ይነጋል በላቸው

አንድ በወያኔው መንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሠራ ባልንጀራ አለኝ። ባለፈው ሰሞን ድንገት ተገናኘንና ሻይ ቢጤ ይዘን ስለዚችው መከረኛ ሀገር ስንጫወት ብዙ ነገር ገረብን። ዛሬ ጊዜ መገረብ ካልሆነ አዲስ ነገር መቼም አልተገኘም። በሀገርና በብዙኃኑ ዜጎች የሚወርደው የሥቃይና የመከራ ዶፍ እንደሆነ በዓይነቱና በይዘቱ እየሰፋ ከመሄድ በስተቀር ሲቀንስ አልታየም፤ እናም እሱም አዲስ ሳይሆን ያው የለመድነው ነውና እንደለመድነው ለ‹ሪከርድ› ያህል አሁንም ጥቂት እንገርብ።

 

አንድ ሽፍታ ነበር። የአንድ ደካማ ገበሬ ሚስት ይወሽማል። ባሻው ጊዜ ሁሉ ወደዚያ ፈሪና ደካማ ገበሬ ቤት እየመጣ ባል ተብዬውን ከቤት በማስወጣት የልቡን ሠርቶ ይወጣል። አንድ ወቅት ይህ ሽፍታ ለሴትዮዋ እንዲህ ይላታል፤ ‹ ጋቢ እፈልጋለሁና ፈትለሽ አሠሪልኝ› እሱዋም ትለዋለች፡- ‹እንዴ? ምንስ ቢሆን ባል አይደለም እንዴ? በገሃድ ፈትዬ እንዴት አለብስሃለሁ? ሰውስ ምን ይለኛል? ባይሆን ፈትዬ አሠራና ባሌን ሽጥ ብዬ ገበያ ስልከው እዚያው እንደፍጥርጥርህ ቀምተህ ውሰድ እንጂ እኔስ አላደርገውም›።እሱም ‹ጥሩ ዘዴ ነው! አይ ሴቶች - ዘዴ መቼም አታጡ› ይልና ይሰናበታል። ሴትዮዋ ጋቢውን ፈትላ ታሠራና ባል ተብዬውን ገበያ ወስዶ እንዲሸጥ ትልከዋለች። በጎንም ለሽፍታው መልእክቱ ይደርሰዋል። ባል ሽጥ የተባለውን ጋቢ ክንዱ ላይ አስቀምጦ ገበያ መሃል ሲንከረፈፍ ያ ወንበዴ ይመጣና በዱላ ዠለጥ አድርጎ ይቀማዋል። ከረፈፉ ባል እቤት ሲገባ ሚስት ‹እንዴት ዋልክ? ገበያው ቀናህ? ጋቢው በደህና ዋጋ ተሸጠልህ?› ትለዋለች። እሱም ይላል፤‹ምን ይሸጣል፤ ያ ወንበዴ ገበያ አስጨናቂ ሰውዬሽ ወሰደልሽ እንጂ!›። ‹ እንዴ? ምነው? አንተስ አንጠልጥለህ የለም እንዴ?ለመሆኑ ዝም አልከው ዛዲያ?› ትለዋለች። ‹አይ፣ ለነገሩ ያቅሜን ተውተርትሬ ነበር፤ ነገር ግን አልቻልኩትም፤ በዱላ ደብድቦ ቀማኝ› ይላታል። ‹ ዱላ ይዞ ነበር እንዴ?› ስትለው ‹አሄሄ … በየትኛው ወንድነቱ ነው ዱላ እሚይዝ? የኔኑ ቀምቶ እንጂ!› አላት አሉ።

 

ወደው አይስቁ ነው ነገሩ። ከሦስት ሚሊዮን ሕዝብ መሀል የወጣ ገበያና ሀገር አስጨናቂ ወያኔ የራሳችንን የ80 ሚሊዮኖቹን ዱላ ቀምቶ መዠለጥ ከያዘ ይሄውና የፊታችን ግም ቦት 20/2004 21 ዓመት ሊሆነው ነው። በጣም ይገርማል። ስንቁንም ትጥቁንም እኛው እየሰጠን መንገዱንም እያሳየን በጠራራ ፀሐይ ቤተ መንግሥት ካስገባነው በኋላ በላያችን ላይ ጢባ ጢቤ ይጫወትብን ያዘ። የመከፋፈያ መርዙንም ረጭቶ እኛን እያናቆረ የወያኔው ግሪሣ ግን በማንአለብኝነት የልቡን እየሠራ ይገኛል። በማን አባት ገደል ገባ የልጆች ጨዋታ እኛን እርስ በርስ እያባላ እሱ ያሻውን ያደርጋል።

 

ዮናስ ጌታቸው የተባለ ዲያስፖራ ዛሬ ምሽት በኢቢኤስ ቲቪ ‹ኑሮ በአሜሪካ› በሚሰኝ ዝግጅት ሲናገር እንደሰማሁት ይህ በሀገራችን ውስጥ በወያኔ ተዘርቶ በአሁኑ ወቅት ፍሬው እየጎመራ ያለው የመከፋፈል አባዜ በውጭ ሀገርም ሥሩን ሰድዶ ኢትዮጵያውያን አንድ እንዳይሆኑ በዘርና በሃይማኖት ነጣጥሎ እያመሳቸው ነው። ተሰድደንም ወያኔ አልለቀቀንም።ለነገሩ እንኳን በሕይወት እያለን ሞተንም የማይለቅ በላ ነው የተላከብን። ይህ የሕልም እንጂ እውን እማይመስል አንደርብ መፍትሔ ካላገኘ ወያኔ 50 ዓመትም ከዚያም በላይ እንደሚቀጠቅጠን ስደትና እንግልቱም በዚያው መጠን ተስፋፍቶ እንደሚቀጥል ከነዚያ ሁለት የኢቢኤስ እንግዶች የቁጭት ንግግር መረዳት ችያለሁ። ህልም እልም በሉ። ሃምሳ ዓመት ቀርቶ አንድ ወርም ሲያስቡት ይጨንቃል። ተንገፈገፍን እኮ።

 

ወደባልንጀራየ ጨዋታ ልመልሳችሁ። የወሬያችን አጀንዳ በኢትዮጵያ የሥልጣን ቦታዎች ሁሉ ሥልጣን ላይ ባሉ ትግሬዎች መያዙን በተመለከተ ነበር - ግራ እንዳይገባችሁ ሥልጣን ላይ የሌሉና በዓላማ ፅናት (የትግሬነትን ወርቃማ ዘመነኛ ዕድል ባለመጠቀም) እንደኛው የሚጨቆኑ ትግሬዎችም ስላሉ ነው። የአማራ ገዢ መደብ ነበር ከተባለ አሁን ደግሞ የትግሬ ገዢ መደብ አለ ቢባል የሚያሣፍር ወይም የሚያስኮንን አይመስለኝም። አንዷ ፍርደ ገምድል ‹ያንቺ ልጅ የኔን ልጅ መትቶት ከሆነ ምች ይምታው፤ የኔ ልጅ ያንቺን ልጅ መትቶት ከሆነ ግን መቼም› አለች እንደተባለው ካልሆነ በስተቀር የአማራ ገዢ መደብ ላይ ማንም ጎጠኛ ዘመኑ አመቸኝ በሎ እየተረባረበ እኔ በግልጽ በሚታየው የትግሬ ገዢ መደብ ላይ ትንሽ ብተነፍስ - እንደስከዛሬው ሁሉ - የሚቀየመኝ እሚኖር አይመስለኝም። ለድረ ገፃዊ አፈናው እንደሆን ለምጀዋለሁ፤ ቢያንስ አንድ አላጣምና በጀመርኩት ልቀጥል ነው፤ ደማችሁ በየትኛውም አቅጣጫ ሳይፈላና ሳይንተከተክ በትግስት ተከተሉኝ።

 

በወዳጄ መሥሪያ ቤት (በቴክኒክ ችግር ምክንያት ስሙን መግለጽ ባለመቻሌ ይቅርታ)70 በመቶው ሠራተኛና 90 በመቶው አመራር የትግሬ ወያኔዎች መሆናቸውን በንዴትና ቁጭት እንደሽሮ እየተንተከተከ ጓደኛየ ነገረኝ። በትግሬዎች ትከሻ ላይ ያረፈውን የአንድን ትልቅ ሀገር የሥልጣንና የሀብት ምንጭ ጠቅልሎ የማስተዳደር ታሪካዊ ኃላፊነት በሚመለከት ሁለታችንም እየተብሰከሰክንና በንዴት እየፎገላን ውይይታችንን ቀጠልን - እንዲያውም ወያኔን ደስ አይበለው ‹አልተናደድንም›። በመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሩን ይዞ ከሞላ ጎደል ሁሉም የአመራር ሥፍራ የተያዘው በትግሬዎች ነው - አልንና ተስማማን። ለላንቲካ ያህል በከፍተኛ የቁጥጥር ቀለበት ውስጥ የሚገኙ የሌላ ብሔር አባላት በአመራር ቦታ ቢኖሩም ከመታዘዝ በስተቀር በራሳቸው ምንም መሥራት አይችሉም። ፌዴራል ፖሊስ 95 ከመቶ በላይ አመራሩ በትግሬ የተያዘ ነው። አየር መንገድና ሲቪል አቬየሽን አመራሩ ከ80 በመቶ በላይ በወያኔ የተያዘ ነው። ወያኔና ትግሬነት መቼም ያው የአንድ ሣንቲም አንደኛው ገጽታ ናቸው። የሌላውን ብሔር የይስሙላ ወያኔ ተውት - የቁጩ ነው። ለሆዱ የገባና ሙስናንና ወንጀልን ጨምሮ በተለያየ ማስፈራሪያ ካርድ የተቀፈደደ - የራሱ ኅልውና የሌለው - በወያኔ ሣምባ እሚተነፍስ - ወያኔ አፍንጫውን ሲዳብስ ኮትና ሸሚዙን በመሀረብነት እሚያቀርብ - የተጋቦት ወያኔ መኖሩ የኢትዮጵያን የሥልጣን ቦታዎች ከወያኔው መንደር የመቶ በመቶ ቁጥጥር አንድ ኢንችም ፈቀቅ አያደርገውም። አፄ ኃ/ሥላሤ ፕሬዚደንት ኒክሰን ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት የምታምር ነጠላቸውን አረሳስተው ሊወስዱባቸው ሲሉ “Nixon, answer my singular, go and eat another” ብለዋል አሉ። ትርጉም፡- ‹ኒክሰን ነጠላየን መልስ፤ ሂድና ሌላህን ብላ!› ወያኔዎችም ‹ሥልጣን የሕዝብ ነው ፤ እኛ ምን ሥልጣንና ሀብት አለንና…› የሚሉ ከሆነ ‹ ይሂዱና ሌላቸውን ይብሉ›። ኢትዮጵያን በወለድ አገድ ይዘው ቁርጥምጥም አድርገው እየጋጧት ነው። የቀራቸው ሰውን እየዘለዘሉ ሥጋውን መብላት ነው።

 

ጉምሩክ ባለሥልጣን አመራሩ መቶ በመቶ በትግሬ የተያዘ ነው። ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሩ - ደሳለኝ እሚባለው ሰውዬ እንደግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለይስሙላ መጎለቱ እንደተጠበቀ ሆኖ - 100 በመቶ በወያኔ ሥር ነው። የመንግሥት ትምህርት ቤቶችና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራር 90 በመቶው በወያኔዎች የተያዘ ነው። ቀበሌና ወረዳን ጨሙሮ ከሞላ ጎደል ሁሉም አስተዳደር ነክ ቦታዎች ለሌላ ብሔር የማይሰጡ የትግሬዎች አንጡራ ቢሮዎች ናቸው። ማዘጋጃ ቤቶች፣ የንግድ ፈቃድና ዕድሳት ቢሮዎች፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ቢሮዎች፣ ምን አለፋችሁ ሁሉም የመንግሥት ቢሮዎች የወያኔ ብቸኛ መፈንጫ ናቸው - የተማሩም ያልተማሩም ትግሬዎች ሥልጣን የመያዝ ትግሬያዊ መብታቸው ያጎናጸፋቸው መብት ነው። የሀገር ውስጥ ጉዳይ የስለላ መዋቅሮች 100 በመቶ በትግሬዎችና በእበላ ባይ ጥገኞች የተሞሉ ናቸው። የሀገሪቱ አንጡራ ሀብት ሕዝብ እየተራበ የመለስን ወንበር ለመጠበቅ እየዋለ ነው። ከሞላ ጎደል የሁሉም በቦርድ የሚተዳደሩ ተቋማትና መ/ቤቶች የቦርድ አባላትና ሊቃነ መናብርት ትግሬዎች መሆን አለባቸው - ለጥቅሙም ለቁጥጥሩም እንዲያመች። ማንም ዜጋ ካምፓኒ ሲመሠርት ለመብረቅ መከላከያ ቢያንስ ጥቂት ትግሬዎችን ማቀፍ አለበት - መያዝ። በአማራነት የሚጠረጠር ዜጋ በሀብት ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ አይፈለግም፤አይፈቀድምም። አማራን ማጥፋት እንጂ እንዲያድግ ዕድል መፍጠር ተገቢ አለመሆኑ በወያኔዎች ዘንድ እንደግብ የተቀመጠ በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ - እመኑኝ- አማራ ሠርቶ አያልፍለትም፤ ለሆዱ አዳሪ ከሆነ ኢትዮጵያ ብትጠበስ እማትሸተው ከሆነ እስከተወሰነ ደረጃ ሊያድግ ይችል ይሆናል። ቢሆንም ‹ይዋል ይደር እንጂ አህያ የጅብ ናት›ን መርሳት አይገባም። አስብቶ አራጁ ወያኔ ሁሉም ዜጋ በዐይኑ ቁራኛ ሥር በመሆኑ በነጻነት እሚንቀሳቀስ ዜጋ ከቶውንም ሊኖር አይችልም። ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሕይወት መኖሩም ያንገበግባቸዋል። ከአሣዛኝ የሚሌኒየሙ ታሪካችን ውስጥ አንዱ ይህን ይመስላል - ኢትዮጵያዊነትንና በተለይም አማራን ደብዛውን ማጥፋት። እስከዚህች ቅጽበት ድረስ ሊፈታ ያልቻለ የታሪክ ምፀታዊ ዕንቆቅልሽ። በእያንዳንዱ የዓለም ሀገር የሚሾሙ ዲፕሎማቶች ትግሬዎች ናቸው። ምናልባት ሰው ካጡና ሊጠቅሙት የሚፈልጉት አፋዳሽ የተጋቦት ወያኔ ካለ በአነስተኛና ጥቃቅን የ‹ሥልጣን› ቦታዎች ሊቀመጥ ይችል ይሆናል። ይህም ሲሆን በከፍተኛ የ24 ሰዓት ክትትልና ቁጥጥር ነው። እጅግ ብዙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የመግባቢያ ቋንቋው ትግርኛ ነው። በዚህ ረገድ ጦጥኛም ቢሆን ግድ የለኝም። ለማሳየት የፈለግሁት ከ11 በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተገኙ ምርጥ ዜጎቻችን የማዕከላዊውን የሥልጣንና የጥቅም ቦታዎች ምን ያህል ለብቻ እንደተቆጣጠሩት ነው። አንድ የሚገርም ትዝብት፡- ሲግናል አካባቢ ነው አሉ - የመኮንኖች መኖሪያ ሠፊ ግቢ ውስጥ፤ ሴቶቹ በሙሉ ትግርኛ ነው አሉ እሚናገሩት። አንደኛዋ ለካንስ ትግርኛ የማትችል ሴት ኖራለች። ሌሎቹ በትግርኛ ወሬያቸውን ሲጠርቁ ይችኛዋ ዕድለቢስና ባጋጣሚ ወደዚያ ቦታ የገባችዋ ሴት ዝም ብላ ትሰማለች - ማዳመጡንማ ከየት አምጥታው። ከዚያን በትግርኛ ሲያናገሯት ባለመመለስዋ ‹ቧይ እንታይ ኮንክን አቲ ዘይተዘሪቢና?› ይብልዋ ማለቴ ይሏታል(አንቺ ለምንድነው የማታናግሪን)። ብሃፂሩ ‹አልችልም›ትላለች። ‹ወይለኸይ እሞ ስለምንታይ ዲኺ አብዚ ግቢ ዝአትው’ኽን?›ይሏታል።(ታዲያ እዚህ ግቢ እንዴት ተገኘሽ - ለማለት ነው - ወይ የቋንቋ መመሳሰል! እንዲያው ዝም ብለን እኮ ነው - ልፉ ሲለን - ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ የምንሆነው)። ጉዳችን ብዙና ብዙ ነው ወገኖቼ። ተዝቆና ተዘርዝሮ አያልቅም። ዕዳችን ብዙ፣ ሸክማችን ግዙፍ፣ ትግላችን መሪር ነው። ይህን በ21 ዓመታት ውስጥ ክፉኛ ተቀብቅቦ የተተከለ የጎጠኝነት ልክፍትና የዘረኝነት መርዝ ለመንቀል ከተዓምር የማይተናነስ ከፍተኛ ሥራ ይጠብቀናል - የመነቀሉ ነገር አያሳስበኝም - በእርግጠኝት ይነቀላል። ችግሩ መቼና ሲነቀል የሚደርሰው ውደመትና ጠሎት እሚያልፈው አካላዊና ኅሊናዊ ጠባሳ ነው፤ በግምት ጊዜውም ቢሆን ሩቅ አይመስለኝም። ተንብይ ብሎ እሚያስቸግረኝ ሰው ቢኖር እውነትን ከመናገር አላመነታም። በአንድ ዓመት ውስጥ ብዙ ለውጥ እንደምናይ ከትንቢት በማይተናነስ ምናልባታዊነት የስድስተኛው የስሜት ሕዋሴ የሚያመላክተኝን የወደፊት ብሩኅ ተስፋ ልጠቁም እፈልጋለሁ።

 

በሌላ በኩል ግን የዘረኝነትና የጠባብነት ጦስ ምን ያህል ከባድ መስዋዕትነት እንደሚጠይቅ ሦርያንና ባሕሬንን በመሳሰሉ ሀገሮች ሕዝቦች እየተማርን መሆናችንን በእግረ መንገድ መጠቆምን እወዳለሁ። ዘረኞች መዥገሮች ናቸው። ከስተው ይሰካሉ፤ አብጠው ሲፈነዱ ወይም ሰውነታችን ክፉኛ እየደማም ቢሆን ጨከን ብለን ስንነቅላቸው ይሞታሉ። ካለምንም መስዋዕትነት ግን አይነቀሉም። ጥገኛ ሕዋስ የራሱ የሆነ የመኖሪያ ዋስትና ስለሌለው የሚለጠፍበትን ሰው የሙጥኝ እንዳለ እስከሕይወቱ ፍጻሜ ይኖራል እንጂ በራሱ ፈቃድ አይለቅም። ወስፋትና ኮሶ ለዚህ ወያኔያዊ ጠባይ ዓይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው። ወያኔ በወስፋትነት ጠባዩ ነው ምድረ ሀበሻን ለሞትና ለስደት ዳርጎ እነሆኝ ዛሬ ሀበሻ ያልደረሰበት የምድራችን ክፍል ላይኖር የቻለው። እስኪያልፍ ያለፋልና አይዞን! ነጻነት ቀርባለች። ሆዳሞችና ለሥልጣንና ለገንዘብ ሲሉ ሀገርንና ወገንን እሚሸጡ ወስፋትና የኮሦ ትሎች ከላያችን እሚረግፉበት ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እየመጣ ነው።… ወያኔዎች አብጠዋል። ዕድሜያቸውንም ጨርሰው ሊፈነዱ ደርሰዋል። በበሰበሰና በገለማ ሥርዓት ውስጥ በፍርሀት እየራዱ ይገኛሉ። የሚያስፈራቸው ግን እንደ 83 ዓመተ ምሕረቱ የወያኔ የብረት ትግል በዚህ ወይ በዚያ አቅጣጫ እየመጣ ባለ ጦር ሳይሆን በዕኩይ ተግባራቸውና የተቀመጡበት ከደምና ከአጥንት የተሠራ ዙፋን በሚያስከትልባቸው ቅዠትና ቅብዥር ነው። መጥፎ ሥራ ጥሩ እንቅልፍን አይሠጥም። ወያኔዎች ያሉ እዬመሰሉ የሉም። ወፍራም እየመሰሉ ከስተዋል። ለዐይናቸን ሙሉ ይምሰሉ እንጂ ጎዶሎ ናቸው - ባዶዎች። ሰው እዬመሰሉ ወደ አውሬነት ተለውጠዋል። እያገኙ የሚያጡ ድሆች ናቸው፤ እንደኛ እያጡ የሚከብሩ ሀብታሞች አይደሉም፤ እኛ ስንሞት እንደምንድንና እንደምንኖርም እናውቃለን። እነሱ ግን እየኖሩ መስለው የሚሞቱ ግዑዛን ናቸው። እያጠራቀሙ አይረኩም። እየወለዱ መካን ናቸው። እየበሉ አይጠረቁም። ነገ ጧት አፈርና ትቢያ በሚሆነው ሥጋ እንጂ በመንፈስ ፍጹም ድሆች ናቸው። ክኒናዊ ማስታገሻ እንጂ እውነተኛ የፀጋ ድኀነትን ወይም ዘላቂ የጤና ፈውስን አያገኙም። በርግጥም ብዙዎቹ የሥጋና የመንፈስ ደዌያት የሚያንገላታቸው በሽተኞች ናቸው። ይህን በሽታቸውን የፎቅ ጋጋታ ወይም የስዊዝ ባንክ የደለበ ተቀማጭ ሊያድንላቸው አይችልም። ድህነታቸውን የረሱ እየመሰላቸው በሀብት ማማ ላይ በሰው ላብና ወዝ ቢወጡም ሌት በቅዠት እየመጣ ያማስናቸዋል። ያልተማሩ ማይማን ጅሎች ናቸው። መቅበዝበዝን እንጂ እርጋታን አያገኙዋትም። የሚሠሩት ክፋት ከዚህ የበለጠ መልካም ዋጋን አያሰጣቸውምና! መጽሐፉም ይላል ‹ ለለአሃዱ በበምግባሩ›። “What goes around comes around.”

 

የክልል መንግሥታት ለይምሰል የአመራር ቦታዎችን የክልሉ ሰዎች የያዙ ቢመስልም እነሐጎስና ጎይቶም ስማቸውን ደስታ፣ ጌታቸው፣ ገመቺሳ፣ አይትሌ፣ ኡስማን፣ዘበርጋ፣ ኡጅሉ፣ ሻመና፣ ፈይሣ፣ ስንሻው፣ … በሚሉ ለየዋሃን(ለስም አምላኪ ቂሎች?) አማላይ የሆኑ የመሀል ሀገር ስሞችን በመጠቀም ተሰግስገው የልባቸውን እያስደረጉና እያደረጉ ይገኛሉ - አዛዥ ናዛዣ እነሱና እነሱ ብቻ ናቸው - ሲፈልጉ ያስገድላሉ፤ ሲያሻቸው ያፈናቅላሉ፤ ይዘርፋሉ ያዘርፋሉ…። ኧረ የነሐጎስ የዚህ ዘመን ድል በጣም ነው እሚያስቀና እባካችሁን። እንዲያው በደፈናው ሁሏም የኢትዮጵያ የሆነች ሥልጣንም ትሁን ሀብት በብቸኝነት ቁጥጥር ውስጥ የገባችው በወያኔዎች እጅ ነው። በረከት በሚመስል ስልቻ/ለቆታ ውስጥ የታሸገች እርግማን ወደትግራዉያን ወንድሞቼና እህቶቼ ሠፈር መግባቷ ከልብ ያሳዝነኛል። አንድ ብልኀ ሰው እንዲህ አለ አሉ፡- ብዙ ከብቶች አሉት። ከእረኞቻቸው አንዱ በጧት ሲከንፍ ይመጣና፤‹ አባባ፣ 20 ላሞች በአንድ ቀን ሌሊት ወልደው አደሩ! ደስ ይበልዎት!› ይላቸዋል። ይሄኔ በደስታ ጮቤ መርገጥ ይገባቸው የነበሩት ቆዳ ለባሽ ከበርቴ ባላገር ‹አሄሄ… ሂጅና ሌላሽን አሞኚ በላት ይቺን አዱኛ! ይቺ አስመሳይ!› አሉ ይባላል። ትልቅ አባባል። ከጨዋ አንደበት የሚፈልቅ ልጨኛ አስተያየት። ያልተጠበቀ እርዚቅ ሲዥጎደጎድ ከጎኑ ሌላ ያልተጠበቀ መቅሰፍት ሊኖር እንደሚችል የማይጠረጥር ሰው የዋህ ነው። ጳውሎስ ኞኞ በሩሕ መጽሔትና ጋዜጣ ሽያጭ ጥሩ ገንዘብ ሲገባለት ጊዜ ‹ዘንድሮ ምን ሊመጣብኝ ይሆን?› ይል እንደነበር ሰምቻለሁ፤ አልቀረለትም። ስለዚህ አገኘሁ ብለህ አትንቀባረር - ምድርን ለመርገጥም አትጸየፍ፤ አጣሁም ብለህ ከእላፊ በላይ አትቆዝም። ሁሉም ሊሆን የግድ ነውና።

 

ቤተ ክህነቱንም ብናይ እንደዚሁ ነው። በኢትዮጵያ የተከፈተው ሰይጣናዊ ዘመቻ እጅግ የተቀነባበረ ነው። ሃይማኖቷንም ሕዝቧንም ዳር ድንበሯንና ሉዓላዊነቷንም እስከወዲያኛው ለማጥፋት ነው ሆ ብሎ ከዓለም ዳርቻ እስከ ዓለም ዳርቻ ተጠራርቶ የተነሳባት - ምድረ አጋንንት። ነገር ግን ወርቅ በእሳት ይፈተን ዘንድ ኢትዮጵያውያንም በወያኔ እየተፈተኑ ነውና ብዙም አንደናገጥ። የፈተናችን ውጤት በቅርቡ ይለጠፋል። በትግስት እንጠብቅ። ተሰትረን የቆየን አሁንም እንታገስ። ‹አይጥ ወልዳ ወልዳ…› እንዲሉ እንዳይሆንብን።

 

ምግባረ ሠናይ እሚባለውን የአባ ጳውሎስ ሆስፒል ብናይ ከዘበኛ እስከ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ትግሬ ናቸው። ሠራተኞቹም ከ80 በመቶ በላይ እሚሆኑት እነሱው ናቸው - እነሱ ስል የኛዎች እነሱ ማለቴ መሆኑን ተረዱልኝ። በየአድባራቱ የሚመደቡት የደብር አስተዳዳሪዎች በአብዛኛው ትግሬዎች ናቸው። እናቴ ትግሬ ማለት ዛሬ ወርቅና አልማዝ ማለት ሆንዋል - በሎካል ሳይሆን በሀርድ ከረንሲ - በዩሮና በስተርሊንግ ፓውንድም ሊገኝ የማይችል ምርጥ ዘር። ለፈገግታ ያህል - እውነተኛ ታሪክ ነው። አንዲት አሮጊት ሴት ዕርዳታ ለመቀበል ከተሰለፉ ሰዎች መካከል ተሰልፈው ወረፋው ይደርሳቸዋል። ዕርዳታ ሰጪው ‹የት አለ ማስረጃዎት?› ብሎ ሲጠይቃቸው ‹የምን ማስረጃ?› ብለው ይመልሳሉ። ‹የኤች አይቪ/ኤድስ ህሙም መሆንዎን የሚገልጽ› ሲላቸው ለካንስ እሳቸው ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የለባቸውም ነበርና ‹ውይ አምላኬ ምን አደረግሁህ? ምናለበት ይህ ኤዲስ የሚሉት በሽታ በኖረብኝና የዛሬን የምቀምሰው አግኝቼ ነገ በሞትኩት!› አሉ። ዛሬ አማራነትም ሆነ ኢትዮጵያዊነት በሳዖላዊ ጭካኔ የሚሳደድና ለዕርድ የሚያጋልጥ መሆኑ በገሃድ እየታዬ የሚገኝ ዘግናኝ ሃቅ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያን በፍቅር ማውሳት በእሳት መጫወት ሆንዋል። የምንለው እውነት ነው፤ ያላልነውና በየጉራንጉሩ እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝ እውነት ግን ይበዛል። ዕድሜ ለመለስ ዜናዊ ሀገራችን ውስጥ ከዚህ ከፍ ሲል ከተገለጸው የበለጠ አሰቃቂ ወያኔያዊ ድሎች ሞልተውናል። በታሪክ መዝግበን እናኖራቸዋለን።

 

የክፍለ ሀገራቸው ሰዎች በሚሠሩት አሣፋሪ ድርጊት አንገታቸውን የሚደፉ ጥቂት ተጋሩ(ትግሬዎች) እንዳሉ እናውቃለን። ኢትዮጵያን ከነዚህ ነቀዞች እጅ ለማውጣትና ወደትክክለኛ መስመር ለማስገባት ቀና ደፋ እሚሉ ትግሬዎች እንዳሉ እናውቃለን። ይህ ተስፋ ሰጪ ነገር ነው። የነሱ ትግልና ጥረት ነው ሌላው የነገ ተስፋችን። ብድር ስንመላለስ ዘመናችንን በከንቱ እንዳንጨርሰው የነዚህኞቹ ደጋግና ነገን አሳቢ ትግራውያን ትግል ከጎናችን መኖሩ ታላቅ ተስፋን ያጭራል፤የትግላችንንም ዕድሜ ያሳጥርልናል፤የሎሚ ተራ ተራን ዘፈንም እንድንረሳ ያግዘናል። አለበለዚያ እንደጠፉት ትግሬዎችና አማሮች ወይም ሌሎች ዜጎች ከሆነ ነገ እሳት እሚጫጫርና ቡና እሚጠራራ ባልኖረ። እንደወያኔ አያያዝ ከሆነና የፈጣሪ ልዩ ጥበቃ ባይጨመርበት ኖሮ ነገራችን ሁሉ ከአሁኑ ግምኛ በሆነ። ነገር ግን ‹ልጁን አንሺ ምጡን እርሺ› ብለን ነገን በነገነቱ ብቻ ለመኖር እንዘጋጃለን እንጂ ሞኝነትንና ወያኔያዊ ‹አይቡን ሳያዩት አጓቱን ጨለጡት› ዓይነት ቂልነትን በምንም ዓይነት መልኩ አንደግምም። አሁን ግን እውነቱን እንናገራለን። ስንናገርም ነገን ማሰብ ባቃታቸው የገዛ ልጆቻችን ትግሬዎች በልዩ ሁኔታ ቅኝ ግዛት ሥር መግባታችንን በድፍረት በማወጅ ነው።… ይህ በግልጽ የሚታይ ሀገራዊ እውነት ለአንዳንዶች ሊኮሰኩስ ይችል ይሆናል - በተለያዩ አሳማኝና ኢአሳማኝ ምክንያቶች የተነሳ። ይሁንና ዋጮን ቢገለብጡት ያው ዋጮ ነውና እውነቱ እውነት መሆኑ ፈጥጦ እየታዬ ነው። እውነትን የምንናገረው ደግሞ ማንንም ለማስደሰት ወይም ለማስከፋት አይደለም - እውነት ስለሆነ ብቻ እንጂ። ጥሩ ኢትዮጵያውያን ትግሬዎችም በዚህ መጣጥፍ ልትከፉ አይገባም። እውነትና መቻቻል ለዬቅል ናቸው። መቻቻል እሚመጣው እየጎመዘዘንም ቢሆን እውነቱን ስንቀበል ነው። የመለስንና የግብረ አበሮቹን ፀሐይ የሞቀው ሀገራዊ እውነታ ለሺኛ ጊዜ መናገር በጥፋት ሊፈረጅ እሚገባው አይመስለኝም፤ ግልብጥ ዘረኝነትም አይደለም። ሲቆነጠጥ የማይጮህና የማያለቅስ ሕጻን አንድም ስሜት አልባ ነው አለዚያም ግዑዝ ነገር ነው። ይህን ማድረጌ ምናልባት በውጭ ለሚኖሩ ወገኖች ይጠቅም እንደሆነ እንጂ ሀገር ቤት ውስጥ ላለነው ይህ ዓይነቱ የወያኔ ድርጊት የለመድነውና የተለማመድነው ነገር ስለሆነ አይሞቀንም አይበርደንም። እየጠበቅን ያለነው የፈጣሪን የማይቀር ፍርድ ብቻ ነው - በቦሌም ይምጣ በባሌ። ስለዚህ ‹ጨዋ ሲጋባ የተፋታ ያህል ነው› እንዲሉ እውነቱን ከአሁኑ እንጋፈጠውና ለመፍትሔው በጋራ እንንቀሳቀስ። የማይቀር አይቀርም። የሚቀር ዱሮውንም አልነበረም። ምን አዲስ ነገር አለ? ምንም! እየተጎዳን ያለን እኛ፣ የምንሞት እኛ፣ የምንሰደድ እኛ፣…ሞቱ እንግልቱ ባይቀርልን መተንፈሱ ይቅርብን?

 

በመጨረሻም የምለየው ዊሊ ሊንች የተሰኘ የ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ባሪያ ፈንጋይ ለመሰሎቹ ባሪያ ፈንጋዮች ባስተላለፈው የባሪያ አያያዝ መልእክት ነው። (ይህን ጽሑፍ የጾደብክልኝን(የመየልክልኝን) ሰው አመሰግናለሁ።)

 

ክቡራን ሆይ! ችግሮቻችሁ ምን እንደሆኑ ስለምታውቁ መዘርዘር አያስፈልገኝም። እዚህ የተገኘሁት የችግሮቻችሁን ብዛት ለመጥቀስ ሳይሆን መፍትሔያቸውን ልጠቁማችሁ ነው። በዚህ በምታዩት ቦርሣ ውስጥ ጥቁሮች ባሪያዎቻችሁን እንዴት መቆጣጠር እንደምትችሉ የሚረዳ ፍቱን ዘዴ ይገኛል። ይህን የባሪያ መቆጣጠሪያ ሥልት በጥንቃቄ ሥራ ላይ ካዋላችሁት ለ300 ዓመትና ከዚያም በላይ ሊያለግላችሁ እንደሚችል ለእያንዳንዳችሁ ዋስትና እሰጣለሁ። ዘዴው ቀላል ነው። ማንኛውም የቤተሰባችሁ አባል ወይም ባሪያዎቻችሁን የሚቆጣጠር እንደራሴያችሁ ሊጠቀምበት ይችላል። በባሪያዎች መካከል የሚታዩትን ልዩነቶች ለይቼ ከማወቄም በተጨማሪ እነዚህ ልዩነቶቻቸው ይበልጥ ጎልተው የሚወጡበትንና ለእኛ ለባሪያ አሳዳሪዎቹ የሚጠቅሙበትን ልዩ ብልሃት ቀይሻለሁ። በዚህም መሠረት ባሪያዎች እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡና እንዳይስማሙ ለኛ የቁጥጥር ሥርዓትም ምቹ እንዲሆኑ(ልን) በመካከላቸው ፍርሀት፣ አለመተማመንና ምቀኝነት ባሕርያቸው እንዲሆኑ የሚያስችል በውጤቱም ሰጥ ለጥ ብለው እንዲገዙልን የሚያደርጉ ዘመንም የማይሽራቸው ልዩ ሥልቶችን ቀምሬያለሁ።

 

እነዚህ ሥልቶች በዌስት ኢንዲስ ግዛት ውስጥ ባለኝ አነስተኛ የእርሻ ማሣ ላይ ተሞክረው አጥጋቢ ውጤት አስገኝተዋል፤ በደቡቡም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚሠሩ አምናለሁ። በባሪያዎች መካከል የሚታዩ እነዚህን የልዩነት ነጥቦች ልብ ብላችሁ አጢኗቸው። በዚህ የልዩነቶች ዝርዝር ውስጥ እንደአጋጣሚ ሆኖ የመጀመሪያ ያደረግሁት ዕድሜን ነው። ቀጥሎ ቀለም ነው። በመቀጠልም የዕውቀትና ግንዛቤ ደረጃ፣ የሰውነት አቋም (መጠን)፣ ፆታ፣ የእርሻዎች መጠንና ይዞታ፣ የባለቤቶች አመለካከት፣ ባሪያዎች የሚኖሩበት ቦታና ሁኔታ ለምሳሌ በሸለቆ ውስጥ ወይም በኮረብታ ላይ ወይም በስተምዕራብና በስተምሥራቅ አሊያም በስተደቡብና በስተሰሜን፣ የጸጉራቸው ሁኔታ(ለስላሳ ወይንስ ከርዳዳ - ረጂም ወይንስ አጭር)፣ … የመሳሰሉት ከልዩነቶቻቸው ጥቂቶቹ ናቸው። ይህን ካልኩ በኋላ ምን ልትሠሩ እንደምትችሉ በጥቂቱ ልጠቁማችሁ። ከዚያ በፊት ግን በባሪያዎች መካከል መተማመን እንዲፈጠር ከማድረግ ይልቅ እርስ በርስ መጠራጠርና አለመተማመን እንዲሁም መሞጋገስና መከባበር እንዲኖር ከማድረግ ይልቅ በምቀኝነት እንዲጠላለፉ ማድረግ ከሁሉ የተሻለው ዘዴ መሆኑን ልጠቁም እወዳለሁ። በመካከላቸው እንዲህ ያለ ልዩነት እንዲፈጠርና አንዱ ሌላውን በክፉ ዐይን እየተመለከተ ምድረ ባሪያ እርስ በርሱ እንዲናከስ መንገዱ ከተመቻቸ አለማንም ጣልቃ ገብት ራሳቸው በሚያደርጉት ግጭትና ፍጭት ለመቶዎች ብቻ ሳይሆን ለሺዎች ዓመታትም ቢሆን እኛ ሳንለፋ ለኛ ይገዙልናል። ዋናው ሥራችን በደካማ ጎናቸው ገብተን እነሱን እስከወዲያኛው ማናከስ ነው። በተጨማሪም ወጣቱን ባሪያ ከሽማግሌው ባሪያ ጋር፣ በመልክ ጠይሙን ባሪያ ከጥቁሩ ባሪያ ጋር፣ ሴቶችን ከወንዶች ወይም ወንዶችን ከሴቶች ጋር ማጋጨትንና ስምምነት እንዳይኖራቸው የዘወትር ጥረት ማድረግን መዘንጋት የለባችሁም። የናንተው ወገን የሆኑ ነጭ አገልጋዮቻችሁና ዕንባ ጠባቂዎቻችሁ ጥቁሮች ባሪያዎቻችሁን ሁሌም እንዲጠራጠሯቸውና እምነት እንዳይጥሉባቸው አድርጉ። …

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ