ኳስ እና የ"ቦይኮት" ፖለቲካ
ክንፉ አሰፋ

በዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ እና የአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫሎች ላይ የቦይኮት (እቀባ) ዘመቻዎች ተነስተው ነበር። የዘማቻዎቹን ውጤቶችም አይተናቸዋል። በዚች አጭር ጽሁፌ የማተኩረው በውጤቶቹ ላይ አይደለም። በሲያትሉም ሆነ በሮም ዝግጅቶች ላይ ስለነበርኩ፤ የቦይኮት ዘመቻዎቹ ከጅምሩ ጥቅም እና ጉዳቶችን አመዛዝነው ነበር ወይ? የሚለውን በጥቂቱ ለመፈተሽ እሞክራለሁ። በዚህ ርዕስ ላይ ስጽፍ አዋራ እንደሚነሳ አምናለሁ። በጉዳዩ ላይ እጅግ ብዙ ሰዎች ሲወያዩ ብታዘብም በፍርሃት ይሁን በሌላ ምክንያት ሃሳባቸውን በአደባባይ ለመናገር ግን ሲደፍሩ አይታይም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...








