በሳውዲ አረቢያ የተደበቁ እውነቶች (ነቢዩ ሲራክ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

የቀይ ባህሩዋን ፈርጥ-ጅዳን ያንቀጠቀጠው የዝናብና ጎርፍ (ክፍል 6)

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

ክፍል አምስት መጣጥፌ የት ላይ እንደቆመ አሳምሬ አውቀዋለሁና ግራ አትጋቡ ... እውነት እላችኋለሁ ቀኑ ሲደርስ እቀጥለዋለሁ ... የዛሬው ከዚህ በፊት እንደማደርገው የኔው ሰበር ዜና መሆኑን አንድ ካላችሁ ወደ መረጃ ቅበላየ ላቅና ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያዊያን መከራ (ክፍል-5 በነብዩ ሲራክ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

ሐጅ ወቅት ላይ ሆኖ ስለ ሮመዳንን ማውራት ሊከብድ ይችል ይሆናል። በዚህ ቀጣይ መጣጥፍ ቅኝቴ በኢትዮጵያዊያን የሳውዲ ዐረቢያ የኑሮ ታሪክ አስከፊ የነበረውን አጋጣሚ ማዘከር ነው። ለዚህም ለሆነው ሁሉ የቅርብ ምስክር ነበርኩና ከማስታወሻ ያሰፈርኩትን የተደበቁ እውነቶችን ወጋወግ ጊዜና ወቅት ሳይገድበው እያነሳሁ ብጥለው አትፍረዱብኝ! ቀኑ ሳይታሰብ መሽቶ ይነጋል። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!) 

በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያዊያን መከራ (ክፍል አራት)

የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar InactiveStar Inactive

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

በሳውዲ የኢትዮጵያዊያን ሮሮ - የተደበቁ እውነቶች ብየ በጀመርኩት ወጋወግ ዙሪያ ሆኗልና የሚቀድም የሚሰልሰውን አወጣለሁ አወርዳለሁ ... መስከረም በጠባ ማግስት ሌላው ቢቀር ከረመዳን ዋዜማ ጀምሮ በቀጠሉት ቀናት መከራው የበዛባቸውን ወገኖች ውሎ አዳር ለመቃኘት መሞከሬ እውነት ነው! ... (ሙሉውን ጽሁፍ አስነብበኝ!)

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ (ክፍል ሦስት)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ - የተደበቁ እውነቶች!

እስር ቤት ሰበራ!

ክፍል ሦስት

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

የረመዳን ዋዜማን ተንተርሸ ከክፍል አንድ ሁለት ያደረስኩትን ቀጣይ መጣጥፍ ሰፋ አድርጌ ለማስቃኘት ያያዝኩትን ዕቅድ የሚያሰናክል አጋጣሚ ተፈጥሯል። ምሽት ላይ ተርሂል ተብሎ ከሚጠራው የጅዳ ጊዜያዊ እስር ቤት ያገኙሁት የስልክ መልእክት ያላሰብኩት የአካሄድ ለውጥ ጠቋሚ ነበር! የተርሂል እስር ቤትን መከራ ሁለንተናዊ ገጽታና የወንድም እህቶቸን መከራ በቀጣይነት ላነሳው የነበረ ጉዳይ ቢሆንም ዛሬ አነሳው ዘንድ ተገደጃለሁ። ታሳሪዎች እጂግ ተማርረዋል። ሁኔታው መልኩን እየቀየረ መመጣቱን ከሚሰጡት የምሬትና የተስፋ መቁረጥ ቃላት መገመት ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ ቀልዶች

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ተስፋዬ ገብረአብ

ወያኔ ጉባዔውን አዳማ ላይ አካሄደ።

እናም ጉባዔው በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ንግግር ተቋጨ። አቶ መለስ ዜናዊም በኃይሌ ንግግር ሲስቅ በቴሌቭዥን ተመለከትነው። አቶ መለስ ዜናዊ፣ “በአምስት ዓመታት አጠናቅቀዋለሁ” ያለውን ትንግርታዊ፣ አስማታዊና ሰማያዊ የልማት ዕቅድ ዶክተር ኃይሌ ከአቶ መለስ ብሶ፣ “በሁለት ዓመታት እንጨርሰዋለን” ሲል ቃል ገባ። አያይዞም አትሌት ኃይሌ፣ “ስለ ሰከንድ ማሰብ አለብን” ሲል ተናገረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ (ክፍል ሁለት)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያውያን መከራ - የተደበቁ እውነቶች - በረመዳን ዋዜማ (ክፍል ሁለት)

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

ረመዳን ለመግባት የቀሩት ጥቂት ቀናት ናቸው። በመጀመሪያ ክፍል መጣጥፌ እየተውተረተርኩ ለማስረዳት እንደሞከርኩት "የዐረብ ሀገር ኑሮ መረረን! ኑሮ አንገሸገሸን በቃን! ወደ ሀገራችን እንገባ!?" በሚል በፖሊስ ለመያዝ ድልድይ ስለወደቁት ወገኖችና በሳውዲ ስለ ረመዳንን አቀባበል ሽር ጉድ የታዘብኩትን ለማሳየት ሞክሬያለሁ። አብዛኛው እህቶችና ጥቂት ወንድሞቸ ከተኮለኮሉበት ድልድይ ስር በደረሰባቸው የወረበላ ወከባ፤ መደብደብና መደፈር ተማርረው ጂዳ ወደ ሚገኘው ቆንስል መስሪያ ቤት ቢያቀኑም ምላሽ አለማግኘታቸውን ለማስቃኘት መዳዳቴን አትረሱትም። በአምስት ቀን ቆይታቸውን ካየሁትና ከግፉዓኑ የሰማሁትን የምስክርነት ቃል ላጋራችሁም ሞክሬያለሁ። ማንበብ እንዳላሰለቻችሁ በሚል የመጣጥፌን ሃሳቦች ሰብሰብ ለማድረግ በግርድፍ በግርድፉ ለማስቀመጥ ስሞክር አልፎ አልፎም ቢሆን የዓረፍተ ነገር መጣረስ የፊደል ግድፈት አልጠፋም። ለዚህም ይቅርታ ጠይቄ ወደ ዛሬ ወጋ ወጌ ላቅና ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...