(አምስተርዳም ጉባዔ ላይ ለጥናት የቀረበ ጽሑፍ)

ፈቃዱ በቀለ

የታሪክ ግዴታ ሆኖ የሰው ልጅ እንደማኅበረሰብ ከተደራጀና፣ ሥልጣንና ሀብት በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቅ ከጀመረ ወዲህ የአንድ ህዝብ ዕድልና የወደፊት ጉዞው፣ ታሪክ የመስራትና ያለመስራት ችሎታው በመጀመሪያ ደረጃ ሊወሰን የሚችለው ሥልጣንን በቁጥጥራቸው ውስጥ ባስቀመጡ ጥቂት ሰዎች አማካይነት ነው።

 

በታሪክ ውስጥ አንድ ህዝብ ከአንድ አገዛዝ ቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ የራሱን ህይወት በነፃ ያደራጀበትና ታሪክ የሰራበት በተለይም ቀደም ብለው በነበሩ ስርዓቶች ውስጥ አልነበረም።
እንደሚታወቀው የአንድ አገዛዝ ምንነት የሚታወቀው ታሪክ ለመስራት ባለው ችሎታና አገርን ጥበባዊ በሆነ መልክ በማስተዳደር ረገድ ነው። አንድ አገዛዝ ታሪክን እንዲሰራ ከፈለገ ደግሞ ንቃተ-ህሊናው በጣም ወሳኝ ነው። በታሪክ ውስጥ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ሥልጣን ላይ ባጋጣሚም ሆነ በጉልበት ቁጥጥ ያሉ ኃይሎች ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን ለመረዳት ብዙ ዐመታት ይፈጅባችዋል። ከዚህ በላይ ይልቅ ከውስጥና ከውጭ የሚመጣ ግፊት ለአንድ አገዛዝ አስተሳሰቡን መለወጥና ታሪክ ለመስራት መቻል ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱ የተረጋገጠ ነው።

ይህንንም አጋጣሚ የሚጠቀምና ታሪካዊ ስራ ለመስራት የሚችል ኃይል ደግሞ ከንቃተ-ህሊና ባሻገር ውስጣዊ ፍላጎት (Will) እንዲኖረው ያስፈልጋል። ሥልጣን ላይ የተቀመጠው እንዲያው ሥልጣን ላይ ለመቀመጥ ብቻ እንዳልሆነ የሚገነዘብና የተገነዘበ ኃይል መሆን አለበት። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብና በተከታታይ የሚመጡትንም ትውልዶች ዕድል በሱ እጅ እንደወደቀ የሚያውቅ መሆን አለበት። ባጭሩ የታሪክ ኃላፊነት ያለበትና የተገነዘበ መሆን አለበት። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ