በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳይ የተሰየመው ችሎት ‹አስገራሚ› ውሎ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

በላይ ማናዬ

∙ተከሳሾቹ ‹‹ዘረፋ›› ተፈጽሞብናል ብለዋል

∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያሌው

ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነቱን ጉባዔ በወፍ በረር

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ዳንኤል ተፈራ 

እንደ መነሻ 

ከሁለት ወር በፊት አንድነትን እንዲመሩ በጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡት ኢ/ር ግዛቸው ሺፈራው ጥቅምት ሁለት ቀን 2007 ዓ.ም ካቢኔያቸውን በትነው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አስረከቡ፡፡ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ኢ/ር ግዛቸው ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር በአመራራቸው ያልተደሰቱ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎችን የ‹‹ልቀቅ›› ጫና መቋቋም እንዳልቻሉና ከህሊናቸው ጋር ተማክረው ለፓርቲው ጥቅም ሲባል በፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ እንደወሰኑ ተናገሩ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ፡ እ.ኤ.አ ኖቬምብር 24/1974ን እናስታውስ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም:- ነጻነት ለሀገሬ)

ባለፈው ሳምንት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን/ት ቤተሰቦች ከዘመዶቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ታሪክ በመጥፎ ገጽታው ሲታወስ የሚኖረውን እ.ኤ.አ ኖቬምበር 14/1974 በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን የእልቂት ሰለባዎች ለማስታወስ በአንድ ላይ ተሰባስበው የጸሎት ስርዓት አድርገዋል፡፡ በዚያ የጥላቻ ዕለት የወታደራዊው አምባገነን ስብስብ ተራ ስብሰባ በማድረግ 60 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችን፣ የመንግስት ሰራተኞችን፣ አርበኞች ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸውን ወታደራዊ መኮንኖችን፣ የተማሩ ወታደራዊ ባለስልጣናትን እና የግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴን ልዩ የጥበቃ አባላት ያካተተ የግድያ እልቂት ለመፈጸም ተራ እና አስደንጋጭ ውሳኔን አሳለፈ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማንነት ፍለጋ! (ክፍል 1)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

አሰፋ ጫቦ

 

እንዲያው ዘው ተብሎ አይገባ ነገር! ” ቤቶች!” ተብሎ” ደጆች!” ተብሎ “ይግቡ/ግባ!” ተብሎ ነው እንጅ። ጠፍቼ ስነበትኩ።ከርምኩ ሳይሻል አይቀርም።”ለመሆኑ አስፋ ጫቦ የት ገባ” ብለው በአደባባይ ከጠየቁት ወሰንሰገድ ገ/ኪዳንንና እንዳለ ጌታ ከበደን ሌሎች እዚህ በስም ያልጠቀስኳቸዉን ሁሉ አመስግናለሁ።ለክፉም ለደጉም ጠያቂ አያሳጣችህ! እኔማ ሌላ ምን እላለሁ ! የቤት ክህነት አባቶች እንደሚሉት ሱባዔ ገብቼ ነበር።ከዚያው ከቤተክህነት ተውሸ፤(ነበርኩብትምና) “ዘኀሀለፈ ሥርየት ወለዘይመጽዕ እቅበት” እላለሁ። ነጠላ ትርጉሙ “ያለፈው ይሰረዝ ይደለዝ ለመጭው መታቀብን/መቆጠብን  ስጠኝ/ስጠን!” እንደማለት ነው።በምወደው መጽሐፍ Gone with Wind   ስካርሌት ኦሐራ (Scarlet O’Hara) Tomorrow is Another Day ትላለች።። “ነገም ሌላ ቀን ነዉ” ብሎታል ተርጏሚው ነብይ መኮንን።እኔም እንድያ እንዳልኩ ይቆጠርልኝ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእስክንድር ነጋ ያገባኛል ባይነት!

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

በላይ ማናዬ

‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚደረግ ደባ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

ለአራት አስርት ዓመታት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው እና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ከህዝብ ፍላጎት ውጭ በኃይል በስልጣን ወንበር ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የወሮበላ የማፊያ ቡድን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቀጣይነት ያለው እና የማያቋርጥ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የባህል ጦርነት በመክፈት ዕቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ