የነፃነቴ ዋጋ ነብሴ ነው!!!

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ግርማ ሰይፉ ማሩ

መረጃ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ጠቃሚ ነው ብሎ መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው፡፡ የተሟላ መረጃ የሰውን ልጅ ሙሉ ያደርገዋል፡፡ መረጃን አጣሞ ማቅረብ ደግሞ የሰውን ልጅ ውሳኔ ለማጣመም ካልሆነ በስተቀር ግቡ ምን ሊሆን እንደሚችል አይገባኝም፡፡ በሰሞኑ ሰው በላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጥርሱም በጥፍሩም ዘመቻ የጀመረው እኔ ላይ ነው፡፡ ዓላማው ግልፅ ነው፡፡ በነፃነት የማሰብ መብቴን ለድርድር እንዳቀርብ ነው፡፡ ለነፃነቴ ያለኝን ዋጋ የማያውቁ ሰዎችን ይህንን ለማድረግ ቢሞክር ካላቸው የመረጃ እጥረት ወይም ማወቅ ባለመፈለጋቸው ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታላቁ ረኃብ፡ ህወሀት አሁንም ቢሆን ለመስረቅ እና ለመዝረፍ ፈቃድ አለው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም - ነጻነት ለሀገሬ)

እ.ኤ.አ በ1984 የተከሰተው የኢትዮጵያ ታላቁ ረኃብ ሲታወስ (ክፍል 2)
ባለፈው ሳምንት ባቀረብኩት ትችቴ (እ.ኤ.አ በ1984 የተከሰተው የኢትዮጵያ ታላቁ ረኃብ ሲታወስ፡ ክፍል1)፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት ረኃብን በማስመልከት ሳቀርባቸው በነበሩት ትችቶች የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እና አሁን በህይወት የሌለው መሪው መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ረኃብ የለም በማለት ሙልጭ አድርገው በመካድ ሲያደርጉት የነበረውን ተራ ቅጥፈት በማጋለጥ በተጨባጭ መረጃዎች ላይ በመመስረት ስሞግት የቆየሁባቸውን ዋና ዋና ጭብጦች በማካተት ክለሳ ማድረጌ ይታወሳል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዝምታው ለምን ነው? (ጋዜጠኛ አንተነህ መርዕድ)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

- ኢትዮጵያ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለችው።
- መንግስት እንደድሮው መግዛት ተስኖታል
- ህዝቡም እንደድሮው መገዛት ታክቶታል
- የተቃዋሚው ቋንቋም እንደባቢሎኖች የተከፋፈለበት ወቅት ላይ ነን
- ከዚያም ብሶ ሚድያው ታፍኗል።
ትግሉን በተደራጀ መልክ ዳር የሚያደርስ ጠርቶ ባልወጣበት ሁኔታ ህዝባዊ ዓመጽ ሊፈነዳ ጫፍ ላይ መድረሱን ለማወቅ ሊቅነት የሚጠይቅ አልሆነም። በዚህ ኔታ ዐመጽ ከተነሳም የሚከተለው ትርምስና እልቂት ቀላል ስላይደለ ንፁህ ህሊና ያለው ሁሉ በግልፅ ታይቶት መፍራት አለበት። ይህ ፍርሃት በጎ ፍርሃት ሊሆን የሚችለው ወደ መፍትሄው መሄድ ካስቻለን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

‹‹እስሬ፣ ጥሩ ክርስቲያን ሰውና ታጋይ አድርጎኛል››

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

‹‹ኢህአዴግ በጭቆና ውስጥ ጸጥ ብሎ የተቀመጠን ሕዝብ እየቆሰቆሰ ነው››

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ከቃሊቲ እስር ቤት

(በኤሊያስ ገብሩ – ጋዜጠኛ)
ትናንት፣ በዕለተ ዓርብ እኔ እና የዕንቁ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከሆነው ፍቃዱ ማህተመወርቅ (ባሪያው) ጋር ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ፖለቲከኛን አቶ አንዷለም አራጌን በቃሊቲ ተገኝተን ጠይቀናቸው ነበር፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠለፋ ጋብቻ በኢትዮጵያ፡ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ወንጀል

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም- በነጻነት ለሀገሬ)

እውነታው ከልብወለድ በላይ እንግዳ ነገር ነው!

እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 7/2014 “ድፍረት፡ የፊልም ጠለፋ በኢትዮጵያ ” በሚል ርዕስ ባወጣሁት ትችት ድፍረት በሚለው ፊልም ላይ የኢትዮጵያ መሪ ተዋንያን ሆና በሰራችው የውርጃ ድርጊት ላይ የነበረኝን ቁጣ ገልጨ ነበር፡፡ በአበራሽ በቀለ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው ያ ፊልም በአሁኑ ጊዜ ጠለፋ እየተባለ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለአቅመ አዳም ባልደረሱ ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸመውን እውነተኛ ኢሰብአዊ እና ኋላቀር ልምድ በማጋላጥ እየተሰራ ያለውን የትወና ታሪክ ይተርክልናል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማለዳ ወግ … በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ / ደ.ህ.ዴ.ን ክብረ በዓል

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ነቢዩ ሲራክ

በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ክንፍ የደ.ህ.ዴ.ን ፖለቲካ ፖርቲ አባላት ወዳጆቸ ባደረጉልኝ ግብዣ መሰረት በደ.ህ.ዴ.ንን 22ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝቸ ነበር። እንደ ዛሬው የደ.ህ.ዴ.ን በዓል ፍሪዳ ተጥሎ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ድርጅቶች የልደት በዓላቸውን ሲያከብሩ እግር ጥሎኝ ስገኝ በምባረርበት የጅዳ ቆንስል ግቢ በሚገኘው የኮሚኒቲ አዳራሽ ተገኝቸም ኬክ እስኪቆረስና ሙዚቃው እስኪጀመር ያለውን ፕሮግራም ተከታትያለሁ። በልደት ፕሮግራሙ በቀረበው የድርጅቱ የትግልጉዞ “የስምጥ ሸለቆው ታጋዮች” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የደቡብ የነጻነት ታጋዮች ከህወሃት ጋር ተቀዳጅተው በቅድመ ደርግ ያደረጉትን ትግል ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር የሰማሁት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ