ወደኋላ የተጓዘው የፕሬስ ሕግ
“ተሻሽሏል” በሚል ሰኔ 24 ቀን 2000 ዓ.ም. (July 1, 2008) በፓርላማው የፀደቀውና አፋኙ የፕሬስ ሕግ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባሉ ወገኖች ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው መዘገባችን አይዘነጋም። በሀገር ውስጥ በመታተም ላይ ያሉ የግል ፕሬሶች ሕጉን አስመልክቶ ያላቸውን ተቃውሞ በተደጋጋሚ ሲያሱሙ የነበረና አሁንም ድረስ ሕጉ አፋኝ መሆኑን እየገለጹ ቢሆንም፤ ገዥው የኢህአዴግ መንግሥት ግን ጩኸታቸውን ‘ጆሮ ዳባ’ ማለቱ ይታወቃል።
ለህዝብ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በሀገር ውስጥ እየታተሙ ካሉት የግሉ ፕሬሶች ውስጥ የ“እንቢልታ” እና የ”ሪፖርተር” ጋዜጦች በርዕሰ አንቀጾቻቸው በሕጉ ላይ ያላቸውን አቋምና አስተያየት፣ እንዲሁም የፎርቹን ጋዜጣ ባለቤትና ዋና አዘጋጅ አቶ ታምራት ገ/ጊዮርጊስ፣ የሪፖርተር አሣታሚና ዋና አዘጋጅ አቶ አማረ አረጋዊ እና የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ዳዊት ከበደ ከእንቢልታ ጋዜጣ ጋር አዲሱን የፕሬስ ሕግ አስመልክቶ ቃለምልልስ አድርገዋል።
ርዕሰ አንቀጾቹንና ቃለምልልሱን እንደሚከተለው ያገኙታል።
1፣ ”የማያንቀሳቅሱ አዋጆችን በማፅደቅ ዲሞክራሲያዊ አገር መገንባት አይቻልም” እንቢልታ ጋዜጣ በቅጽ 1፣ ቁጥር 28 ዕትሙ
2፣ ”ከፕሬስ ነፃነት ሽሽት” ሪፖርተር ጋዜጣ ነኀሴ 13 ቀን 2000 ዓ.ም.
3፣ ”በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንቢልታ ጋዜጣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 30
4፣ “ወደኋላ የተጓዘው አዲሱ የፕሬስ ሕግ” (እንቢልታ ጋዜጣ ከሦስቱ ጋዜጦች ጋር ያደረገው ቃለምልልስ