




ኩችዬ
በውጭ የሚኖረው ወጣት ባገሩ ፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ አለመሆኑ ያሳዝነኛል። አንዳንዴማ ከዚያም ያለፈ ነው የሚያደርገኝ። ሰሞኑን ታዲያ ጃዋር ሲራጅ መሀመድ የተባለ ኦሮሞ ወገኔ ተስፋ ዘራብኝ። ሙሉውን አስነብበኝ ...





ፍቅሩ
ባለፈው እሁድ ሚያዝያ 3 ቀን 2002 ዓ.ም. የወጣው በሀገር ቤት የሚታተመው የእንግሊዝኛው ”ፎርቹን” ጋዜጣ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ግለሰቦች ለኢህአዲግ ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ 20 ሚሊዮን ብር እንዳዋጡ ዘገበ። ’እሰየው!’ የሚያሰኝ ክንውን ነው - ከምርጫ 97 በኋላ የንግዱ ማኅበረሰብ እንዲህ በግላጭ የሚደግፈውን ፓርቲ ማሳወቁ ’ይበል!’ የሚያሰኝ ነው። በንግድ ሥራ የተሰማሩ ግለሰቦች እንዲህ በድፍረት የሚደግፉትን ፓርቲ ሲያሳውቁ ለሁሉም ጥሩ ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ የፈቀደውን ፓርቲ የመደገፍ መብት አለውና። ሙሉውን አስነብበኝ ...





መክብብ ማሞ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
የስምንት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው መድረክ ከፍተኛ አመራሮች በአሜሪካ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እንዲሁም በመጪው ምርጫ ዙሪያ በውጪ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ ድጋፍ ለማግኘትና ያለውንም ለማጠናከር ካለፈው ሣምንት ጀምሮ ወደ አሜሪካ እየገቡ ይገኛሉ። አቶ ገብሩ አስራት፣ ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራው እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የሚገኙበት ቡድን ያለፈው ቅዳሜ በሲያትል እንደሁም እሁድ በሳን ሆዜ ከተሞች ስብሰባዎችን አድርገዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...





አሥራት አብርሃም
በጊዜ ምንገባው
ማምሸቱን የተውነው
ሌባ ወይም ሰይጣን
አይደለም … የፈራነው
ፅልመት ተገን አርገው
ማጅራት የሚመቱ
ገዥዎች ስላሉ ነው።
ይህ ግጥም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉ ተቀዋሚ ፖለቲከኞች ስጋት የሚያመላክት ነው። የገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት ቀን ህዝቡ እያየ በተቀዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ ሲብስባቸው ወይም ሲደነግጡ ካልሆነ በስተቀር ጥቃት ለማድረስ አይደፍሩም። ማታ በጭለማ ከሆነ ግን እንድትመታ ወይ ማጅራት መቺ ገዝተው፣ ወይም ከአሁን በፊት በሆነ ነገር የተጣላህን ሰው ፈልገው፣ “አይዞህ! እንደፈለክ አድርገው!” ብለው ይልኩብሃል። ዕድለኛ ከሆንክ ተደብድበህ በሕይወት ትተርፋለህ። እስካሁን አራት የዓረና-መድረክ ተወዳዳሪዎች በዚሁ መልክ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ከሞት ብቻ ተርፈዋል። ድንገት ጎደሎ ቀን ከገጠመህ ደግሞ ሞትህ የግድ ይሆንና ልክ እንደ አረጋዊ ገብረዮሐንስ የሠላማዊ ትግል ሰማዕት ሆነህ ትሞታለህ። ሙሉውን አስነብበኝ ...





ተድላ ወሰኔ ነጋሽ - Tirschenreuth, Germany
... በዚሁ መጠን ትግሉ እንዲቀጥል ለማድረግ ወሳኝ ነን በሚሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና መሪዎቻቸው በዓላማቸው ፀንተው ሲቆዩና የትግል ስልቶቻቸውን በኢህአዲግ መጠን ለአሸናፊነት በሚያበቃ ተርታ ደርጅተው አይታዩም። አንድነትና ኢትዮጵያዊነት በወሬ ወይም በወረቀት ላይ ብቻ ካልሆነ በስተቀር እስከመጨረሻው አይተገበርም። ... ሙሉውን አስነብበኝ ...