ትንሽ ወግ ስለደምሴ ዳምጤ
አያልቅበት አደም
የደምሴን መታመም ከሰማሁ ወዲህ ያደረበት የስኳር ሕመም (ዲያቤቲክስ) የዓይኑን ብርሐን ከማሣጣት በዘለለ ይህን ያህል ለሕይወቱ ያሰጋል ብዬ አልገመትሁም። ለመጀመሪያ ሕክምና ወደ ባንኮክ ተጉዞ ሲመለስ የአንደኛው ዓይኑ ብርሐን ማጣት አስከፊ ዜና ቢኖርም የቀኝ ዓይኑ ብርሐን ወደ 20 ከመቶ የተመለሰ መሆኑንና ሊሻሻል እንደሚችል በመስማቴ ተመስገን ብያለሁ።
መቼም ስለደምሴ ዳምጤ የስፖርት ዘገባ በተለይ በስሜት ተውጦ የሚናገራቸው ነገሮች ብዙዎቻችን የምናስታውሣቸው ናቸው።
ሞስኮ ኦልምፕክ እና ደምሴ
የስፓርት ዜናውን ሱቅ ስንላክ ከሚጠበቅብን ጊዜ በልጅነት ልብና እግር በሩጫ ሰርቀን ዘውዴ ጠጅ ቤት ከጠጅ ቀጂው ብርሃኑ ኩርኩርም ጋር ድብብቆሽ እየተጫወትን እነ ምሩፅ ይፍጠርን ያየንበት ወቅት ነበር። ከዚያም ደምሴ ዳምጤ ስሜት እየተናነቀው “ጀግናው ምሩፅ ይፍጠር” በመጀመሪያ በ10 ሺህ ሜትር ከዚያም 5000 በድጋሚ በማሸነፉ ሁለት የወርቅ ሜዲሊያዎችን እንዳገኘና “ይፍጠር ዘ ሺፍተር” የሚል ቅጥያ ስም መጎናፀፉን ሲዘግብ የሩጫው ሜዳ አገላለፁ በጣም አስደማሚ ነበር። … (ሙሉውን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



