አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Prof. Getatchew Haile ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

መግቢያ፤

መጀመሪያ ለመግቢያ ያህል፥ “ዘመድ” የሚለውን ቃል እንዴትና ለምን እንደተጠቀምኩበት ላስረዳ። “ዘመድ” ማለት “ወገን” ማለት ነው። በእንግሊዝኛ “kin, family, tribe” ማለት ነው። በየሊቃቸው የሚመሩ የተለያዩ የመላእክት ሠራዊት “ዘመድ” ወይም “ነገድ” ነው የሚባሉት”--ዘመደ መላእክት፣ ነገደ መላእክት። ሌሎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው መጠሪያዎች “ቤት” (ቤተ አምሐራ)፣ “ጎሳ” (የጉጂ ጎሳ)፣ “ዘር” ናቸው። ዛሬ ደግሞ “ብሔረ ሰብ” የሚለው መጠሪያ ነግሧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንተም ደመቀ መኮንን!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አንተነህ መርዕድ

ይድረስ ለማውቅህና ለማታውቀኝ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

የኢትዮጵያ ህዝብ እስከአሁን መሪዎቹን መርጦ አያውቅም። ሁሉም በጉልበት ትክሻው ላይ ተፈራርቀው ወጥተውበታል፤ እየተካኩም አሁን ላለበት ከዓለም የመጨረሻነትና የርሃብ ተምሳሌትነት አድርሰውታል፤ አድርሳችሁታል። ያለፈ ታሪክ እየቆፈርን ማን ምን ሠራ እያሉ ለመዘባነን በአሁኑ ወቅት ህሊና ላለው አንገብጋቢ ጥያቄ አይመስለኝም። በእጃችን ላይ ያለውን ዐይኑን አፍጥጦ የመጣውንና የብዙ ሺዎችን ህይወት ለመቅጠፍ “ሀ’’ ብሎ የጀመረውን ርሃብ ለመግታት ደመኛ ጠላቶችም ቢሆኑ የሚተባበሩበት ወቅት ነውና። ከየትም ወገን ይምጣ ርሃብን ለፖለቲካ ፍጆታ የመጠቀምን ያህል ጭካኔ ከቶ የለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ችጋርና የእውቀት ችጋር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በፈረንጆች ባህል እውቀት ሥልጣን ነው፤ እንዲያውም እውቀት ኃይል ነው ይላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ባህል እውቀት ሥልጣን የለውም፤ እንዲያውም ሥልጣን እውቀት ይመስለናል፡፡

በ1951 ዓ.ም. በትግራይ ችጋርን በዓይኔ አይቻለሁ፤ በጆሮዬ ሰምቻለሁ፤ በአካሌ ቀምሼዋለሁ፤ ጠኔ ይዞኝ ተደግፌ ወደቤቴ ገብቻለሁ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መከራ ሲመጣ አይነግርም ዐዋጅ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ነፃነት ዘለቀ

ውድ አንባቢያን ዛሬ ትንሽ ለየት ባለ ሁኔታ የልብ የልባችንን ነው የምንጫወተው። መደባበቅ ብሎ ነገር አይኖርም። ለምኑ ብለን? ለየትኛው ጊዜስ ብለን እንወሻሽ? “በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ” - መተዛዘብን ለዛሬ እንርሳት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የድህነት ዘበኛ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

Ethiopian Electric Power Corporation. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንጓድ ካፍትሌ ከአርባምንጭ

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የደርግ ሥርዓት መገርሰሱን በማስመልከት ያስተላለፉትን መልዕክት ሰምቼ ነበር። መልዕክቱ ባጭሩ እንዲህ የሚል ነበር። “የድህነት ዘበኛ የነበረው ሥርዓት ስለተወገደ ከዚህ በኋላ ጦርነታችሁ ከዘበኛው ጋር ሳይሆን ቀጥታ ከጠላቱ (ድህነት) ጋር ነው።” በእርግጥ ደርግ ሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ”ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር!” እያለ ሕዝቡ በድህነት እንዲማቅቅ አድርጓል። ከዚህ የተነሳ የሥርዓቱ መውደቅ ብዙዎችን በደስታ አስፈንጥዟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቀድሞ ዴምሕት አባላት በወያኔ ፎቶገጭ ቤት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ነፃነት ዘለቀ

Former TPDM fighters. የቀድሞ ዴምሕት አባላት

እንደምን ሰነበታችሁ። እንኳን ለአዲሱ ዓመት የ2008 ዓ.ም. ሁለተኛ ወር “ለጥቅምት አንድ አጥንት” በሠላም አደረሳቹ። ጥቅምት ብርዳምና ንፋሳም ነው። ዘንድሮም እንደዛው ነው። የአዲስ አበባ የሰሞኑ ብርድ ሚስት ያሳቅፋል። ግን ስንገናኝ ሠላምታ የማንለዋወጠው ለምንድነው? ብዙ መጣጥጥፍ ጸሐፊዎች ይህን ወግ ልማድ ረስተው በቀጥታ ሊያስተላልፉት ወደሚፈልገጉት ቁም ነገር ይገባሉ - ያበሳጩኛል። “እንዴት ሰነበታችሁ” ማለት ማንን ገደለ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ