”ጴጥሮስ ያቺን” ቃል (መክብብ ማሞ)
መክብብ ማሞ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )
”ፋሺስቶች ያገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሉዋቸው እውነት እንዳይመስላችሁ። ሽፍታ ማለት ያለ ሀገሩ መጥቶ የሰውን ሀገር የሚወር ይህ በመካከላችሁ መጥቶ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ለእርሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው። የኢትዮጵያ መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን!” አቡነ ጴጥሮስ።
ያለፈው ረቡዕ ሐምሌ 22 ቀን ጀግናው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ በግፍ የተገደሉበት 73ኛ ዓመት ነበር። እኒህ ታላቅ አባት ለሰማዕትነት ያበቃቸው ዋናው ምክንያት በወቅቱ ለተጠየቁት ቀላል ለሚመስል ጥያቄ፤ ”ቃሌን አልክድም” ብለው በመቆማቸው ነበር።



