የሀብታሙ አያሌው ባለ አራት ምዕራፍ ፖለቲካ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ይገረም አለሙ

ሀብታሙ አያሌው
አቶ ሀብታሙ አያሌው

አቶ ሀብታሙ አያሌው እሱም ብዙ እያለ ስለ አርሱም እየተባለ ነው። ፖለቲካችንም ማህበራዊ ኑሮአችንም የተቃኘው በእውነት ላይ ሳይሆን በስሜት ላይ ሆነና አፍቅረን ሰንደግፍ ሆነ ጠልተን ስንነቅፍ ምክንያት ብቻ አይደለም ለከትም የለንም። ሜዳው ላይ ልጆች በዙና፣ ጨዋነት እየኮሰመነ ዋልጌነት እየገነነ መጣና ትላልቆቹ ዕድሜ ጠገቦቹ ተግባራቸው አገር ሊያድን፣ ረጋ ሰከን ብሎ ነገሮችን ግራ ቀኝ አይቶና መዝኖ የመደገፍም የመንቀፍም ባህል የሌለን መሆናችን ሰሞኑን በአቶ ሀብታሙ አያሌው ዙሪያም እየታየ ነው። ሜዳው ላይ ልጆች በዝተው ጨዋነት እየኮሰመነ ዋልጌነት በመግነኑ ትላልቆቹ ስራቸው አገር ሊያድን ምክራቸው ትውልድ ሊቀርጽ የሚችሉቱ አፋቸው ከመናገር እጃው ብእር ከማንሳት በመቆጠቡ ነገራችንን በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዲሉ አድርጎታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሞረሽ፣ ዋናውን ነገር ገሸሽ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ይገረም አለሙ

Major Dawit Woldegiorgis
ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ሻ/ቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ሲያትል በአገራዊ ንቅናቄው ስብሰባ ላይ የተናገሩትን አዳመጥኩት፣ ከዚህ ንግግር በመነሳት ከተጻፉት አንዳዶቹንም አነበብሁ “የሻለቃ ዳዊት የዋሽንግተን ሲያትል ንግግር በሞረሽ ዕይታ!” የሚለው ጽሁፍ በሁለት ምክንያት ቀልቤን ሳበው። የመጀመሪያውና እንዳነበው የገፋፋኝ በድርጅት ስም የተጻፈ መሆኑ ሲሆን፤ ይህችን አስተያየት እንድጽፍ ያበቃኝ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በሻ/ቃ ዳዊት የተነሱና ሞረሽ ከጻፈ አይቀር ምላሽ ሊሰጥባቸው ይገቡ የነበሩ አበይት ጉዳዩችን ወደ ጎን የተወ ሆኖ ማግኘቴ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መንግሥትነት ከቤት ይጀምራል

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ምሕረት ዘገዬ

Charity
Charity begins at home

ፈረንጆች “Charity begins at home” ይላሉ። እንዲህ ሲሉ መልካምነት ወይም በጎነት ከቤት እንደሚጀምር ለመግለጽ ነው። እኔም ከዚህ አባባል ኮርጄ “መንግሥትነት ከቤት ይጀምራል” አልሁ። በመሠረቱ ከቤት የማይጀምር ነገር የለም። ከቤት የሚጀምር ነገር በጎም ሆነ ክፉ በውጭም ይታያል። ከቤት ያልጀመረ ከውጭ አይመጣም። ስለዚህ የብዙ ነገሮች መሠረት ቤት ነው። የሰው ዕድገት የሚጀምረው ከቤት በመሆኑ ቤታችን በኛነታችን ላይ ያለው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም። “እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ” መባሉም ለዚህ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጣራው ለሚያፈስ ቤት፤ የወለል እድሳት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

ጣራው የሚያፈስ ቤት
ጣራው ለሚያፈስ ቤት፤ የወለል እድሳት

መላ አከላቷን ዝንጀሮ እሾህ ወግቷት

መቆም መራድ መቀመጥ ተስኖአት

የትኛውን እንንቀልልሽ ብለው ቢጠይቋት፣

ብታስቀድሙልኝ የመቀመጫየን

እኔ እነቅለዋለሁ ቁጭ ብዬ ሌላውን፣

በማለት መለሰች

ቅድሚያ የሚሰጠውን ነገር ስላወቀች።

ጣሪያው በሚያፈስ ቤት ውስት እየኖሩ ክረምት በመጣ ቁጥር እየተሰቃዩ በጋ ሲሆን የወቅት መለዋወጥ የተፈጥሮ ባህርይ መሆኑ ተዘንግቶ ነገር አለሙን በመርሳት ወለሉን ቢያድሱት ግድግዳውን ቀለም ቢያብሱት አይቀሬ ነውና ክረምት ሲመጣ የሚሆነውን አስቡት፤ ከንቱ ልፋት አጉል ብክነት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለአርበኛው ጸሐፊ ዕዝራ አስቻለው ዘለቀ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ግርማ በላይ

በተከታታይ የጻፍካቸውን ሁለት ግሩም መጣጥፎች በፍቅር አነበብኳቸው። በነዚህ ጽሑፎች እንደተረዳሁት ጥሩ አንባቢ ነህ፤ የብዕር አጣጣልህም ውብ ነው። አገርህንም እንደምትወድ በጽሑፍህ ብቻ ሣይሆን በረሃ መውረድህ ራሱም በቂ ምሥክር ነው። ማቄን ጨርቄን ሳትል ለአንዲት እናትህ ኢትዮጵያ ስትል እያሳለፍከው ያለኸውን መከራና ስቃይ መረዳት እችላለሁና የእምዬ አምላክ ይከተልህ። አንተን ብቻም ሣይሆን ለተመሳሳይ በጎ ዓላማ የተሰለፋችሁትን ጓዶችህንም ሁሉ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ፤ ያሰባችሁትንም ያሳካላችሁ። በረከቱ የሁላችንም ነውና። እኛም በጸሎት ከጎናችሁ አለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አስቸኳይ ማሳሰቢያ ለአማራ ምሁራንና ለአማራው በዲያስፖራ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በእውቀቱ ዘኢትዮጵያ

በአሁኑ ወቅት የአገራችን የኢትዮጵያ ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪ የሆነበትና የአገራችንም ህዝብ ከባድ መከራና ፍርሃት ውስጥ የተዘፈቀበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል፤ የአገሪቱ ሁኔታ ከፍተኛ ሥጋት ላይ መሆኑን ለችግሩ ዋና ምክንያት የሆኑት የወያኔ ገዢዋች እንኳን ሳይቀሩ አገሩ በእሳት ሊቃጠል እንደሚችል በግልፅ እየተናገሩበት ያለ ጉዳይ ነው። ይህ ሁኔታ አገርን በሚጎዳ መንገድ እንዳይሄድ ለማድረግ የምሁራን ድርሻ በጣም ከፍተኛ መሆን ይገባዋል። የአማራውና የኦሮሞ ህዝብ ያነሱት የፍትህና የእኩልነት ጥያቄዋች በአገሪቱ ገዢዎች መሀከል ዘንድ ከፍተኛ ትርምስ የፈጠረና ሁኔታውም በየት አቅጣጫ እንዲሚሄድ ለማወቅ በሚያስቸግር በመንታ መንገድ ላይ እንገኛለን። የኢትይጵያ ህዝብም የወያኔ የእሳት ማገዶ እንዳይሆን ትልቅ ሥራ ከፊት ለፊት ተደቅኗል። በአማራው ህዝብ ላይ የተፈፀመውና በመፈፀም ላይ ያለው ከባድ ግፍና መከራ በአማራው ህዝብ ውስጥ ኃይለኛ ብሶትን ፈጥሯል። ነገር ግን ይህ ብሶት ወደ በጎ ድል እንጂ ወደ ሽንፈት እንዳይሸጋገር ትልቅ ሥራ ያስፈልገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ