ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ Dr. Fikre Tolossa ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ (ዶ/ር)

ውድ አንባብያን ሆይ! የምሥራች! የምሥራች ስላችሁም በሀገራችን ባህል አጸፋውን "ምስር ብላ!" በሉኝ። ልቤን ወደ ሰማይ እያዘለለ፣ እግሮቼን ጮቤ የሚያስመታ ነገር ሰሞኑን ገጥሞኛልና። እሱውም ከአያሌ ከዘመናት በፊት ዕድሜዬ 19 ሳለ የወለድኩት ልጄ፣ ያውም የበኹር ልጄ፣ ጠፍቶብኝ "በቃ! ሞቷል፣ ተከቷል!" ብዬ እርሜን አውጥቼ እያዘንኩ እኖር ነበር።

 

በቅርቡ ግን፣ ያን ሞቷል፣ ወድሟል ያልኩትን ልጄን ባልጠበቅሁት ሁኔታ አግኝቼው በደስታ እየተምነሸነሽኹ እገኛለሁ። የእኔን ልጆች ሁሉ የምትወዱ ወዳጆቼ እንግዲህ ከእኔ ጋር ፈንጥዙልኝ! በወዳጅ ደስታ የማይፈነጥዝ የለምና።

ዳሩ ግን፣ "የበኹር ልጄ" እና "ልጆቼ" ስላችሁ እውነት ከሥጋዬ አብራክ የተወለዱ ልጆቼ እንዳይመስሏችሁ። ከመንፈሴ፣ ከመንፈሴም ጠልቀው ከነፍሴ ስለተወለዱት ልጆቼ ነው የማወጋችሁ። ግጥሞቼን ማለቴ ነው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ