ውይይት ከአቶ ደበበ ጉሉ፣ ዳንኤል ጥላሁንና ተክለሚካኤል አበበ ጋር
በሳውድ አረቢያ ይኖሩ በነበሩ እጅግ ቁጥራቸው የበዛ ኢትዮጵያዊያን ላይ ተደራራቢ እስራት፣ ወከባ፣ እንግልትና በኢትዮጵያዊያት ሴቶች እህቶቻ ላይ አስገድዶ መድፈርን ያስከተለ ስቃይ ሲደርስ ሰንብቷል። መቆሚያ ጊዜውም በውል አልታወቀም። የእነኝህን ኢትዮጵያዊያን ስቃይ በሚመለከት ቫንኩቨር ካናዳ በየሳምንቱ የሚተላለፈው መለከት የኢትዮጵያ ራዲዮ ከአቶ ደበበ ጉሉ፣ ዳንኤል ጥላሁንና ተክለሚካኤል አበበ ጋር ውይይት ተደርጓል። የመንግስት ሚና፣ በውጭና ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎና ጥረት፤ ውጤትና ቀጣይነት ይዳሰሳሉ። ውይይቱ Dec 30, 2013 የቀረበ ነው።