ ኮንግሬስንም ሆነፕሬዜዳንቱ የሥልጣኖች ሁሉ የበላይ ወደ ሆነው ሕገ መንግሥት በማቅረብ የፍርድ ነበልባሉን ያቀምሱታል ያልሱታል።
ኢትዮጵያዊያን የሚፈልጉት በህግ የሚመራን መስተዳድር እንጂ በሰዎች የሚመራን አገዛዝ አይደለም?
የሕግ የበላይነትአንድናወጥ የሆነ አሰራር የለውም እንደየአካባቢውና ሕብረተሰቡ የሚተገበር በመሆኑ እንከን የለሽ ብሎ አጠራርና ስያሜ ሊኖር አይችልም፡፡ እርግጥ አንዳንድ ተመሳሳይነትና በሁሉም ሕብረተሰቦች ተቀባይነት ያላቸው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነጥቦች ነቅሶ ለማውጣት በቅድሚ ያ ስለሕግ የበላይነት ከሌሎች ተሞክሮዎችና ልምዶች በቂ እውቅና ሊኖር አስፈላጊነው፡፡ ግን የመማማር ሂደቱ እንደቻይና የሚሞላ አሻንጉሊትና ሕልውና ቢስነትን የተከተበ በብጥስጣሽ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የሰከነ መረጃና ኢንፎርሜሽን ያለውና ያንንም በሚገባ ያጠና ሊሆን ይገባል፡፡ የሕግ የበላይነት ሃሳቦችን በማሰባሰብ የሚቃረኑትን እያስታረቀና ከአንዱ የሚሻለውን ሌላ ሃሳብ በማካተት፤ ወጥ የሆነ የሕግ የበላይነት ለሃገርና ለሕዝብጠቃሚ፤ በሥልጣን ያሉትን ተግባራቸውን እያስተዋለ በመመዘን ሚዛናዊና የሰመረ አስተዳደርን በነጻነትና በሰላም ሃገር የሚመራበትን ዴሞክራሲያው፤ ፍትሃዊና፤ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩበትን የሕግ የበላይነት ነው መፍጠር የሚያስፈልገው።
በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት በእርግጠኝነት የጥንት ልምድ እንጂ አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሕግ ሲጓደልበት፤ ባለስልጣናት አለአግባብ በስልጣናቸው በመመካት ሲጎዱት የሕግን የበላይነት ለማስከበር የሚጠቀምበት ‹‹በሕግ ዓምላክ›› የሚለው ሃረግ ማስረጃ ይሆናል፡፡ ይህም የሚደረግበት ሰበብ፤ የሕግን የበላይነት ፍንጭ በአውቶክራቶች ሸራ ላይ ተስሎ ከሩቁፍንጣቂውስለሚታየውነው፡፡ መረሳት የሌለበት ጉዳይም የኢትዮጵያ ሲቪክ ባህል አደገኛ የሆነውን የሕግ እጦት በመቋቋም እስከ ዛሬ ድረስ መዝለቁ ነው። ‹‹ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ›› የሚለውም የኖረ ተምሳሌት ይህንኑ የሚያረጋግጥነ ው፡፡ ንጉሥ መለስ ዜናዊም የዘመኑ የዚያ ያለፈ ስርአት ቅሪት ተጠቃሚና አክራሪነው፡፡ ከጨቋኝና ግፈኛ የፈላጭቆራጭ አገዛዝ ወደዴሞክራሲ በሚደረገው ሽግግር ኢትዮጵያዊያን ከተለያዩ የሕግ የበላይነት አይነቶች የመምረጥዕድልይኖራቸዋል።
በኔ አመለካከት የሕግ የበላይነት እጅጉን አስፈላጊ የሆነ የዴሞክራሲያው አስተዳደር ስርአት መመርያ ነው፡፡ ሃገርን ለማስተዳደርዋነኛ መመርያነው፡፡ ሕዝባዊ ስርአትን፤ ሃገርን ለመገንባት መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ሃገርን፤ ሰላምን ዴሞክራሲን ፍትህንና የሃቅና የይቅር ለእግዚአብሔርን ስርአት ለመገንባት ቁልፍ ሚና ያለው ነው፡፡ የሕግን የበላይነት ከዴሞክራሲ ጋር አላወዳድርም ሆኖም ግን ግልጽ ሰላማዊና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫን ከድርጅቶች ጋር ሊኖር በሚችል መግባባት ብዙ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ግን አምናለሁ፡፡ የሕግ የበላይነት ለፍትህ ዋስትና አያስገኝም፤ ነገር ግን ለዜጎች ነጻ ፍትሕ የሚደርስበትን መንገድ ነጻና ግልጽ ተጠያቂ በሆነ ፍትሃዊ ስርአት ይቀይሳል፡፡ በዚህም እኩልነትን፤ ሰብአዊ መብትን እና ሌሎችንም ለማስፈን ዋስትና ባይሆንም፤ የሕግ የበላይነት በሌለበት የሰብአዊ ክብር መጠበቅና በፍትሕ ፊትም እኩል ዳኝነት ማግኘት አይቻልም፡፡የመልካም አስተዳደር ዋነኛና ብቸኛ መገለጫው የሰብአዊ መብት መከበር ነው።
ሃሳባዊያን፤ የመንፈሳዊ ምሁራን፤ አብዮታዊያን፤ የሰብአዊ፤ የሲቪል መብቶች ጠበቆች፤ በእነ ሲሴሮ፤ ኦውጎስቲን፤ አኩይናስ፤ ጋንዲ፤ ኪንግ፤ እንዲሁም የአሜሪካንን ዴክሌሬሽን ኦፍ ኢንዲፔንደንስን ባዋቀሩትና ፍትህ አልባ የሆነ ሕግ የእዝ ሕግ እንጂ ፍትህ አይደለም በማለት የተሟገቱትን በመሳሰሉ ቀደምት ታላላቅ ፈላስፋዎች ሥራ ሃሳቤ ይሞላል፡፡ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪነግ “ማንኛውም የሰው ልጆችን ከፍ ከፍ የሚያደረግ ሕግ ሁሉ ፍጹም ነው፡፡ ማንኛውም የሰውን ልጅ ክብር የሚያዋርድም ጎደሎ ነው ብለዋል፡፡ማንም ቢሆን ፍጹም የሆነ ሕገን የማክበር ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን የሞራል ግዴታም አለበት። የጎደለ ሕግንም በተመለከተ አሻፈረኝ የማለትና የመሞገት የሞራል ግዴታ አለበት። ጎደሎ ሕግ በምንም መለኪያ ፍትህ ተብሎ ሊጠቀስና ተቀባይነትም ሊኖረው አይችልም።” ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ በኢትዮጵያም የሚካሄደው ሽግግርም፤ ከባዶ ሕግ ወደ ፍጹምና ምሉዕ ሕግ ሽግግር ነው፡፡ ከአበቃለት ውድቀት ወደ ብሩህ እድገት መሸጋገርያ ነው። መንግሥት ሕዝቡን ሲፈራና ሲያከብር ሕዝቦችም መሪዎቻቸውን አለመፍራትን ሲያውቁና ሲገነዘቡት በኢትዮጵያ መሰረቱ የጸና የሕግ የበላይነት ይኖራል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ።



