ዕርቀ ሠላም ማን ይፈልጋል? ለምንስ ያስፈልገናል?

ከሽመልስ ተክለጻድቅ (ዶ/ር)

በተጣሉ ግለሰቦች፣ ወገኖች፣ ማኅበረሰቦች መካከል ከሠላም መለስተኛ በሆነ መልኩ በአሸናፊው ወገን ተጽዕኖና ፍላጎት ላይ የተመሠረተ መረጋጋት ሊፈጠር ይችላል። መረጋጋቱ ለረጅም ጊዜ ከቆየና የአሸናፊው እብሪት ከበረደ፣ ተሸናፊውም የደረሰበት የአካልም ሆነ የመንፈስ ቁስሉ ካገገመ ሠላሙ እየዳበረ መሄድ ይችላል።

 

ጥሉና መናቆሩ ከከረረ፣ ቅራኔው የርዕዮተ ዓለም እምነት ላይ የተመሠረተ ከሆነ ወይም ነው ብሎ ከታመነ፣ ግጭቱ ያስከተለውም ውጤት በሠፊው የነፍስ መጥፋትና የንብረት መውደም ካደረሰ፣ ግጭቱን ያስነሳው ግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ቅራኔ ሳይፈታና አሸናፊና ተሸናፊውን ሳይለይ የግጭቱ ጊዜ ከተራዘመ፣ በተጣሉት ወገኖች መካከል ሠላም ሊወርድ የሚችለው በዕርቀ ሠላም መንገድ ብቻ ነው። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ