የካምፓላ ማስታወሻ
ክንፉ አሰፋ
በምስራቅ አፍሪካ የስራ ጉብኝታችን፤ ከኪጋሊ-ሩዋንዳ ተነስተን አመሻሹ ላይ ካምፓላ ስንገባ ጸሃይ ብርሃንዋን ለጨረቃ አስተላልፋ እልም ብላ ጠፍታለች። ውቧ ካምፓላ በምሽት ከምድር በላይ 2000 ጫማ ርቀት ላይ ስትታይ በከፊል ጨለማና፤ በከፊል ብርሃን ተሸፍናለች። ይህም ከምእራቡ ዓለም ለሚገባ ተጓዥ እንግድነቱ እንዳለ ሆኖ ለጊዜው ግርታን ይፈጥራል። ‘በኢትዮጵያ የምንሰማው የመብራት በፈረቃ አባዜ እዚህም አለ እንዴ?’ ስል ጠየቅሁ ራሴን። ብዙም ሳልውል ግን ችግሩ የተፈጠረው የኡጋንዳ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ጣቢያው "ክፉኛ በመመታቱ" እንደሆነ ሰማሁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...




