ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?
ግርማ ሞገስ
ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የሀገር ተወላጅ እና የውጭ ሀገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በሥልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሕቅ ነው።
ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በሥልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሠራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከሀገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የሕክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ሥራ የመሳሰሉ ዘመናዊ (Secular) ትምህርት ቀስመው ሀገራቸውን ለመርዳት ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን የእነ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ (1886-1919) ሁሉ የቁጭት ጥያቄ ነበር።
በጣት የሚቆጠረው የነገብረሕይወት ትውልድ የውጭ ትምህርት ቀስሞ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ባፄ ምኒልክ ዘመን ነበር። ይሁን እንጂ ለዘመናዊነት በር የተከፈተው ባፄ ኃይለሥላሴ ዘመን እንደነበር፣ በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ1942 ዓመተ ምህረት (እ.ኤ.አ. 1950) የአዲስ አበባ የተፈጥሮ እና የሶሻል ሣይንስ ኮሌጅ መከፈቱን፤ ኮሌጁ የተደራጀው በኢትዮጵያ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመክፈት በንቃት ይሠሩ በነበሩ ካናዳውያን እየሱሳውያን (Jesuits) ሲሆን፣ የተማሪዎቹ ቁጥር ከ100 በታች እንደነበር ክፍሉ ታደሰ (The Generation, p. 15-16) ያመለክታል። እሱም ቢሆን እጅግ ዘግይቶ የመጣ በውቅያኖስ ላይ ያረፈ ትንሽ ጠብታ ያህል ነበር። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)



