“ወያኔዎችን አጥኗቸው፣ እወቋቸው“ ሙሉጌታ ሉሌ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሙሉጌታ ሉሌ / Mulugeta Luleበልጅግ ዓሊ

"ደግ ደጉን ስናጣ፣ ኀዘኑ መረረ

ሞት አምላኩ ከድቶት፣ ገሎት በነበረ።"

- የሠፈራችን ሙሾ አውራጅ

እነሆ ጋሼ ሙሉጌታ ዐረፈ። ከዚህ ምስቅልቅሉና ቅጥ አምባሩ ከወጣ ዓለም በአካል ተለየ። ጋሼ ሙሉጌታ ከእንግዲህ የሀገሩን አፈር በሞቱ እንኳ ላይቀምስ ነው። ዛሬ የሰው ሀገር አፈር ለብሶ በዝምታ ማሸለቡን መርጧል። ሀገሩን እንደናፈቀ የተለያት ቢሆንም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር ትምህርት ሰጥቶን አልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሰሞኑ ጫጫታ ባሻገር፣ የትብብሩ መሠረቶችና ተግዳሮቶች በቅጡ መዳሰስ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዩሱፍ ያሲን (ኦስሎ)

የዴሞክራሲያዊ ምንቕስቓስ ህዝቢ ትግራይ ዴምህት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሞላ አስገዶም / Mola Asgedom

ከሰሞኑ ጫጫታ ባሻገር

የሞላ አስገዶም ኩብለላ፣ ፍርጠጣ ክሕደት ወይም በመንግሥት ደጋፊዎች እንደተባለው ወሽመጥ በጣሽ የጀግንነት ሥራ በአሥመራ ተጓዞችና ደርሶ - ተመላሾች መሓል እየተቋጠረ መጥቷል ብለን ያሰብነው ንትርኩን እንደገና አደበላለቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይቅርታ - የወያኔ ካርታ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይቅርታ - የወያኔ ካርታ / yekerta ye tplf kartaይገረም አለሙ

1437ኛው የኢድ አል አድኻ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲከበር ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት፤ በሽብር ወንጀል ተከሰው ከተፈረደባቸው የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መካከል ስድስቱ በቅርቡ የተለቀቁት በእነርሱ ጥያቄና ጥረት እንደሆነ፤ ጥያቄአቸው ምላሽ በማግኘቱና ጥረታቸው በመሳካቱ መደሰታቸውን ገልጸው፤ ለመንግሥት ምሥጋና ማቅረባቸውን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ከስፍራው ባስተላላፈው ዘገባ አሰምቶናል። ወያኔ ግዜና ወቅት እየጠበቀ የሚጠቀምባት የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ የይቅርታ ካርድ በሌላ መንገድና መልክ ተመዘዘች ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትግሉ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ወይንስ ለምኒልክ ቤተመንግሥት?

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

Prof. Mesfin Woldemariam. ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ይገረም አለሙ

ፈጣሪ ዕድሜ ከጥንካሬ ጋር ያደላቸው በሀገር ጉዳይ የማይታክቱት ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ሰሞኑን በምድረ አሜሪካ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረጉትን ውይይት፤ ዘመነ ቴክኖሎጂ ምስጋን ይግባውና በያለንበት ሆነነን ተከታትለናል። ከውይይቱ ታዳሚዎች ከቀረቡ በርካታ ጥያቄዎች አንዱ፣ “በያ ትውልድ ላይ ጨከኑበት” የሚል ነበር። ፕ/ር መስፍን ሲመልሱም፤ አልጨከንኩበትም እውነቱን ነው የተናገርኩት፣ አንዳንዶቹ እንደውም ተማሪዎቼ ነበሩና አነጋሬአቸዋለሁ፣ ፍላጎታቸው ለሀገርና ለሕዝብ ሳይሆን ሥልጣን ነበር ብለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሕአዴግ አይቀሬ ዕጣ - አስጊው የኢትዮጵያ ጣጣ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አንዱዓለም ተፈራ

መከወኛ ሃሳብ፤

ዛሬ ካለንበት የፖለቲካ ሀቅ ላይ ቆመን የነገዋን ኢትዮጵያ በሃሳብ ብንመለከት፤ ሶስት እውነታዎች ገጠው ይታያሉ። የመጀመሪያው፤ አሁን በሥልጣን ላይ ባለው የገዥ ቡድን አስተዳደር፤ ምንም ቢሆን ምንም፤ ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊኖራት አለመቻሉ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፤ ኢሕአዴግ፤ ውስጡ እየነቀዘ፤ ወደ አንድ ፓርቲነት ከማደግ ይልቅ፤ በየድርጅቶቹ መጎነታተል እየተወጣጠረ፤ ከውስጥ መርቅዞ ወደ መበታተኑ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው። ሶስተኛው ደግሞ፤ አሁን በያዝነው ሂደት፤ ሀገራችን እጅግ ወደ ከፋና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ውስጥ እየዘቀጠች መሆኗ ነው። እኒህ ፈጠው ያደገደጉ የፖለቲካ ሀቆች፤ በዚህ ጽሑፍ ተተንትነው ቀርበዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“በስመ ተቃዋሚ ተቃቅፎ መሳሳም” - ለትልቁ ዓላማ?

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

(ሶሊያና ሽመልስ /Soli S Gebremichael - Zone 9)

ከጥቂት ጊዜያት በፌት አንድ የመጽሐፍ ዳሰሳ ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር። መጽሐፉ “ፌኒክሷ ዛሬም፣ ሞታም ታንቀላፋለች” ሲሆን ጸሐፊዋ የቀድሞው የሕወሓት አባልና አመራር የአቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ወ/ሮ ውብማር ናቸው። በዳሰሳው ወቅት በትግል ጊዜ ለምን መጽሐፉ ላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እንዳልፈቱ ሲጠየቁ ወይዘሮዋ እንዲህ ብለው መልሰው ነበር።

“ደርግን የሚያህል ጠላት ከፊት ለፊታችን እያለ እንዴት እርስ በርስ በመጣላት ጊዜ እናባክናለን? ነጻ ስንወጣ የሕወሓት ፖሊሲና ፕሮግራም ሁሉንም ነገር ይፈታዋል።” ብለን ተውነው ይላሉ።

በኋላ ላይ ደግሞ ሕወሓትን ስለመለወጥ ሲጠየቁ ‹‹ሕወሓት ከዚህ በኋላ የሚለወጥ ድርጅት አይደለም አርጅቷል። 40 ዓመት በኋላ የድርጅት ባሕሪይ አይቀየርም›› ሲሉ ይከራከራሉ።

የትኛው ጠላት? የትኛው ትልቁ ዓላማ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ